Get Mystery Box with random crypto!

💚💛❤️ ዮቶራዊያን💚💛❤️

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiomerejaa — 💚💛❤️ ዮቶራዊያን💚💛❤️
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiomerejaa — 💚💛❤️ ዮቶራዊያን💚💛❤️
የሰርጥ አድራሻ: @ethiomerejaa
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 24.98K
የሰርጥ መግለጫ

24 Hour News

Ratings & Reviews

2.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 5

2023-02-10 18:42:57 መረጃ

ቅዱስ ሲኖዶስ በሰጠው መግለጫ ከጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ጋር በነበረው ውይይት የቤተክርስቲያኗ ብዙ ጥያቄዎቿ እንደተመለሰላትና ነገ ጥዋት 3 ሰዓት ላይ ዝርዝር እና ሰፊ መግለጫ እንደሚሰጥ አሳውቋል።
1.0K views15:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-10 17:11:57 አዋሽ ባንክ  ከሰሞኑ ፆመ ነነዌን አስመልክቶ ሲኖዶሱ ካስተላለፈው የአለባበስ ውሳኔ  ጋር በተያያዘ የተሰጠኝ ስም ሀሰት ነው ብሏል

(እለታዊ የኢትዩትዩብ መረጃዎች)

በማህበራዊ የትስስር ገፁ ላይ እንዳሰፈረው ሰሞኑን ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሐይማኖት ጋር ተያይዞ በተፈጠረው ችግርና ቅዱስ ሲኖዶሱ በፆመ ነነዌ ለእምነቱ ተከታዮች ባስተላለፈው የፆምና ፀሎት ፕሮግራም ላይ ሊከተሉ ከሚገባው የአለባበስ ስርዓት ጋር ተያይዞ  በጥቂት ግለሰቦችና ቡድኖች የባንኩን ስም የማጠልሸት የተደረገው ጥረት ፍፁም ስህተት ነው ብሏል።

ባንኩ  ከማንኛውም ሐይማኖታዊና ፖለቲካዊ ጣልቃ ገብነት የፀዳ መሆኑን በመግለፅ  በባንኩ ውስጥ የሚሰራ ማንኛውም ሰራተኛ ከከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች እስከ ታችኛው የስራ መደብ ያሉት የራሳቸውን የግል አመለካከት፣ ሐይማኖታዊና ፖለቲካዊ አቋም ያላቸው እንደመሆኑ መጠን የማንንም መብት የማይነካና ጣልቃ የማይገባ መሆኑን ገልጿል።

በመሆኑም ሰሞኑን የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሐይማኖት ተከታይ ሰራተኞቹ ጥቁር ልብስ እንዳይለብሱ ከልክሏል፣ የለበሱትንም ከስራቸው አባሯል ተብሎ የተነዛው መሰረተ ቢስ ወሬ ከእውነት የራቀ፣ በፍፁም አዋሽን የማይመለከት መሆኑን ለክቡራን ደንበኞቻችንና ለመላው ህዝባችን በትህትና ማሳወቅ እንፈልጋለን፡፡

ስለዚህ በእነዚህ ጥቂት ግለሰቦች ለወዲፊቱም ተመሳሳይ አሉባልታዎች ቢነዙም አዋሽን የማይመለከት መሆኑን እየገለፅን የባንኩን ስም በማጠልሸት ተግባር ላይ የተሳተፉትን በህግ የሚጠይቅ መሆኑንም አሳውቋል።
1.1K views14:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-09 16:57:37 የመንግስት ጣልቃ መግባት በሀገር ሰላምና ደህንነት ላይ ስጋት እየፈጠረ ነው ሲል ኢዜማ አሳሰበ!

“በአሁኑ ወቅት ግልፅ በሆነ መንገድ ጣልቃ እየገባ ያለው መንግሥት ለሀገር ሰላምና ደህንነት ስጋት እየፈጠረ” ነው ሲል የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ) አሳሰበ።ፓርቲው ዛሬ ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው መንግስት የፈጠረውን ስጋት ተገንዝቦ “ኃላፊነቱ ህግን አክብሮ ማስከበር መሆኑን በመረዳት እንዲንቀሳቀስ ለማሳሰብ እንወዳለን” ሲል አስታውቋል።

መንግስት በህገ መንግስቱ መሰረት ገለልተኛ መሆን እና ህኝ ማስከበር ሲገባው በገሀድ ያሳየው ወገንተኝነት እንዳሳዛነው የገለፀው ኢዜማ ለተፈጠሩት ቀውሶች መንግስት ተጠያቂነት አለበት ብሏል።

በኦሮሚያ ክልል “በተደጋጋሚ የሚስተዋሉ የንፁሐን ዜጎችን ሞት፣ አስከፊ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችና መፈናቀሎችን ተቆጣጥሮ ሰላምና ደኅንነትን ማስከበር ያልቻለው የክልሉ መንግሥት በሃይማኖት ጉዳይ ላይ ጣልቃ እየገባ እንደሀገር ያለንበትን ችግር ውስብስብ እያደረገው ይገኛል” ሲልም ፓርቲው አስታውቋል።በተጨማሪም “የፌደራል መንግሥቱም ቢሆን ይህን ዐይን ያወጣ ጣልቃ ገብነት በገሀድ እያየ የዜጎችን ሰላምና ደህንነት ለማስጠበቅ ምንም ዓይነት እርምጃ ባለመውሰዱ ዋነኛው ተጠያቂ ያደርገዋል” በማለት የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ ገልጿል።
1.0K views13:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-09 15:59:43 የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ለዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና ራሳቸውን እንዲያዘጋጁ ትምህርት ሚኒስቴር አሳሰበ

የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር) በመውጫ ፈተና ዙሪያ ከተማሪዎች ህብረት ተወካዮች ጋር የተወያዩ ሲሆን የመውጫ ፈተና በመጪው ሐምሌ ወር በኦንላይን ለሁሉም የመንግስትና የግል ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች እንደሚሰጥ ገልጸዋል። ለሚሰጠው የመውጫ ፈተና ብቁ ለመሆንም ተማሪዎች በየዩኒቨርሲቲዎቹ የሚሰጠውን የመጨረሻውን ሴሚስተር ፈተና መውሰድና ኮርሶችን ማጠናቀቅ እንደሚገባም አስገንዝበዋል፡፡

ለፈተናው በሁሉም የትምህርት መስኮች ላይ የተመረጡ ኮርሶች የብቃት ልየታ ተደርጎላቸው ዩኒቨርሲቲዎች እንዲያውቁት መደረጉን የጠቆሙት ሚኒስትር ዴኤታው በአሁኑ ወቅት የፈተና ንድፈ ማሳያና የፈተና ዝግጅት ስራ በመከናወን ላይ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡ በመሆኑም ተማሪዎች በቀሪዎቹ አምስት ወራት ተገቢውን ዝግጅት በማድረግ ራሳቸውን ለፈተናው ብቁ ማድረግ እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡

በመድረኩ የተገኙ የተማሪዎች ህብረት ተወካዮችም ወደ ዩኒቨርሲቲዎቻቸው ሲመለሱ ተማሪዎች ለፈተናው በቂ ዝግጅት እንዲያደርጉ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው ሚኒስትር ዴኤታው ተናግረዋል፡፡በውይይቱ ከሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች የተውጣጡ የተማሪዎች ህብረት ፕሬዝዳንቶች መገኘታቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
1.2K views12:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-08 17:55:31 ኢትዮጵያ ፈላጭ ቆራጭ የመንግሥት አገዛዝ ካላቸው አገራት መካከል አንዷ ሆነች

ከዓለም ሕዝብ መካከል 8 በመቶ ያክሉ ብቻ በ“ሙሉ ዲሞክራሲ” ሥርዓት ውስጥ እንደሚኖሩ ተገልጿል

ረቡዕ ታሕሳሥ 1 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ) ከሰሞኑ ይፋ በሆነውና የዓለም አገራትን የዴሞክራሲን ሁኔታ በሚለካው የፈረንጆቹ 2022 ዓመት የዲሞክራሲ ኢንዴክስ፤ ኢትዮጵያን ፈላጭ ቆራጭ የመንግሥት አገዛዝ ካላቸው አገራት መካከል አንዷ አድርጓታል፡፡

“ኢኮኖሚስት ኢንተለጀንስ” የተሰኘው ተቋም ይፋ ያደረገው የአገራት ዓመታዊ የዲሞክራሲ ኢንዴክስ ጥናት፤ ኢትዮጵያ ባለፈው የፈረንጆቹ 2022 በፈላጭ ቆራጭ የመንግሥት አስተዳደር ውስጥ ማለፏን አመላክቷል፡፡

የዲሞክራሲ ኢንዴክስ ጥናቱ የ167 የዓለም አገራትን የዲሞክራሲ ዕድገት ደረጃ መሰረት አድርጎ ዓመታዊ ሁኔታን እየገመገመ ይመድባል፡፡

ምደባው የሚካሄደው ዴሞክራሲን ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ የሚያድርጉ፣ በከፊል ተግራዊ የሚያደርጉ፣ ከዲሞክራሲም ከፈላጭ ቆራጭም የሚቀላቅሉ እና ፈላጭ ቆራጭ አስተዳደር የተከተሉ ብሎ ይመድባቸዋል፡፡

የዴሞክራሲ ኢንዴክሱ የተጠናቀረው ከ60 መስፈርቶችን ግምት ውስጥ በማስገባት ሲሆን፤ ምዘናው በአምስት ዋና ዋና ምድቦች ይከናወናል፡፡ የዜጎች ነፃነት፣ ምርጫና ብዝሃነት፣ የሕዝብ የፖለቲካ ተሳትፎ፣ የመንግሥት እንቅስቃሴ እና የፖለቲካ ባህል ዋና ጠቋሚዎች ናቸው፡፡

በጥናቱ መሰረት ከመላው የዓለም ሕዝብ መካከል 8 በመቶ ያክሉ ብቻ በ“ሙሉ ዲሞክራሲ” ሥርዓት ውስጥ ይኖራሉ ተብሏል፡፡ ቀሪው የዓለም ሕዝብ ከለዘብተኛ ዲሞክራሲ እስከ ፈላጭ ቆራጭ አገዛዝ ባሉት የአገዛዝ ስርዐቶች ውስጥ የሚኖር ነው፡፡

የአገራት ዴሞክራሲ መረጃ ጠቋሚው ጥናቱ እንደ ፈረንጆቹ 2007 ለመጀመሪያ ጊዜ የተጠናቀረ ሲሆን፣ ከ2010 ጀምሮ ዓመታዊ ሆኗል።
1.0K views14:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-08 17:54:58
945 views14:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-08 17:54:53 በመዲናዋ የሞተር ብስክሌት እና የባጃጅ እንቅስቃሴ ተከለከለ

ረቡዕ ታሕሳሥ 1 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ) በመዲናዋ አዲስ አበባ ከሚካሄደው 36ኛው የአፍሪካ ሕብረት ስብሰባ ጋር ተያይዞ፤ ከዛሬ የካቲት 1/2015 ከቀኑ 6:00 ሰዓት ጀምሮ በከተማዋ ሞተር ብስክሌት እና የባለ ሦስት እግር ተሽከርካሪ (ባጃጅ) ማሽከርከር የተከለከለ መሆኑን የከተማው የትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ አስታውቋል።

በዚሁ መሰረት ከዛሬ ከቀኑ 6:00 ሰዓት ጀምሮ እስከ የካቲት 5/2015 አመሻሽ 12:00 ሰዓት ድረስ በከተማዋ የባለ ሦስት እግር ተሽከርካሪ (ባጃጅ) በማሽከርከር ፍጹም የተከለከለ መሆኑን ኤጀንሲው ገልጿል።

እንዲሁም፤ ሞተር ብስክሌቶችን ከዛሬ የካቲት 1/2015 ጀምሮ 36ኛው የአፍሪካ ሕብረት ስብሰባ እስኪጠናቅ የካቲት 13/2015 አመሻሽ 12:00 ሰዓት ድረስ ማሽከርከር ፍጹም የተከለከለ መሆኑንም አስታውቋል።

ኤጀንሲው ክልከላው የሚመለከተው የፀጥታ እና የትራፊክ ቁጥጥር ሥራ አካላት ከሚጠቀሙባቸው ውጪ በአዲስ አበባ ከተማ በኹሉም አካባቢዎች የሚንቀሳቀሱ ባጃጆችን፣ ባለሁለት እግር ሞተር ብስክሌቶችንና በኤሌክትሪክ የሚሰሩትን ጭምር መሆኑን ገልጿል፡፡

የባጃጅ ባለንብረቶችና አሽከርካሪዎች፣ የሞተር ብስክሌት ባለንብረቶችም ሆኑ አሽከርካሪዎች ይሄንኑ ክልከላ መሰረት በማድረግ፤ እስከ ተጠቀሰው ቀን ድረስ በትዕግስት እንዲጠብቁ ኤጀንሲው ያሳሰበ ሲሆን፤ ይህንን መልዕክት በሚተላለፉ አካላት ላይ ጥብቅ እርምጃ እንደሚወስድም አስታውቋል፡፡
893 views14:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-08 17:54:17
847 views14:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-08 17:54:11 ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ከመንግስት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ጋር ተወያይተዋል::

Prime Minister Abiy Ahmed held a discussion this afternoon on current issues with senior government officials.

#PMOEthiopia
803 views14:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-08 15:54:14 በቱርክ እና ሶርያ በደረሰ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ የሟቾች ቁጥር ከ7 ሺ 800 በላይ ሆኗል

በደቡብ ምስራቅ ቱርክ በጋዚያንቴፕ ከሶሪያ ድንበር አቅራቢያ በተከሰተዉ ኃይለኛ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ በቱርክ ብቻ ከ5 ሺ 894 በላይ ሰዎች ህይወት አልፏል።የቱርኩ ፕሬዝዳንት ሬሴፕ ጣይብ ኤርዶጋን በሰኞው አሰቃቂ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ በከፋ ጉዳት በደረሰባቸው 10 ግዛቶች ዉስጥ ለሦስት ወራት የሚቆይ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አውጀዋል።

በ10 ከተሞች ከ13 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በሀገሪቱ ከ1939 ዓ.ም ወዲህ ባጋጠሟት ከባድ የመሬት መንቀጥቀጥ ተጎድተዋል።

የቱርኩ ፕሬዝዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን በትዊተር ገፃቸው ላይ ባሰፈሩት መልዕክት በመሬት መንቀጥቀጡ ወደተመቱ አካባቢዎች የፍለጋ እና የነፍስ አድን ቡድን የሚሰሩ ባለሙያዎች ወዲያውኑ መላኩን ገልጸዋል።

በጉዳዩ ላይ መረጃ ለማሰባሰብ ከተጎዱት የስምንት ግዛቶች አስተዳዳሪዎች ጋር በስልክ መነጋገራቸውን የጽህፈት ቤታቸው መግለጫ አስታውቋል።ፕሬዝዳንቱ አክለዉ አሜሪካ፣ እንግሊዝን እና ደቡብ ኮሪያን ጨምሮ እርዳታ ላደረጉ 70 ሀገራት ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ኳታር 10 ሺ  ተንቀሳቃሽ ቤቶችን በቱርክ እና ሶሪያ የመሬት መንቀጥቀጥ ለተጎዱ አካባቢዎች ከ120 የነፍስ አድን ሰራተኞችን ጋር ልካለች፡፡ከ11 ዓመታት በላይ በዘለቀው የእርስ በርስ ጦርነት ክፉኛ በተጎዳችው ሶሪያ፣ ከ1 ሺ 932  በላይ ሰዎች መሞታቸውንና 3 ሺ 500የሚያህሉ ሰዎች መቁሰላቸውን የሶርያ የመንግስትና ወዶ ገቡ የነጭ ቆብ የረድኤት ተቋም አስታዉቋል።

የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋው በሶርያ ሐማ፣ አሌፖ እና ላታኪያ ግዛቶች በርካታ ሕንፃዎችን አውድሟል።የዩናይትድ ስቴትስ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ በጋዚያንቴፕ ከተማ አቅራቢያ 17 ነጥብ 9 ኪ.ሜ ያለው ጥልቀትና  በሬክተር  ስኬል 7 ነጥብ 8 የተለካ አደጋ መድረሱን ይፈ አድርጓል።

የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋው የተሰማው በዋና ከተማዋ አንካራ እና በሌሎች የቱርክ ከተሞች እንዲሁም በሰፊው የሀገሪቱ ክልል መሆኑን ዳጉ ጆርናል ዘግቧል።በአደጋው በርካታ ሕንፃዎች የፈረሱ ሲሆን በዲያርባኪር ከተማ አንድ ሰፊ የገበያ አዳራሽ ወድሟል።

አንድ እማኝ  እንደተናገሩት እኔ ያረፈኩበት ቤት ለ45 ሰከንድ ያህል መንቀጥቀጡን ተናግረዋል። የቱርክ የመሬት መንቀጥቀጥ ተመራማሪዎች አደጋው በሬክተር ስኬል 7 ነጥብ 4 የተለካ እንደሆነ ገምተዋል። ከደቂቃዎች በኋላ ሁለተኛ መንቀጥቀጥ አካባቢውን እንደመታ ተናግረዋል።ቱርክ በዓለም ላይ ከፍተኛ የሆነ የመሬት መንቀጥቀጥ ከሚደርስባቸው ዞኖች ውስጥ አንዷ ነች። እ.ኤ.አ. በ 1999 በቱርክ ሰሜን ምዕራብ ክፍል በደረሰ ከባድ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ ከ17 ሺ  በላይ ሰዎች ህይወታቸው አልፏል።
1.2K views12:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ