Get Mystery Box with random crypto!

ሰመራ ዩኒቨርሲቲ በተያዘው ወር መጨረሻ ለሚሰጠው የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ቅድመ ዝግጅት እየተደ | Educate Ethiopia

ሰመራ ዩኒቨርሲቲ በተያዘው ወር መጨረሻ ለሚሰጠው የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ገልጿል።

ዩኒቨርሲቲው ከ8 ሺህ 100 በላይ የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች በትምህርት ሚኒስቴር ተመድበውለታል።

ከዩኒቨርሲቲው እና ከክልሉ ትምህርት ቢሮ የተውጣጣ ግብረ ኃይል ለፈተናው እየተደረገ ያለውን ዝግጅት ግምግሟል።

ዩኒቨርሲቲው ለተፈታኞች የመፈተኛ ክፍል፣ የምግብ እና የመኝታ ክፍል አገልግሎቶች ዝግጅት እያከናወነ እንደሚገኝ ተመላክቷል።

ፈተናውን ለመስጠት የቀረው ጊዜ አጭር በመሆኑ እየተደረገ ያለውን ዝግጅት በፍጥነት ማጠናቀቅ እንደሚገባ የዩኒቨርሲቲው አካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዝዳንት አብዱረህማን ከድር (ዶ/ር) ገልጸዋል።

ለበለጠ ትምህርታዊ መረጃ @educate_ethiopia ቤተሰብ ይሁኑ

Credit: tikvah