Get Mystery Box with random crypto!

ኢትዮጵያ ፈላጭ ቆራጭ የመንግሥት አገዛዝ ካላቸው አገራት መካከል አንዷ ሆነች ከዓለም ሕዝብ መካ | 💚💛❤️ ዮቶራዊያን💚💛❤️

ኢትዮጵያ ፈላጭ ቆራጭ የመንግሥት አገዛዝ ካላቸው አገራት መካከል አንዷ ሆነች

ከዓለም ሕዝብ መካከል 8 በመቶ ያክሉ ብቻ በ“ሙሉ ዲሞክራሲ” ሥርዓት ውስጥ እንደሚኖሩ ተገልጿል

ረቡዕ ታሕሳሥ 1 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ) ከሰሞኑ ይፋ በሆነውና የዓለም አገራትን የዴሞክራሲን ሁኔታ በሚለካው የፈረንጆቹ 2022 ዓመት የዲሞክራሲ ኢንዴክስ፤ ኢትዮጵያን ፈላጭ ቆራጭ የመንግሥት አገዛዝ ካላቸው አገራት መካከል አንዷ አድርጓታል፡፡

“ኢኮኖሚስት ኢንተለጀንስ” የተሰኘው ተቋም ይፋ ያደረገው የአገራት ዓመታዊ የዲሞክራሲ ኢንዴክስ ጥናት፤ ኢትዮጵያ ባለፈው የፈረንጆቹ 2022 በፈላጭ ቆራጭ የመንግሥት አስተዳደር ውስጥ ማለፏን አመላክቷል፡፡

የዲሞክራሲ ኢንዴክስ ጥናቱ የ167 የዓለም አገራትን የዲሞክራሲ ዕድገት ደረጃ መሰረት አድርጎ ዓመታዊ ሁኔታን እየገመገመ ይመድባል፡፡

ምደባው የሚካሄደው ዴሞክራሲን ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ የሚያድርጉ፣ በከፊል ተግራዊ የሚያደርጉ፣ ከዲሞክራሲም ከፈላጭ ቆራጭም የሚቀላቅሉ እና ፈላጭ ቆራጭ አስተዳደር የተከተሉ ብሎ ይመድባቸዋል፡፡

የዴሞክራሲ ኢንዴክሱ የተጠናቀረው ከ60 መስፈርቶችን ግምት ውስጥ በማስገባት ሲሆን፤ ምዘናው በአምስት ዋና ዋና ምድቦች ይከናወናል፡፡ የዜጎች ነፃነት፣ ምርጫና ብዝሃነት፣ የሕዝብ የፖለቲካ ተሳትፎ፣ የመንግሥት እንቅስቃሴ እና የፖለቲካ ባህል ዋና ጠቋሚዎች ናቸው፡፡

በጥናቱ መሰረት ከመላው የዓለም ሕዝብ መካከል 8 በመቶ ያክሉ ብቻ በ“ሙሉ ዲሞክራሲ” ሥርዓት ውስጥ ይኖራሉ ተብሏል፡፡ ቀሪው የዓለም ሕዝብ ከለዘብተኛ ዲሞክራሲ እስከ ፈላጭ ቆራጭ አገዛዝ ባሉት የአገዛዝ ስርዐቶች ውስጥ የሚኖር ነው፡፡

የአገራት ዴሞክራሲ መረጃ ጠቋሚው ጥናቱ እንደ ፈረንጆቹ 2007 ለመጀመሪያ ጊዜ የተጠናቀረ ሲሆን፣ ከ2010 ጀምሮ ዓመታዊ ሆኗል።