Get Mystery Box with random crypto!

💚💛❤️ ዮቶራዊያን💚💛❤️

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiomerejaa — 💚💛❤️ ዮቶራዊያን💚💛❤️
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiomerejaa — 💚💛❤️ ዮቶራዊያን💚💛❤️
የሰርጥ አድራሻ: @ethiomerejaa
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 24.98K
የሰርጥ መግለጫ

24 Hour News

Ratings & Reviews

2.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2023-03-10 17:13:46 በኢትዮጵያ በተወሰኑ የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ላይ የተደረገው ክልከላ እንዲነሳ አምነስቲ ጠየቀ

ኢትዮጵያ ውስጥ የቴሌግራም፣ ፌስቡክ ፣ ዩትዩብ መሰል የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች እስካሁን ምክንያቱ ግልፅ ባልተደረገበት ሁኔታ ገደብ ከተደረገባቸው ዛሬ 29ኛ ቀኑን ይዟል።

ይህን አስመልክቶ ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት አምነስቲ ኢንተርናሽናል እገዳው በአስቸኳይ እንዲነሳ ጠይቋል።

አምነስቲ የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት «በሰዎች ራሳቸውን የመግለጽና መረጃ የመፈለግና የማግኘት መብት ጣልቃ የመግባት ልምዳቸውን እንዲያቆሙ»ም አሳስቧል።

ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ በማኅበራዊ ትስስር ዘዴዎች ላይ የተደረገው እገዳ እንዲነሳ መጠየቃቸው ይታወሳል።
344 views14:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-10 17:13:16
312 views14:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-10 17:13:12 "አርሶ አደሩ በዚህ ልክ መሸጥ አለብህ ሊባል አይገባም!" ዶክተር ይልቃል ከፋለ

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ርእሰ መስተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፋለ መንግስት አርሶ አደሩ ያመረተውን ምርት በዝቅተኛ ዋጋ እንዲያስረክብ የሚል ትእዛዝ ከማውረዱ ጋር ተያይዞ ከምክር ቤት አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥተዋል።

ርእሰ መስተዳድሩ በሰጡበት ምላሽ የክልሉን የምርት ፍላጎት ማርካት አስፈላጊ ነው፤ ከዚያ ያለፈውን ለገበያ ማቅረብ ያስፈልጋል። አርሶ አደሩ በዚህ ልክ መሸጥ አለብህ ሊባል አይገባም፤ ገበያ በወሰነው መሠረት ሊሸጥ ይገባል ነው ያሉት።

አክለውም በአማራ ክልል በቂ ምርት አለ፤ በምርት መጠን ላይ መጨመር እንጂ መቀነስ አልታየም፡፡ ነገር ግን ገበያው አሻቅቧል። በገበያ ሕግ የማይመራ የገበያ ሥርዓት በመኖሩ የዋጋ ንረቱ ምክንያት ሁኗል ብለዋል።
310 views14:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-10 10:46:32 ዐበይት ዜናዎች

1፤ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ መለስ ዓለም የአሜሪካው ውጭ ጉዳይ ሚንስትር አንቶኒ ብሊንከን ኢትዮጵያን ሊጎበኙ መሆኑን ትናንት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ማስታወቃቸውን መግለጫውን የተከታተሉ ዜና ምንጮች ዘግበዋል። ብሊንከን በኢትዮጵያ ጉብኝታቸው፣ ከመንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናት ጋር እንደሚነጋገሩ ቃል አቀባዩ ተናግረዋል። ብሊንከን መቼ ኢትዮጵያን እንደሚጎበኙ ግን መለስ አልጠቀሱም። ብሊንከን ኢትዮጵያን ከጎበኙ፣ የሰሜኑ ጦርነት ከተቀሰቀሰ ወዲህ የአሁኑ ጉብኝታቸው የመጀመሪያቸው ይሆናል።

2፤ በኦሮሚያ ክልል የጉጂ ዞን የአገር ሽማግሌዎችና አባ ገዳዎች አዲስ በተዋቀረው ምሥራቅ ጉጂ ዞን ላይ ያላቸውን ቅሬታ ለፌደራሉና ለክልሉ መንግሥት ማቅረባቸውን ትናንት አዲስ አበባ ላይ በሰጡት መግለጫ መናገራቸውን የዋዜማ ሪፖርተር ዘግቧል። የአገር ሽማግሌዎቹ፣ የክልሉ መንግሥት የአዲሱን የምሥራቅ ቦረና ዞን ስያሜ እለውጣለሁ ማለቱን ሽማግሌዎቹ ተናግረዋል። አዲሱ ምሥራቅ ቦረና ዞን በቅርቡ የተደራጀው፣ ከቦረና፣ ጉጂ እና ባሌ ዞኖች አንዳንድ ቦታዎችን በማካተት ሲሆን፣ ሦስቱ ዞኖች ተመካክረው የዞኑ ስያሜ እንደሚቀየር እንደተነገራቸው የአገር ሽማግሌዎቹ ገልጸዋል። የጉጂ ዞን ዋና ከተማ ነገሌ ቦረና በአዲሱ ዞን ስር መካለሏንና ጉጂ ዞን ዋና ከተማውን አዶላ ሬዴ ላይ እንዲያደርግ የተወሰነውን ውሳኔ በመቃወም፣ በጉጂ ዞን የተቃውሞ ሰልፎችን ሲያደርጉ ሰንብተዋል።

3፤ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የከተማዋ የመኖሪያ ቤት አከራዮች እስከ መጭው ሰኔ ወር ድረስ የቤት ኪራይ እንዳይጨምሩ ውሳኔ ማሳለፉን አስታውቋል። የከተማዋ አስተዳደር፣ በከተማዋ የተከሰተውን የኑሮ ውድነትና ከፍተኛ የዋጋ ንረት ለመቆጣጠር በአስቸኳይ የእህል ምርት ወደ ከተማዋ በብዛት እንዲገባና እንዲሰራጭ የሚያስተባብር ግብረ ኃይል ማቋቋሙንም ገልጧል።

4፤ የተመድ ጸጥታው ምክር ቤት በሱዳን ዳርፉር ግዛትላይ የጣለውን የጦር መሳሪያ ማዕቀብ ለአንድ ዓመት አራዝሟል። ጸጥታው ምክር ቤት፣ ለዳርፉር ያቋቋመው የባለሙያዎች ተቆጣጣሪ ቡድን የሥራ ቆይታ ጭምር እንዲራዘም ወስኗል። ሆኖም ምክር ቤቱ ከቀነ ገደቡ በፊት ሁኔታዎችን እየገመገመ ማዕቀቡን ሊያሻሽል እንደሚችል ገልጧል። የሱዳን ወታደራዊ መሪዎች፣ ጸጥታው ምክር ቤት የጦር መሳሪያ ማዕቀቡን እንዲያነሳ ከፍተኛ ጥረት ሲያደርጉ ነበር። [ዋዜማ]
670 views07:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-09 21:41:48
436 views18:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-09 21:41:45 ዘመናዊ ባርነት በአማራ ክልል!
***
በተያዘው አመት ከ500 ሺ በላይ ሴቶችን ወደ አረብ ሀገራት ለመላክ ስልጠና ሊሰጣቸው መሆኑ ተሰምቷል።
የሚገርመው ደግሞ ይህ ስልጠና የሚሰጠው በአማራ ክልል ብቻ በሁሉም ዞኖች በተለይም በሞጣ፤ ደብረማርቆስ፤ ደጀን ከተሞች እድሜአቸው ከ18 አመት በላይ ለሆኑ ሴቶች ስልጠናው እንደሚሰጥ መገለጹ ነው።
1. ለምን አማራ ክልል ብቻ?
2. የአማራ ክልል መንግስት ይህንን ዘመናዊ ባርነት ማስቆም ሲገባው እና ዜጎች በሀገራቸው ሰርተው እንዲኖሩ ምቹ ሁኔታን መፍጠር ሲገባው ለምን ለባርነት በራሱ በመንግስት የስልጠና ወጪ ሽፋን ሰጥቶ ለመላክ ወሰነ?
3. የሚላኩት ዜጎችስ ዋስትና ምንድነው?
4. መንግስት ከአረብ ሀገራት ጋር ባለው የስራ ግንኙነት ተብሎ የተገለፀውስ ምን አይነት ስምምነት ነው?
434 views18:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-09 20:39:14
554 views17:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-09 20:39:09 ቡድኑ ወደ ስራ ሊገባ ነው!

የቤተክርስቲያን ችግሮች እና ዘለቄታዊ መፍትሔ ጥናትና ትግበራ ኮሚቴ በሚል ስያሜ የተቋቋመው እና ከሁሉም የሞያ ዘርፎች የተውጣጡ የቤተክርስቲያን ልጆችን ያቀፈው ቡድን ወደ  ትግበራ ሊገባ ነው።

ኮሚቴው የጥናታዊ  ጽሑፍ በማቅረብ አላማውን እና የአሰራር ሂደቱን ያብራራ ሲሆን ሰፊ ውይይት  አካሂዷል።
በቅድስት ቤተክርስቲያን መዋቅር  ውስጥ ከዶግማ በስተቀር ከላይ ጀምሮ እስከ ታች ድረስ ያሉችግሮችን ለማስተካከል እንደሠራም ተገልጿል ።
ውጤቱን በተመለከተ  ቤተክርስቲያን የራሷ መንፈሳዊ ፍርድ ቤት እንዲኖራት ማድረግን ጨምሮ 25 ዝርዝር ነጥቦች ላይ አተኩሯል።  ከ90በላይ አባላትን በጥናት ያሳተፈው ኮሚቴ በ14ቡድኖች ተዋቅሮ ስራውን በቅርቡ ይጀምራል ።

ምንጭ:-EOTC TV
533 views17:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-09 20:20:46
532 views17:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-09 20:20:43 2 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር የህዝብና የሀገር ሀብት ለብክነት መዳረጉ ተገለጸ

የብሔራዊና የክልል የጸረ-ሙስና ኮሚቴ ከተቋቋመ ጊዜ ጀምሮ 759 ጥቆማዎች የደረሱት ሲሆን በ175 ጥቆማዎች ላይ ምርመራ በማድረግ በ81ዱ ላይ የክስ መዝገብ ማደራጀቱን እና የክስ መዝገብ በተደራጀባቸው መዝገቦች ውስጥም 640 ተጠርጣሪዎች መኖራቸውን አሳውቋል።

እስከ አሁን በተደረጉ የማጣራት ሥራዎችም 2 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር ግምት ባላቸው የመንግሥትና የሕዝብ ኃብት ላይ ጉዳት መድረሱ የተረጋገጠ ሲሆን በሌላ በኩል 25,885 ካ.ሜ በምርመራ የሙስና ወንጀል ተፈፅሞ መገኘቱን ተጠቁሟል።

ይህ የተባለው የብሔራዊና የክልል የጸረ-ሙስና ኮሚቴ ሰብሳቢዎችና አባላት የጋራ የአፈጻጸም ግምገማ በሚካሄድበት መድረክ ነው።
530 views17:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ