Get Mystery Box with random crypto!

61 ቦንቦችን ጨምሮ የተለያዩ መሳሪያዎችን ለሽብር ቡድኑ ሸኔ ሊያደርሱ በድብቅ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ | 💚💛❤️ ዮቶራዊያን💚💛❤️

61 ቦንቦችን ጨምሮ የተለያዩ መሳሪያዎችን ለሽብር ቡድኑ ሸኔ ሊያደርሱ በድብቅ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ተጠርጣሪዎች ተያዙ

መነሻዉን አዋሽ አድርጎ አዳማ በአንድ ግለሰብ ቤት በመደበቅ ለሸኔ ታጣቂ ቡድን ሊሄድ የነበረ 61 ቦምብ፣ 53 ፊዉዝ፣ 1 ላዉንቸር ከ2 ተተኳሽ ቁንቡላ ጋር እንዲሁም 9 የብሬን ዝናር፣ 20 የክላሽ ካርታ፣ 11 የስናይፐር ካርታ፣ 1 የመኪና ፈንጂ ፊዉዝ፣ 1 የብሬን ጥይት፣ 5 የብሬን ማመላለሻ፣ 2 የስናይፐር መነፅር፣ 1 የብሬን አናት፣ ከሽብር ቡድኑ ጋር መረጃ የሚለዋወጡበት አንድ ላፕቶፕ መያዘቸዉን ለመረጃዉ ቅርበት ያላቸዉ ታማኝ ምንጮች በፎቶ የተደገፈ መረጃ በመላክ አረጋግጠዋል።

የብሕራዊ መረጃና ደኀንነት አገልግሎት የዚህ ህገወጥ ድርጊት ተሳታፊ ሁለት አዘዋዋሪዎች ላይ ጥብቅ ክትትል ሲያደርግ ቆይቶ ለኦሮሚያ ክልል ፖሊስ ጥቆማ በመስጠት አዳማ ላይ በቁጥጥር ስር እንዲዉሉ ማድረጉን ምንጮች ተናግረዋል ፡፡