Get Mystery Box with random crypto!

በቱርክ እና ሶርያ በደረሰ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ የሟቾች ቁጥር ከ7 ሺ 800 በላይ ሆኗል በ | 💚💛❤️ ዮቶራዊያን💚💛❤️

በቱርክ እና ሶርያ በደረሰ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ የሟቾች ቁጥር ከ7 ሺ 800 በላይ ሆኗል

በደቡብ ምስራቅ ቱርክ በጋዚያንቴፕ ከሶሪያ ድንበር አቅራቢያ በተከሰተዉ ኃይለኛ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ በቱርክ ብቻ ከ5 ሺ 894 በላይ ሰዎች ህይወት አልፏል።የቱርኩ ፕሬዝዳንት ሬሴፕ ጣይብ ኤርዶጋን በሰኞው አሰቃቂ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ በከፋ ጉዳት በደረሰባቸው 10 ግዛቶች ዉስጥ ለሦስት ወራት የሚቆይ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አውጀዋል።

በ10 ከተሞች ከ13 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በሀገሪቱ ከ1939 ዓ.ም ወዲህ ባጋጠሟት ከባድ የመሬት መንቀጥቀጥ ተጎድተዋል።

የቱርኩ ፕሬዝዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን በትዊተር ገፃቸው ላይ ባሰፈሩት መልዕክት በመሬት መንቀጥቀጡ ወደተመቱ አካባቢዎች የፍለጋ እና የነፍስ አድን ቡድን የሚሰሩ ባለሙያዎች ወዲያውኑ መላኩን ገልጸዋል።

በጉዳዩ ላይ መረጃ ለማሰባሰብ ከተጎዱት የስምንት ግዛቶች አስተዳዳሪዎች ጋር በስልክ መነጋገራቸውን የጽህፈት ቤታቸው መግለጫ አስታውቋል።ፕሬዝዳንቱ አክለዉ አሜሪካ፣ እንግሊዝን እና ደቡብ ኮሪያን ጨምሮ እርዳታ ላደረጉ 70 ሀገራት ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ኳታር 10 ሺ  ተንቀሳቃሽ ቤቶችን በቱርክ እና ሶሪያ የመሬት መንቀጥቀጥ ለተጎዱ አካባቢዎች ከ120 የነፍስ አድን ሰራተኞችን ጋር ልካለች፡፡ከ11 ዓመታት በላይ በዘለቀው የእርስ በርስ ጦርነት ክፉኛ በተጎዳችው ሶሪያ፣ ከ1 ሺ 932  በላይ ሰዎች መሞታቸውንና 3 ሺ 500የሚያህሉ ሰዎች መቁሰላቸውን የሶርያ የመንግስትና ወዶ ገቡ የነጭ ቆብ የረድኤት ተቋም አስታዉቋል።

የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋው በሶርያ ሐማ፣ አሌፖ እና ላታኪያ ግዛቶች በርካታ ሕንፃዎችን አውድሟል።የዩናይትድ ስቴትስ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ በጋዚያንቴፕ ከተማ አቅራቢያ 17 ነጥብ 9 ኪ.ሜ ያለው ጥልቀትና  በሬክተር  ስኬል 7 ነጥብ 8 የተለካ አደጋ መድረሱን ይፈ አድርጓል።

የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋው የተሰማው በዋና ከተማዋ አንካራ እና በሌሎች የቱርክ ከተሞች እንዲሁም በሰፊው የሀገሪቱ ክልል መሆኑን ዳጉ ጆርናል ዘግቧል።በአደጋው በርካታ ሕንፃዎች የፈረሱ ሲሆን በዲያርባኪር ከተማ አንድ ሰፊ የገበያ አዳራሽ ወድሟል።

አንድ እማኝ  እንደተናገሩት እኔ ያረፈኩበት ቤት ለ45 ሰከንድ ያህል መንቀጥቀጡን ተናግረዋል። የቱርክ የመሬት መንቀጥቀጥ ተመራማሪዎች አደጋው በሬክተር ስኬል 7 ነጥብ 4 የተለካ እንደሆነ ገምተዋል። ከደቂቃዎች በኋላ ሁለተኛ መንቀጥቀጥ አካባቢውን እንደመታ ተናግረዋል።ቱርክ በዓለም ላይ ከፍተኛ የሆነ የመሬት መንቀጥቀጥ ከሚደርስባቸው ዞኖች ውስጥ አንዷ ነች። እ.ኤ.አ. በ 1999 በቱርክ ሰሜን ምዕራብ ክፍል በደረሰ ከባድ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ ከ17 ሺ  በላይ ሰዎች ህይወታቸው አልፏል።