Get Mystery Box with random crypto!

Educate Ethiopia

የቴሌግራም ቻናል አርማ educate_ethiopia — Educate Ethiopia E
የቴሌግራም ቻናል አርማ educate_ethiopia — Educate Ethiopia
የሰርጥ አድራሻ: @educate_ethiopia
ምድቦች: እውነታው
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 25.70K
የሰርጥ መግለጫ

A channel dedicated to brighten Ethiopia through education .
We share study tips, tricks motivations and resources that will help your academic carrier.
For any questions @EducateEthiopiaBot
For any resources @EducateEthResources

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 10

2022-09-28 15:38:22
ሰመራ ዩኒቨርሲቲ በተያዘው ወር መጨረሻ ለሚሰጠው የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ገልጿል።

ዩኒቨርሲቲው ከ8 ሺህ 100 በላይ የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች በትምህርት ሚኒስቴር ተመድበውለታል።

ከዩኒቨርሲቲው እና ከክልሉ ትምህርት ቢሮ የተውጣጣ ግብረ ኃይል ለፈተናው እየተደረገ ያለውን ዝግጅት ግምግሟል።

ዩኒቨርሲቲው ለተፈታኞች የመፈተኛ ክፍል፣ የምግብ እና የመኝታ ክፍል አገልግሎቶች ዝግጅት እያከናወነ እንደሚገኝ ተመላክቷል።

ፈተናውን ለመስጠት የቀረው ጊዜ አጭር በመሆኑ እየተደረገ ያለውን ዝግጅት በፍጥነት ማጠናቀቅ እንደሚገባ የዩኒቨርሲቲው አካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዝዳንት አብዱረህማን ከድር (ዶ/ር) ገልጸዋል።

ለበለጠ ትምህርታዊ መረጃ @educate_ethiopia ቤተሰብ ይሁኑ

Credit: tikvah
739 viewsedited  12:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-26 18:17:36
በአዲስ አበባ 49 ሺህ 203 ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተናን ይወስዳሉ።

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተናው የሚሰጥባቸው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት፦

• አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ
• ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ
• የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ
• አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ
• የፌደራል ቴክኒክና ስልጠና ኢንስቲትዩት

ተፈታኝ ተማሪዎች በፈተና ወቅት የምግብ እና የመኝታ አገልግሎቶችን በየተቋማቱ እንደሚያገኙ ተገልጿል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በብሔራዊ ፈተናው ቅድመ ዝግጅት ላይ ፈተናውን ለማስፈፀም ከተቋቋመው ኮማንድ ፖስት ጋር ውይይት አድርጓል፡፡

ለበለጠ ትምህርታዊ መረጃ @educate_ethiopia ቤተሰብ ይሁኑ

Credit: tikvah
823 viewsedited  15:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-26 16:19:05 የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የፈተና ዝግጅት እና አስተዳደር ዳይሬክተር አቶ ዲናኦል ጫላ የተፈታኞችን መብትና ግዴታዎች እንዲሁም ለተፈታኞች የተፈቀዱ እና የተከለከሉ ነገሮች ያቀረቡ ሲሆን በዚህም

የተፈታኞች መብቶች የሆኑት፡-

ከፈተና ጥያቄ ውጪ ማንኛውንም ያልተረዳውን ነገር ጠይቆ የመረዳት መብት

በየኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ ምግብ፣ የህክምና አገልግሎት፣ የማደሪያ ክፍል፣ ፍራሽና ትራስ የማግኘት መብት

ማንኛውም ተፈታኝ በዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ ያለውን የቤተ መጽሐፍት፣ የመጸዳጃ ቤቶች፣ የሻወር፣ የካፍቴሪያዎች፣ የሚኒ ሱፐር ማርኬቶች፣ የተለያዩ ሱቆች፣ የመናፈሻና መዝናኛ

አገልግሎቶችን የመጠቀም መብት

የኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ የጋራ የደህንነት ጥበቃ የማግኘት መብት
. በፈተና ሰዓት መፈተኛ ክፍል ገብቶ ብርሃናማ የመፈተኛ ቦታ፣ ወንበር፣ መጻፊያ ጠረጴዛ የማግኘት መብት

ፈተና ከመጀመሩ አንድ ቀን ቀድሞ ስለፈተናው ገለጻ (ኦሬንቴሽን) የማግኘት መብት
የተፈታኞች ግዴታ የሆኑት፡-
. ማንኛውም ተፈታኝ በፈተና ማዕከልም ይሁን መፈተኛ ክፍል አድሚሽን ካርድ ይዞ የመገኘት ግዴታ

ማንኛውም ተፈታኝ ወደ ዩኒቨርሲቲ ሲመጣ የትምህርት ቤት ወይም የነዋሪነት መታወቂያ ይዞ መገኘት

ማንኛውም ተፈታኝ ወደ ግቢ ከመግባቱ በፊትና ወደ መፈተኛ ክፍል ከመግባቱ በፊት ሙሉ አካላዊ ፍተሻ የመፈተሽ ግዴታ

ማንኛውም ተፈታኝ በዩኒቨርሲቲ ግቢና በመፈተኛ ክፍል የተከለከሉ ቁሳቁሶችን/ዕቃዎችን መያዝ የለበትም

ማንኛውም ተፈታኝ እርሳስ፣ ላጲስና የእርሳስ መቅረጫ ይዞ መገኘት

ማንኛውም ተፈታኝ የፈተና ደንብን የማክበር ግዴታ

ማንኛውም ተፈታኝ በፈተና ማዕከል ውስጥና በመፈተኛ ክፍል ውስጥ የፈተና አስፈጻሚዎች የፈተና አስተዳደር ሥራን ውጤታማ ለማድረግና ሁኔታዎችን ለማመቻቸት የሚያደርጉትን ጥረት የመተባበር ግዴታ አለበት

ማንኛውም ተፈታኝ ፈተና ከመጀመሩ በፊት መፈተኛ ክፍል የመገኘት ግዴታ አለበት

ተፈታኙ ፈተናው ሳይጠናቀቅ ከፈተና ክፍል የሚወጣ ከሆነ የፈተና ጥያቄ የያዘውን ቡኩሌት ለፈታኙ የማሰረከብ ግዴታ አለበት

ማንኛውም ተፈታኝ ወደ ተመደበበት ዩኒቨርሲቲ ሲመጣ አንሶላ፣ ብርድልብስና የትራስ ጨርቅ ይዞ የመምጣት ግዴታ አለበት

ዩኒፎርም ለብሶ መገኘት አለበት


ለተፈታኞች የተፈቀዱ ነገሮች

አዲስ ወይም ቀድሞ ለመማርና ለማጥናት ሲጠቀሙበት የነበሩ ማስተወሻ ደብተር ፣ የትምህርት መጽሐፍ፣ መንፈሳዊ/ኃይማኖታዊ መጽሐፍት፣ ባዶ ወረቀት

ደረቅ ምግቦች ወይም ሰንዱች ምግቦች (ጩኮ፣ በሶ፣ ዳቦ ቆሎ፣ ቆሎ….)
ገንዘብ (ብር)

የልብስ ወይም የእጅ ቦርሳ፣ የግል ልብስ፣ ጫማ

የግል ንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁስ (ሳሙና፣ ሞዴስ፣ የጥርስ ብሩሽ፣ የጥርስ ሳሙና፣ የገላ ማድረቂያ ፎጣ፣ ሶፍት፣ ሻምፖ፣ ኮንዲሽነር፣ ሎሽን፣ ቻፕስቲክ፣ የጸጉር ቅባት፣ የፊት ቅባት)
ለተፈታኞች የተከለከሉ ነገሮች

ማንኛውንም ዓይነት የጦር መሣሪያ ይዞ መገኘት የተከለከለ ነው፡፡

ማንኛውንም ዓይነት ስለት እና ሹልነት ያላቸውን ብረታ ብረቶችና ጠንካራ ፕላስትኮች ይዞ መገኘት የተከለከለ ነው

ማንኛውም ድምጽ የሚቀዳ፣ ፎቶ የሚያነሳ፣ ቪዲዮ የሚቀርጽ፣ ከቴሌ መስመርም ሆነ ከቴሌ መስመር ውጭ መልዕክት በዲጂታል መንገድ የሚሰጥ ወይም የሚቀበል የግል ዕቃ/መሳሪያ /ቴክኖሎጂ ውጤት፣ ስልክ፣ አይ-ፓድ፣ ታብሌት፣ ኮምፕዩተር፣ ላፕቶፕ፣ ስማርት ሰዓት፣ ማጂክ ብዕር/እስክሪብቶ፣ ማጂክ ኮት/ጃኬት እና ሌሎች ማንኛቸውም ፎቶ፣ ምስል እና ድምጽ የሚቀርጹ የኤሌክትሮኖክስ መሣሪያዎችን በዩኒቨርሲቲው ግቢ ውስጥም ሆነ ግቢ ዙሪያ ይዞ መገኘት ወይም መጠቀም የተከለከለ ነው፡፡

በዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ ማንኛውንም ዓይነት የግል ፍላሽ ዲስክ፣ ሃርድ ዲስክ፣ ሲዲ፣ ሚሞሪ፣ ሚሞሪ ሪደር፣ ኦ-ቲጂ ኮንቨርተርና መሰል ዕቃዎችን ይዞ መገኘት ወይም መጠቀም የተከለከለ ነው፡፡

ማንኛውም አደንዛዥ እጾች (ጫት፣ ሲጋራ፣ በሓኪም ማዘዣ የሌለው መድኃኒት (በሽሮፕም ይሁን በታብሌት፣ ህክምና መስጫ መርፌ)) መያዝ ወይም መጠቀም የተከለከለ ነው፡፡

ማንኛውም ዓይነት የአልኮል መጠጥ ይዞ
መገኘት ወይም መጠቀም የተከለከለ ነው፡፡

ማንኛውም ዓይነት የአንገት ሐብል፣ የጸጉር ጌጥ፣ የጆሮ ጌጥ፣ የጣት ቀለበት፣ የእጅ አንባር፣ አድርጎ ወይም ይዞ መገኘት የተከለከለ ነው፡፡ (ከልሙጥ የጋብቻ ቀለበት በስተቀረ)

ፈተና ከተጀመረ ከ30 ደቂቃ በኋላ ወደ ፈተና ክፍል መግባት እና ፈተናው ተጀምሮ 45 ደቂቃ ሳይሞላ ከፈተና ክፍል መውጣት የተከለከለ ነው፡፡

ተፈታኙ ፈተናው ሳይጠናቀቅ ከፈተና ክፍል የሚወጣ ከሆነ የፈተና ጥያቄ የያዘውን ቡኩሌት ይዞ መውጣት ተከለከለ ነው፡፡

በፈተና ሰዓት በመፈተኛ ክፍል ውስጥ ማስቲካ መያዝም ሆነ መጠቀም የተከለከለ ነው፡፡

በዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ በግልም ሆነ በቡድን መጮህ ወይም በጣም ከፍተኛ ድምጽ ማሰማት የተከለከለ ነው፡፡
የሚሉት ተጠቃሽ ናቸዉ፡፡

በአዲስ አበባ 49,203 ተማሪዎች ፈተናውን ለመውሰድ መመዝገባቸውንና ፈተናውም ከመስከረም 30 ጀምሮ በቅድሚያ የሶሻል ሳይንስ ተማሪዎች ተፈትነው ሲጨርሱ የናቹራል ሳይንስ ተማሪዎች ቀጥለው እንደሚፈተኑ የተገለጸ ሲሆን ተፈታኝ ተማሪዎች በፈተና ወቅት የምግብና የመኝታ አገልግሎቶችን በየተቋማቱ እንደሚያገኙም ተጠቁማል፡፡

ለበለጠ ትምህርታዊ መረጃ @educate_ethiopia ቤተሰብ ይሁኑ

ምንጭ፡ የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ
1.1K viewsedited  13:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-23 12:11:28
ከመፈተኛ ዩኒቨርሲቲ ከ50 ኪሎ ሜትር በላይ ለሆኑ የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች የትራንስፖርት ወጪን ትምህርት ቤቶቻቸው የሚገኙባቸው ወረዳዎች እንደሚሸፍኑ የሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አስታውቋል።

ከመስከረም 30 እስከ ጥቅምት 17 ቀን 2015 ዓ.ም በሁለት ዙር ለሚሰጠው የ12ኛ ክፍል ፈተና በቂ ቅድመ ዝግጅት መደረጉን አገልግሎቱ ገልጿል።

የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር እሸቱ ከበደ ለ ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት (ኤፍ ቢ ሲ) የሰጡት ቃል ፦

- ፈተና ማተም ጨምሮ ሌሎች አስፈላጊ ዝግጅቶች ከወዲሁ ተጠናቀዋል።

- ከመፈተኛ ዩኒቨርሲቲዎች በ50 ኪሎሜትር ርቀት ውስጥ ያሉ ተፈታኝ ተማሪዎች የትራንስፖርት ወጪን በራሳቸው ይሸፍናሉ፤ ከ50 ኪሎ ሜትር ርቀት #በላይ የሚገኙ ተማሪዎች ደግሞ ትምህርት ቤቶቻቸው የሚገኙባቸው ወረዳዎች ወጪያቸውን ይሸፍናሉ።

- ተፈታኝ ተማሪዎች መያዝ #የሚፈቀዱላቸው ፦

• መጽሐፍት፣
• ሲያጠኗቸው የነበሩ ማስታወሻወች፣
• የንጽህና መጠበቂያዎች
• የሌሊት ልብስ ከተፈቀዱት ቁሳቁስ መካከል ናቸው።

ተማሪዎች ማንነታቸውን የሚገልጽ የቀበሌ መታወቂያ ፣ የመፈተኛ ካርድ ወይም አድሚሽን ካርድ መያዝ ይኖርባቸዋል።

- ተፈታኝ ተማሪዎች መያዝ #የሚከለከሏቸው ቁሳቁስ፦

• ማንኛውንም የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣
• ከጋብቻ ቀለበት ውጪ የተለየ ፈርጥ ያላቸው ቀለበቶች፣
• ሀብሎች ፣
• የጸጉር ጌጦች
• ድምጽ የሚያወጡ ጃኬቶች መያዝ አይቻልም።

- የመፈተኛ ዩኒቨርሲቲዎች ለተፈታኝ ተማሪዎች የመኝታና የምግብ አገልግሎት ያመቻቻሉ።

ለበለጠ ትምህርታዊ መረጃ @educate_ethiopia ቤተሰብ ይሁኑ

Credit: tikvah
2.0K viewsedited  09:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-22 16:03:17
የዩኒቨርሲቲ መግቢያ እና የሁለተኛ ደረጃ ማጠናቀቂያ ፈተና ተፈታኞች ለፈተና ወደ ተመደቡበት ካምፖስ ጉዞ ሲያደርጉ መያዝ የተፈቀደላቸው፣ መያዝ የተከለከሉ እና የጊዜ ሰሌዳ እንደሚከተለው ሀመሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።

መያዝ የተፈቀደው፦

• አንሶላ፣ ትራስ ጨርቅ፣ የማታ ልብስ፣ ደረቅ ምግብ፣ ልብስ፣ ቦርሳ፣ የመፈተኛ ካርድ፣ እርሳስ፣ ላጲስ፣ የማስታወሻ ደብተር፣ ባዶ ወረቀት፣ መፅሐፍ

መያዝ የተከለከሉ፦

• ማንኛውም ድምፅ የሚቀዳ፣ ቪዲዮ የሚቀዳ ወይም ፎቶግራፍ የሚያነሳ መሳሪያ፣ ካሜራ
• ማንኛውም ከቴሌ መስመርም ይሁን ከቴሌ ውጭ መልዕክት በዲጂታል ቴክኖሎጂ መቀበያ ወይም ማስተላለፊያ ውጤቶች (ታብሌት፣ ኮሚፕዩተር፣ ላፕቶፕ፣ ስልክ፣ አይፓድ፣ ሃርድ ዲስክ፣ ፍላሽ)

የጊዜ ሠሌዳ፦

• ማህበራዊ ሳይንስ
➤ 26 እስከ 28/01/2015 ዩኒቨርሲቲ መግቢያ
➤ 29/01/2015 ኦሬንቴሽን
➤ 30/01/2015 እስከ 02/02/2015 ፈተናው የሚሰጥበት ጊዜ

• የተፈጥሮ ሳይንስ
➤ 05 እስከ 06/02/2015 ዩኒቨርሲቲ መግቢያ
➤ 07/02/2015 ኦሬንቴሽን
➤ 08/02/2015 እስከ 11/02/2015 ፈተናው የሚሰጥበት ጊዜ

ለበለጠ ትምህርታዊ መረጃ @educate_ethiopia ቤተሰብ ይሁኑ

Credit: tikvah
3.0K viewsedited  13:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-20 06:57:01 በአዲሱ ሴሚስተር አሪፍ ውጤት ለማምጣት አንዱ ማድረግ ያለባችሁ ነገር ለስኬት የሚያበቃ እቅድ ማውጣት ነው። ይህን እንዴት ማድረግ እንደሚቻል ለማወቅ ከታች ያለውን ቪዲዮ ተመልከቱ።

@educate_ethiopia







3.9K views03:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-19 15:54:51
የ2015 የትምህርት ዘመን ተጀምሯል።

የ2015 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በዛሬው ዕለት መጀመሩን የትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል።

በተመሳሳይ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2015 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ተካሂዷል።

የዘንድሮው የትምህርት ዘመን በአዲስ አበባ ከተማ በአዲስ ስርዓተ ትምህርት ትግበራ መጀመሩ ተገልጿል።


ለበለጠ ትምህርታዊ መረጃ @educate_ethiopia ቤተሰብ ይሁኑ
4.3K viewsedited  12:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-16 18:05:37 #አስቸኳይ_መልዕክት

በአማራ ክልል በቅርቡ ለሚሰጠው የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ተፈታኝ ተማሪዎች የተላለፈ አስቸኳይ መልዕክት፡፡

የ2014/2015 ዓ.ም በአማራ ክልል የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ተፈታኝ ተማሪዎች ከመስከረም 30/2015 ዓ.ም ጀምሮ በክልሉ ባሉ ዩኒቨርስቲዎች ፈተናው እንደሚሰጥ መገለፁ ይታወሳል፡፡

በመሆኑም ተፈታኝ ተማሪዎች ቀድመው ሊዘጋጁባቸው  የሚገቡ ዋና ዋና ነጥቦች እንደሚከተለው ይቀርባሉ፡፡

1. ሁሉም ተፈታኝ ተማሪዎች በፈተና ማዕከልም ይሁን በመፈተኛ ክፍል አድሚሽን ካርድ ይዞ መገኘት ግዴታ በመሆኑ አድሚሽን ካርድ ፎርም ከሞሉበት  ትምህርት ቤት እና ወረዳ በአካል በመገኘት እስከ መስከረም 10/2015 ዓ.ም እንዲረከቡ፡፡

2. በአድሚሽን ካርዱ ላይ የስም፣ የስትሪም እና የጾታ ወዘተ..ስህተት ካለ በአስቸኳይ ለትምህርት ቤቱ እና ለወረዳው ሪፖርት እንድታደርጉ በጥብቅ እያሳሰብን ይህንን የማያደርጉ ተማሪዎች ካሉ ፈተና ለመውሰድ እንደሚቸገሩ፤

3. ሁሉም ተፈታኝ ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲ ሲመጡ የትምህርት ቤት ወይም የኗሪነት መታወቂያ ይዞ መገኘት የሚገባ መሆኑ፤

4. ሁሉም ተፈታኝ ተማሪዎች በፈተና ጊዜ እርሳስ፣ ላጲስና የእርሳስ መቅረጫ  ይዘው መገኘት ያለባቸው መሆኑ ከዚህ ዉጭ ሌሎች ቁሳቁሶችን በዩኒቨርሲቲ ግቢ እና በመፈተኛ ክፍል መያዝ የተከለከለ መሆኑ፤

5. ሁሉም ተፈታኝ ተማሪዎች ትምህርት ቤቱ፣ ወረዳው እና ዞኑ በሚያዘጋጀው የጉዞ ፕሮግራም መሰረት ወደ መፈተኛ ዩኒቨርሲቲ የሚጓዙ መሆኑን በመረዳት ዝግጅት ማድረግ ያለባቸው መሆኑን፤

6. ሁሉም ተፈታኝ ተማሪዎች ወደ ተመደበበት ዩኒቨርሲቲ ሲሄድ አንሶላ፣ ብርድልብስና የትራስ ልብስ ይዞ የመምጣት ይኖርባቸዋል፡፡

ይህን መረጃ ሸር በማድረግ ለተማሪዎችና ተማሪ ወላጆች እንዲሁም የሚመለከታቸው አካላት እንዲደርስ ትብብራችሁን እንድታደርጉ በተፈታኝ ተማሪዎች ስም ቢሮው ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡

የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ
ባህርዳር

ለበለጠ ትምህርታዊ መረጃ @educate_ethiopia ቤተሰብ ይሁኑ

Credit:tikvah
5.9K viewsedited  15:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-15 23:12:37
* ጥንቃቄ

የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና መቃረብን ተከትሎ የተለያዩ ሀሰተኛ መረጃዎች በስፋት እየተሰራጩ በመሆኑ ተማሪዎች እንዲሁም የተማሪ ወላጆች ጥንቃቄ ልታደርጉ ይገባል።

" የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ተሸጋገረ " እየተባለ በአንዳንድ የማህበራዊ ገፆች ላይ የሚሰራጨው መረጃ ምንጩ የማይታወቅ በትምህርት ሚኒስቴር ሆነ በሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ያልተገለፀ ነው።

ተማሪዎች ከፈተና ጋር በተያያዘ ማንኛውም አዲስ መረጃ ሲኖር በትምህርት ሚኒስቴር / በትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገፆች እንዲሁም በህዝብ መገናኛ ብዙሃን የሚገለፅ መሆኑን በማወቅ በሀሰተኛ መረጃ ሳትረበሹ ተረጋግታችሁ ዝግጅታችሁን ልታደርጉ ይገባል።

የተማሪ ወላጆችም ትክክለኛና የተረጋገጡ መረጃዎች በትክክለኛ የመስሪያ ቤቶቹ አድራሻ እንዲሁም በህዝብ መገናኛ ብዙሃን የሚነገሩት መሆናቸውን በማስገንዘብ ልጆቻችሁ እንዳይረበሹ ልታድርጉ ይገባል።

ተፈታኝ ተማሪዎች እንዲረበሹና የለፉበት ዝግጅታቸው እንዲደናቀፍባቸው የሚያደርጉ ሀሰተኛ የፈጠራ ወሬዎችን የምታሰራጩ አካላት ድርጊታችሁ ፍፁም ተገቢ ያልሆነ ፤ በትውልድ ላይም አሉታዊ ተፅእኖ ያለው መሆኑን በማወቅ ከድርጊታችሁ ልትታቀቡ ይገባል።

ተማሪዎች ምንጩ የማይታወቅ እና የተለያዩ አካላት ተከታይ ለማፍራት እንዲሁም ሆን ብለው ተማሪ እንዲረበሽ ለማድረግ ሲሉ በማህበራዊ ሚዲያ የሚያሰራጩትን መረጃ ወደ ጓደኞቻችሁ ባለመላክ ሀሰተኛ መረጃዎችን ተከላከሉ።

ለበለጠ ትምህርታዊ መረጃ @educate_ethiopia ቤተሰብ ይሁኑ

Credit: tikvah
5.5K viewsedited  20:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-14 12:25:21
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ቅድመ ዝግጅት ዙሪያ ፈተናው ከሚሰጥባቸው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አመራሮች ጋር ውይይት አካሄደ፡፡

ዘንድሮ ፈተናው በሀገር አቀፍ ደረጃ ከመስከረም 30/2015 ዓ.ም ጀምሮ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እንደሚሰጥ ቀደም ብሎ በትምህርት ሚኒስቴር የተገለጸ ሲሆን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርም ፈተናውን አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፤ ኮተቤ ትምህርት ዩኒቨርሲቲ ፤ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲና አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ለመስጠት የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተሰሩ ነው፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ ዘንድሮ ፈተናው ለመጀመሪያ ጊዜ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ቅጥር ግቢ ውስጥ የሚሰጥ እንደመሆኑ የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ የፈተና ሂደቱ በስኬት እንዲጠናቀቅ የተለያዩ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን በመስራት ላይ እንደሚገኝ ገልጸው ፈተናው የተማሪዎችን የቀጣይ የህይወት ምዕራፍ የሚወስን በመሆኑ በአዲስ አበባ ፈተናው የሚሰጥባቸው ተቋማትም ሆኑ ሌሎች ጉዳዩ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት አስፈላጊውን ዝግጅት ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው አስገንዝበዋል፡፡

በአዲስ አበባ 49,203 ተማሪዎች ፈተናውን ለመውሰድ መመዝገባቸውንና ፈተናውም ከመስከረም 30 ጀምሮ በቅድሚያ የሶሻል ሳይንስ ተማሪዎች ተፈትነው ሲጨርሱ የናቹራል ሳይንስ ተማሪዎች ቀጥለው እንደሚፈተኑ የተገለጸ ሲሆን ተፈታኝ ተማሪዎች በፈተና ወቅት የምግብና የመኝታ አገልግሎቶችን በየተቋማቱ እንደሚያገኙም ተጠቁማል፡፡

ለበለጠ ትምህርታዊ መረጃ @educate_ethiopia ቤተሰብ ይሁኑ


Credit: Temert Bebete
5.6K viewsedited  09:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ