Get Mystery Box with random crypto!

ዶ/ር ዳንኤል በቀለ በመንግሥት ግፍ የተፈፀመባቸውን እስረኞች መጠየቅ እንደማይችሉ ተነገራቸው። የ | 💚💛❤️ ዮቶራዊያን💚💛❤️

ዶ/ር ዳንኤል በቀለ በመንግሥት ግፍ የተፈፀመባቸውን እስረኞች መጠየቅ እንደማይችሉ ተነገራቸው።

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ኮሚሽነር  ዶክተር ዳንኤል በቀለ ከፍተኛ ሰብዓዊ መብት ጥሰት የተፈፀመባቸውን 28 የአማራ ተወላጆችን ሜክሲኮ በሚገኘው የፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ ሄደው ተጎጂዎችን ለማየት እና የተፈፀመባቸውን ሰብዓዊ ጥሰት ለማጣራት ቢሞክሩም ፖሊስ ጥቃት የደረሰባቸውን እስረኞች አላሳይም በማለት መመለሳቸውን ገልፀዋል።

ጥቃት የደረሰባቸው የአማራ ተወላጆች ግን ጥቃት የተፈፀመባቸውን አካላቸውን እና ዝርዝር ሁኔታውን  ፍርድ ቤት በቀረቡ ጊዜ ማስረዳታቸው ይታወቃል።

መፈንቅለ መንግሥት ለማድረግ ሞክራችኋል በሚል ለ28 ቀናት በኦሮሚያ ክልል ገላን ከተማ በሚገኘው የልዩ ኃይል ካምፕ ውስጥ ኢ-ሰብአዊ ድርጊት ሲፈፀምባቸው መቆየቱን ከዚህ በፊት መዘገባችን ይታወሳል።

ከ28 ታሣሪዎቹ መካከል የእግር እና የእጃቸው ጥፍር በፒንሳ የተነቀለ፣ ጀርባቸውን በኤሌክትሪክ የተገረፉ በዱላ እና በክላሽ ሰደፍ የተደበደቡ እንዳሉ ይታወቃል።