Get Mystery Box with random crypto!

የመንግስት ጣልቃ መግባት በሀገር ሰላምና ደህንነት ላይ ስጋት እየፈጠረ ነው ሲል ኢዜማ አሳሰበ! | 💚💛❤️ ዮቶራዊያን💚💛❤️

የመንግስት ጣልቃ መግባት በሀገር ሰላምና ደህንነት ላይ ስጋት እየፈጠረ ነው ሲል ኢዜማ አሳሰበ!

“በአሁኑ ወቅት ግልፅ በሆነ መንገድ ጣልቃ እየገባ ያለው መንግሥት ለሀገር ሰላምና ደህንነት ስጋት እየፈጠረ” ነው ሲል የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ) አሳሰበ።ፓርቲው ዛሬ ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው መንግስት የፈጠረውን ስጋት ተገንዝቦ “ኃላፊነቱ ህግን አክብሮ ማስከበር መሆኑን በመረዳት እንዲንቀሳቀስ ለማሳሰብ እንወዳለን” ሲል አስታውቋል።

መንግስት በህገ መንግስቱ መሰረት ገለልተኛ መሆን እና ህኝ ማስከበር ሲገባው በገሀድ ያሳየው ወገንተኝነት እንዳሳዛነው የገለፀው ኢዜማ ለተፈጠሩት ቀውሶች መንግስት ተጠያቂነት አለበት ብሏል።

በኦሮሚያ ክልል “በተደጋጋሚ የሚስተዋሉ የንፁሐን ዜጎችን ሞት፣ አስከፊ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችና መፈናቀሎችን ተቆጣጥሮ ሰላምና ደኅንነትን ማስከበር ያልቻለው የክልሉ መንግሥት በሃይማኖት ጉዳይ ላይ ጣልቃ እየገባ እንደሀገር ያለንበትን ችግር ውስብስብ እያደረገው ይገኛል” ሲልም ፓርቲው አስታውቋል።በተጨማሪም “የፌደራል መንግሥቱም ቢሆን ይህን ዐይን ያወጣ ጣልቃ ገብነት በገሀድ እያየ የዜጎችን ሰላምና ደህንነት ለማስጠበቅ ምንም ዓይነት እርምጃ ባለመውሰዱ ዋነኛው ተጠያቂ ያደርገዋል” በማለት የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ ገልጿል።