Get Mystery Box with random crypto!

ለ12ኛ ክፍል ተፈታኞች በሙሉ!! 'የ2014 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች ቅሬታ ማቅረቢ | 💚💛❤️ ዮቶራዊያን💚💛❤️

ለ12ኛ ክፍል ተፈታኞች በሙሉ!!

"የ2014 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች ቅሬታ ማቅረቢያ ጊዜ ነገ አርብ ጥር 26/2015 ዓ.ም ከቀኑ 11፡30 ሰዓት የሚያበቃ መሆኑን አውቃችሁ በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ውስጥ እንዲታቀርቡ እናሳውቃለን፡፡

ቀድማችሁ ቅሬታ ያቀረባችሁ ተፈታኞች የቅሬታችሁን መልስ www.neaea.gov.et:8081 ድረ ገጽ ላይ የመለያ ቁጥራችሁን (Registration Number/ID) ብቻ በማስገባት ከዛሬ 12፡00 ሰዓት ጀምሮ ማየት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

ማሳሰቢያ
• ቅሬታዎች ሁሉም ተጣርተው ሲጠናቀቁ በቀጣይ ቀናት የሚናሳውቅ በመሆኑ የቅሬታችሁ ምላሽ ያልደረሳችሁ ተፈታኞች በትዕግስት እንዲትጠብቁ እናሳስባለን፡፡
• ባልተሟላ ወይም በተሳሳተ ወይም በሌላ ሰው መለያ ቁጥር ያመለከታችሁ የስም ዝርዝራችሁን ዛሬ ከምሽቱ 4፡00 ሰዓት ጀምሮ ከላይ በተጠቀሰው ድረ ገጽ አድራሻ ላይ የምናሳውቅ ሲሆን ቅሬታችሁን በድጋሚ በተስተካከለ መለያ ቁጥራችሁ ማመልከት ትችላላችሁ፡፡"

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት