Get Mystery Box with random crypto!

' በማህበራዊ ሚዲያ የተገለፀው ግነት የበዛበት ነው ' የዋቻሞ ዩኒቨርሲቲ ዩኒቨርሲቲው በወቅታዊ | 💚💛❤️ ዮቶራዊያን💚💛❤️

" በማህበራዊ ሚዲያ የተገለፀው ግነት የበዛበት ነው " የዋቻሞ ዩኒቨርሲቲ

ዩኒቨርሲቲው በወቅታዊ ጉዳይ ላይ መግለጫ አውጥቷል።

በመግለጫው ፤ ከዩኒቨሲቲው እውቅና ውጪ ባልተፈቀደ ሁኔታ በቀን 03/10/2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 3:00 ጀምሮ በሀገር አቀፍ ደረጃ በሁሉም ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚሰጠውን የ2015 ዓ.ም ተመራቂ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና (Exit Exam) " አንፈተንም  "በሚል  በዋናው ግቢ በዉስን ተማሪዎች ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ተሞክሮ ነበር ብሏል።

የተደረገውን ሙከራ ተከትሎ በጥቂት የማህበራዊ ሚዲያዎች የፀጥታ ችግር እንዳለና መደበኛ የመማር ማስተማር ሥራ ላይ መስተጓጎል እንዳለ በማስመሰል ሀሰተኛ መረጃዎች እየተሰራጨ  እንዳለ ለመገንዘብ ችለናል ብሏል።

በማህበራዊ ሚዲያዎች የሚሰራጨው ዜና ግነት የበዛበት " ነው ያለው ዩኒቨርሲቲው " የተፈጠረውን መጠነኛ ያለመግባባት ለመፍታት የዩኒቨርሲቲው ደህንነት ከፌዴራል ፖሊስ፣ ከሀዲያ ዞን ፖሊስ፣ ከሌሞ ወረዳ ፖሊስ እንዲሁም ከሌሎች ከሚመለከታቸው የፀጥታ ኃይሎች ጋር በቅንጅት በመስራት በአስተማማኝ ሁኔታ ሠላማዊ የሆነ የመማር ማስተማር ሥራ ማስቀጠል ተችሉዋል ብሏል።

ዩኒቨርሲቲው ፤ ለተማሪዎች እና የተማሪ ወላጆች ባስተላለፈው መልዕክት በነበረው መጠነኛ የተቃዉሞ እንቅስቃሴ በተማሪዎች ላይ " ምንም ዓይነት ጉዳት " ያለመድረሱንና ዩኒቨርሲቲው ወደተለመደው መደበኛ የመማር ማስተማር ሥራ መመለሱን አሳውቋል።

ተቋሙ ባወጣው መግለጫ ላይ በቪድዮ እና በፎቶ ስለተያዙት ማስረጃዎች ምንም ያለው ነገር የለም።