Get Mystery Box with random crypto!

'አርሶ አደሩ በዚህ ልክ መሸጥ አለብህ ሊባል አይገባም!' ዶክተር ይልቃል ከፋለ የአማራ ብሔራዊ | 💚💛❤️ ዮቶራዊያን💚💛❤️

"አርሶ አደሩ በዚህ ልክ መሸጥ አለብህ ሊባል አይገባም!" ዶክተር ይልቃል ከፋለ

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ርእሰ መስተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፋለ መንግስት አርሶ አደሩ ያመረተውን ምርት በዝቅተኛ ዋጋ እንዲያስረክብ የሚል ትእዛዝ ከማውረዱ ጋር ተያይዞ ከምክር ቤት አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥተዋል።

ርእሰ መስተዳድሩ በሰጡበት ምላሽ የክልሉን የምርት ፍላጎት ማርካት አስፈላጊ ነው፤ ከዚያ ያለፈውን ለገበያ ማቅረብ ያስፈልጋል። አርሶ አደሩ በዚህ ልክ መሸጥ አለብህ ሊባል አይገባም፤ ገበያ በወሰነው መሠረት ሊሸጥ ይገባል ነው ያሉት።

አክለውም በአማራ ክልል በቂ ምርት አለ፤ በምርት መጠን ላይ መጨመር እንጂ መቀነስ አልታየም፡፡ ነገር ግን ገበያው አሻቅቧል። በገበያ ሕግ የማይመራ የገበያ ሥርዓት በመኖሩ የዋጋ ንረቱ ምክንያት ሁኗል ብለዋል።