Get Mystery Box with random crypto!

በኢትዮጵያ በተወሰኑ የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ላይ የተደረገው ክልከላ እንዲነሳ አምነስቲ ጠየቀ | 💚💛❤️ ዮቶራዊያን💚💛❤️

በኢትዮጵያ በተወሰኑ የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ላይ የተደረገው ክልከላ እንዲነሳ አምነስቲ ጠየቀ

ኢትዮጵያ ውስጥ የቴሌግራም፣ ፌስቡክ ፣ ዩትዩብ መሰል የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች እስካሁን ምክንያቱ ግልፅ ባልተደረገበት ሁኔታ ገደብ ከተደረገባቸው ዛሬ 29ኛ ቀኑን ይዟል።

ይህን አስመልክቶ ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት አምነስቲ ኢንተርናሽናል እገዳው በአስቸኳይ እንዲነሳ ጠይቋል።

አምነስቲ የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት «በሰዎች ራሳቸውን የመግለጽና መረጃ የመፈለግና የማግኘት መብት ጣልቃ የመግባት ልምዳቸውን እንዲያቆሙ»ም አሳስቧል።

ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ በማኅበራዊ ትስስር ዘዴዎች ላይ የተደረገው እገዳ እንዲነሳ መጠየቃቸው ይታወሳል።