Get Mystery Box with random crypto!

Educate Ethiopia

የቴሌግራም ቻናል አርማ educate_ethiopia — Educate Ethiopia E
የቴሌግራም ቻናል አርማ educate_ethiopia — Educate Ethiopia
የሰርጥ አድራሻ: @educate_ethiopia
ምድቦች: እውነታው
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 25.70K
የሰርጥ መግለጫ

A channel dedicated to brighten Ethiopia through education .
We share study tips, tricks motivations and resources that will help your academic carrier.
For any questions @EducateEthiopiaBot
For any resources @EducateEthResources

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 7

2022-10-27 18:37:15
#ECSU

የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ የ2015 ትምህርት ዘመን የነባር እና አዲስ ገቢ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ፦

➤ ነባር የቅዳሜና እሁድ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ
     ➭ ጥቅምት 18 እና 19/2015 ዓ.ም

➤ ነባር የመደበኛ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ
     ➭ ጥቅምት 21/2015 ዓ.ም

➤ ነባር የማታ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ
     ➭ ጥቅምት 22/2015 ዓ.ም

➤ የነባር ተማሪዎች ትምህርት የሚጀምረው
     ➭ ጥቅምት 23/2015 ዓ.ም

(ተጨማሪ መረጃ ከላይ ይመልከቱ።)

Credit: tikvahUniversity

ለበለጠ ትምህርታዊ መረጃ @educate_ethiopia ቤተሰብ ይሁኑ
2.6K viewsedited  15:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-11 13:46:17
የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በትናንትናዉ እለት በሀዋሳ ዩኒቨርስቲ አደጋ የደረሰባቸዉን ተማሪዎች ጠየቁ
---------------------------------------------------------------------

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በትናንትናዉ ዕለት አደጋ የደረሰባቸዉን በሃዋሳ ዩኒቨርስቲ የሚፈተኑ የ2014 ዓም 12ኛ ክፍል ተፈታኞች ደህንነት ለመጠየቅ ዛሬ ጠዋት ሀዋሳ ሪፌራል ሆስፒታል ተገኝተዋል፡፡

“አሁን ዋናዉ የእናንተ ማገገም ነዉ፡፡ ለፈተናዉ አትጨነቁ” በማለትም የተጎዱ ተማሪዎች በጤንነታቸዉ ዙሪያ እንዲያተኩሩ መክረዋል፡፡

በትናንትናዉ እለት ህይወቱ ላለፈዉ ተማሪም የተሰማቸዉን ከፍተኛ ሀዘን ገልጸዉ ለተማሪዉ ወላጆች እና ቤተሰቦች መጽናናትን ተመኝተዋል፡፡

በደረሰዉ ጉዳት እንደአገር እናዝናለን፡፡ ነገር ግን ሂደቱ የፈተና ስርዓቱ ከስርቆት ተጠብቆ ተማሪዎች በራሳቸዉ ጥረት ዉጤታማ እንዲሆኑ እና የተሻለች አገር የመገንባት በመሆኑ በዚህ ተስፋ መቁረጥ የለብንም ብለዋል፡፡ ወላጆችም ይህንን ተረድተዉ ከትምህርት ማህበረሰቡ ጋር በጋራ እንዲቆሙ ጠይቀዋል፡፡

የተከሰተዉ የድልድይ መደርመስ አደጋ ወደ ከፋ ደረጃ እንዳይሸጋገር ተማሪዎቹን ለማዳን ለተረባረቡ የጤና ተቋማት ፣ የሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ማህበረሰብ እና የአካባቢዉ ነዋሪዎች ምስጋና አቅርበዋል፡፡

በሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ትናንት በደረሰዉ አደጋ ምክንያት ተቋርጦ የነበረዉ ፈተና ዛሬ የተጀመረ ሲሆን ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ የፈተና አሰጣጡንም ጎብኚተዋል፡፡

ትምህርት ሚኒስቴር !
1.5K views10:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-10 11:37:22
ከ560 ሺህ በላይ ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና በመውሰድ ላይ ናቸው - ትምህርት ሚኒስቴር

በ130 ማዕከላት ከ560 ሺህ በላይ ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና በተረጋጋና በሰላም እየወሰዱ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር ገለጸ።

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እንዲሁም ሚኒስትር ዴኤታዎች የፈተናውን አጀማመርና አጠቃላይ ሂደት በሚመለከት መግለጫ ሰጥተዋል።

በዚህም በ130 ማዕከላት ከ560 ሺህ በላይ ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና በተረጋጋና በሰላም እየወሰዱ መሆኑን አብራርተዋል።

በሐዋሳ ዩኒቨርስቲ በዋናው ግቢ የሚገኝ ድልድይ ተደርምሶ በተወሰኑ ተማሪዎች ላይ አደጋ መድረሱንም ሚኒስትሩ ጠቁመዋል።

በአደጋው ጉዳት ለደረሰባቸው ተማሪዎች ሃዘናቸውን ገልጸው፤ በአደጋው ጉዳት ያጋጠማቸው ተማሪዎች ህክምና እየተደረገላቸው መሆኑን አስታውቀዋል።

በአደጋው ጉዳት የገጠማቸው ተማሪዎች ካገገሙ በኋላ ፈተናውን እንዲወስዱ ይደረጋል ብለዋል።

ከተጠቀሱት አካባቢዎች በስተቀር በሌሎች ትምህርት ቤቶች ግን ፈተናው በሰላምና በተረጋጋ መልኩ እየተሰጠ መሆኑን ሚኒስትሩ ገልጸዋል።

ምንጭ - ኢዜአ
1.5K views08:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-10 11:27:27
የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች መሰጠት ተጀመረ


የተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ማስፈተን ጀምረዋል።

በመደወላቡ፣ በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ፣ በጂማ፣ በኦዳ ቡልቱም እና ነቀምቴ ዩኒቨርሲቲዎች ተገኝተው እንደተመለከቱት ፈተናው ተጀምሯል።

ምልከታ ከተደረገበት መካከል አንዱ የመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ሲሆን ከ11 ሺህ የሚበልጡ ተማሪዎች መፈተን ጀምረዋል።

ለፈተና የሚያስፈልጉ ቅድመ ሁኔታዎችን ቀድመው መጠናቀቃቸውን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶ/ር አህመድ ከሊል ለኢዜአ ተናግረዋል።

ተፈታኞችን ለፈተና የሚያዘጋጁ አጠቃላይ ገለጻ እንደተደረገላቸውም ጠቅሰዋል።

ተማሪዎች የፈተና ሕጉን በመጠበቅ ተረጋግተው እንዲፈተኑም መክረዋል።

በዩኒቨርሲቲው የተመደቡ ተፈታኞች በበኩላቸው፣ በራሳችን ጥረት የተሻለ ነጥብ ለማስመዝገብ ተዘጋጅተናል ብለዋል።

አዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲም በተመሳሳይ ከ10 ሺህ በላይ ተማሪዎች ፈተና መውሰድ ጀምረዋል።

የጂማ ዩኒቨርሲቲም በሁሉም ካምፓሶቹ 25 ሺህ ተማሪዎችን ማስፈተን ጀምሯል።

የኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ ከ9 ሺህ በላይ ተመሪዎችን ማስፈተን ጀምሯል።

ምንጭ - ኢቢሲ
1.4K views08:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-10 07:42:28
ኤዱኬት ኢትዮጵያ በመላ ሀገራችን ዛሬ የሚጀምረውን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ መልቀቂያ ፈተና ለምትወስዱ ተማሪዎች መልካም ዕድል ትመኛለች።

ፈጣሪ ከናንተ ጋር ይሁን
1.6K viewsedited  04:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-09 10:18:20
የጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ አህመድ(ዶ/ር) መልዕክት ለ12ኛ ክፍል ተፈታኞች

የሀገራችን የነገ ተስፋዎች ሆይ

ኢትዮጵያ እናንተን ስታይ ተስፋ ነው የሚታያት። ይህ የምትፈተኑት የ12ኛ ክፍል ፈተና ለኢትዮጵያ እውነተኛ ተስፋዎች መሆናችሁን የምታረጋግጡበት እንደሚሆን አምናለሁ። እናንተን እዚህ ለማድረስ ወላጆች፣ መምህራን እና መላው ማኅበረሰብ ለዓመታት ለፍቷል። ውጤቱን የምታሳዩት ከኩረጃና ከስርቆት ነጻ ሆናችሁ፣ በራሳችሁ ተማምናችሁ፣ ፈተናውን ስትፈተኑ ነው።

የተሰጣችሁን መመሪያ አክብሩ፤ ተረጋግታችሁ ፈተናችሁን ሥሩ፤ በምንም አትሸበሩ፤ የኢትዮጵያ አምላክ ዕውቀቱን ይግለጥላችሁ።
2.5K views07:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-08 21:15:13
የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ከ12ኛ ክፍል ተፈታኞች ጋር እራት በሉ።

ፕሮፌሰሩ ቀን በነበራቸው የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ቆይታ ተማሪዎቹ የተሳፈሩባቸው ባሶች በመግባት ጭምር የጎበኙ ሲሆን በእራት ሰዓት በነበራቸው ቆይታ " የጉዟቸውን ሁኔታ ማየት፣ የሚበሉትን በልተን ደህንነታቸውን ማረጋገጥ ስለሚገባን ያንን እያደረግን ነው። ወላጆች የልጆቻቸው ደህንነት ሳያሳስባቸው በሙሉ ልባቸው እንዲተማመኑብን እንፈልጋለን" ብለዋል።

ሚኒስትሩ ከተማሪዎች ጋር በነበራቸው ቆይታ ተማሪዎችን አበረታተዋል። የህይወት ልምዳቸውንም አጋርተዋል።

ትምህርት ሚኒስቴር !
490 views18:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-08 20:43:32
የዚህ admission card ባለቤት ካርዱን ባስ ውስጥ ወድቆ ስለተገኝ በዚ ስልክ ደውላ ማግኝት ስለምትችል 0910222366 ይህን የተመለከታችሁ አካላት ተባበሩ።

Credit: tikvah

ለበለጠ ትምህርታዊ መረጃ @educate_ethiopia ቤተሰብ ይሁኑ
754 viewsedited  17:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-08 20:40:23
#ማሳሳቢያ፡-

ተፈታኞቻችን ወደ መፈተኛ ማዕከላት ገብተዋል፡፡ የተከለከሉ ነገሮችን ማንም ተፈታኝ ይዞ እንዳይገባ ከወረዳ ጀምሮ ገለጻ ተደርጓል፡፡ በተጨማሪም አካላዊ ፍተሻ ተደረጓል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ የተለያየ የማጭበርበሪያ ዘዴዎችን በመጠቀም የተከለከሉ ነገሮችን በተለይም ተንቀሳቃሽ ስልክን ዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ ይዘው የተገኙ ተፈታኞች በህግ ቁጥጥር ስር ይገኛሉ፡፡ ድርጊቱ ከፍተኛ የፈተና ደንብ ጥሰት በመሆኑ ውሳኔው ከሁሉም ፈተና የሚሰረዙ ይሆናል፡፡

በተመሳሳይ ከዚህ በኃላም የተከለከሉ ነገሮችን መፈተኛ ማዕከላት (የኒቨርሲቲ) ግቢ ውስጥ ማንኛውም ተፈታኝ ይዞ ቢገኝ ከሁሉም ፈተና የሚሰረዝ መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ ገለጻውን ባለመቀበልና አካላዊ ፍተሻዎችን በማጭበርበር ስለፈጸመው ጉዳይ ተጨማሪ ህጋዊ ምርመራ የሚካሄድ ሲሆን እንደግኝቱም ተመጣጣኝ ህጋዊ እርምጃ የሚወሰድ ይሆናል፡፡

ፈተና የሁሉም ማህበረሰብ ሀብት በመሆኑ ሁሉም ዜጋ ለፈተና ደህንነትና ፍትኃዊነት የበኩሉን አዎንታዊ ድርሻ እንዲወጣ ጥሪ እናቀርባለን፡፡

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት

ለበለጠ ትምህርታዊ መረጃ @educate_ethiopia ቤተሰብ ይሁኑ
798 views17:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-08 09:46:53 አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎችን መቀበል ጀምሯል።

ዩኒቨርሲቲው በዘጠኝ ካምፓሶቹ ከ38 ሺህ በላይ የ12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎችን እንደሚቀበል ተገልጿል።

ለበለጠ ትምህርታዊ መረጃ @educate_ethiopia ቤተሰብ ይሁኑ

Credit: tikvah
1.7K viewsedited  06:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ