Get Mystery Box with random crypto!

አዋሽ ባንክ  ከሰሞኑ ፆመ ነነዌን አስመልክቶ ሲኖዶሱ ካስተላለፈው የአለባበስ ውሳኔ  ጋር በተያያዘ | 💚💛❤️ ዮቶራዊያን💚💛❤️

አዋሽ ባንክ  ከሰሞኑ ፆመ ነነዌን አስመልክቶ ሲኖዶሱ ካስተላለፈው የአለባበስ ውሳኔ  ጋር በተያያዘ የተሰጠኝ ስም ሀሰት ነው ብሏል

(እለታዊ የኢትዩትዩብ መረጃዎች)

በማህበራዊ የትስስር ገፁ ላይ እንዳሰፈረው ሰሞኑን ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሐይማኖት ጋር ተያይዞ በተፈጠረው ችግርና ቅዱስ ሲኖዶሱ በፆመ ነነዌ ለእምነቱ ተከታዮች ባስተላለፈው የፆምና ፀሎት ፕሮግራም ላይ ሊከተሉ ከሚገባው የአለባበስ ስርዓት ጋር ተያይዞ  በጥቂት ግለሰቦችና ቡድኖች የባንኩን ስም የማጠልሸት የተደረገው ጥረት ፍፁም ስህተት ነው ብሏል።

ባንኩ  ከማንኛውም ሐይማኖታዊና ፖለቲካዊ ጣልቃ ገብነት የፀዳ መሆኑን በመግለፅ  በባንኩ ውስጥ የሚሰራ ማንኛውም ሰራተኛ ከከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች እስከ ታችኛው የስራ መደብ ያሉት የራሳቸውን የግል አመለካከት፣ ሐይማኖታዊና ፖለቲካዊ አቋም ያላቸው እንደመሆኑ መጠን የማንንም መብት የማይነካና ጣልቃ የማይገባ መሆኑን ገልጿል።

በመሆኑም ሰሞኑን የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሐይማኖት ተከታይ ሰራተኞቹ ጥቁር ልብስ እንዳይለብሱ ከልክሏል፣ የለበሱትንም ከስራቸው አባሯል ተብሎ የተነዛው መሰረተ ቢስ ወሬ ከእውነት የራቀ፣ በፍፁም አዋሽን የማይመለከት መሆኑን ለክቡራን ደንበኞቻችንና ለመላው ህዝባችን በትህትና ማሳወቅ እንፈልጋለን፡፡

ስለዚህ በእነዚህ ጥቂት ግለሰቦች ለወዲፊቱም ተመሳሳይ አሉባልታዎች ቢነዙም አዋሽን የማይመለከት መሆኑን እየገለፅን የባንኩን ስም በማጠልሸት ተግባር ላይ የተሳተፉትን በህግ የሚጠይቅ መሆኑንም አሳውቋል።