Get Mystery Box with random crypto!

Educate Ethiopia

የቴሌግራም ቻናል አርማ educate_ethiopia — Educate Ethiopia E
የቴሌግራም ቻናል አርማ educate_ethiopia — Educate Ethiopia
የሰርጥ አድራሻ: @educate_ethiopia
ምድቦች: እውነታው
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 25.70K
የሰርጥ መግለጫ

A channel dedicated to brighten Ethiopia through education .
We share study tips, tricks motivations and resources that will help your academic carrier.
For any questions @EducateEthiopiaBot
For any resources @EducateEthResources

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 12

2022-04-25 10:28:09 የዩኒቨርሲቲዎችን ትክክለኛ ገፅ ብቻ በመከተል ከሀሰተኛ የዩኒቨርሲቲ ጥሪዎች እራሳችሁን ጠብቁ ፦

ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ፦ https://m.facebook.com/DDUniv/

ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ፦ https://m.facebook.com/Hawassa.University/

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፦ https://m.facebook.com/Addis-Ababa-University-496255483792611/

ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፦ https://m.facebook.com/TheUniversityofGondar/

ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፦ https://m.facebook.com/bduethiopia/?ref=page_internal&mt_nav=0

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ፦ https://m.facebook.com/ArbaMinchUniversityCCD/?_se_imp=0ueaW0ZojpEObV9zR

ሀረማያ ዩኒቨርሲቲ ፦ https://m.facebook.com/HRMUNIV/

ጅማ ዩኒቨርሲቲ ፦ https://m.facebook.com/JimmaUniv/

አርሲ ዩኒቨርሲቲ ፦ https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=357578986410375&id=100064748293256

ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ፦https://m.facebook.com/pages/category/Education-website/Wolaita-Sodo-University-246568056057804/

ዋቻሞ ዩኒቨርሲቲ ፦ https://m.facebook.com/WachemoUniversity2008/

ጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ፦ https://www.facebook.com/265529850297666/posts/1845133279003974/?app=fbl

መደወላቡ ዩኒቨርሲቲ ፦ https://www.facebook.com/141864125910414/posts/4794315817331865/?app=fbl

ወለጋ ዩኒቨርሲቲ ፦ https://m.facebook.com/pages/category/Education-website/Wollega-University-Corporate-Communications-2319182621440303/

አሶሳ ዩኒቨርሲቲ ፦ https://www.facebook.com/234983083247967/posts/5141798579233035/?app=fbl

ወራቤ ዩኒቨርሲቲ ፦ https://www.facebook.com/2181225212102194/posts/3109977289226977/?app=fbl

ቦረና ዩኒቨርሲቲ ፦ https://m.facebook.com/BoranaUniversityBRU/

ቀብሪድሃር ዩኒቨርሲቲ ፦ https://m.facebook.com/pages/category/Education/Kebri-Dehar-University-306587496533329/

ጂንካ ዩኒቨርሲቲ ፦ https://m.facebook.com/pages/category/Education/Jinka-University-178538809733160/

ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ፦ https://www.facebook.com/547073878695780/posts/5065885566814566/?app=fbl

ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ፦ https://www.facebook.com/1879460055640998/posts/3057857987801193/?app=fbl

ወልዲያ ዩኒቨርሲቲ ፦ https://m.facebook.com/WoldiaUniversity/

ወሎ ዩኒቨርሲቲ ፦ https://m.facebook.com/WolloUniversity111/

ደምቢዶሎ ዩኒቨርሲቲ ፦ https://www.facebook.com/1301588393256101/posts/5145148712233364/?app=fbl

ኦዳቡልቱም ዩኒቨርሲቲ ፦ https://m.facebook.com/OBUEthiopia/

አምቦ ዩኒቨርሲቲ ፦ https://m.facebook.com/AmboUniversityofficial/

ሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ፦ https://m.facebook.com/Mizan-Tepi-University-MTU-362390684253048/

ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ፦ https://www.facebook.com/614590095253065/posts/5432186613493365/?app=fbl

ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ፦ https://www.facebook.com/979926502053136/posts/5129611493751262/?app=fbl

ሰመራ ዩኒቨርሲቲ ፦ https://www.facebook.com/336146983089022/posts/5029908297046177/?app=fbl

ኮተቤ ፦ https://www.facebook.com/792405150779154/posts/5397052686981021/?app=fbl

ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ፦ https://www.facebook.com/100064618752509/posts/386404006856888/?app=fbl

መቱ ዩኒቨርሲቲ ፦ https://www.facebook.com/330316734055129/posts/1468350973585027/?app=fbl

መቅደላአምባ ዩኒቨርሲቲ ፦ https://m.facebook.com/Mekdela.Amba.University/

ተጨማሪ ጥያቄዎች ካላችሁ ከታች በአስተያየት መስጫው አስቀምጡ።

via ቲክቫህ


@educate_ethiopia
9.5K views07:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-25 08:46:15
የዩኒቨርስቲ ምደባ ይፋ ሆነ

ትምህርት ሚኒስቴር የ2013ዓ.ም የ12ኛ ክፍል የዩኒቨርስቲ ምደባ ይፋ አድርጓል።

የ2013 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስደው ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ መንግስት ዩኒቨርስቲዎች በወጪ መጋራት (ስኮላርሽፕ) የመግቢያ መቁረጫ ነጥብ ላመጡ ተማሪዎች ምደባ ተደርጓል።

ከዚህ በፊት በተገለጸዉ የመቁረጫ ነጥብ እና ከኦሮሚያ፣ አማራ፣ አፋርና ቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች ተጨማሪ ተማሪዎች ምደባ የሚያስገኝላቸው ውሳኔ መተላለፉ ይታወሳል፡፡

በዚህም መሰረት ተማሪዎች ከዛሬ ጀምሮ የተመደቡበትን ዩኒቨርስቲ ለማየት በድህረገፅ፡-https://result.ethernet.edu.et ፣ በSMS፡- 9444 እንዲሁም በቴሌግራም፡- @moestudentbot መጠቀም ይችላሉ።

ተማሪዎች ከምደባ ጋር ተያይዞ ላላችው ማንኛውም ጥያቄ በድህረገፅ https://complaint.ethernet.edu.et በማመልከት ጥያቄዎቻቸውን ማቅረብ ይችላሉ፡፡

ዩኒቨርሲቲዎች እስከ ሚያዝያ 24/2014 ዓ.ም ድረስ ተገቢዉን ዝግጅት አድርገው የመጀመሪያ ዓመት አዲስ ገቢ ተማሪዎችን የቅበላ መርሃ ግብር የሚያሳዉቁ በመሆኑ ተማሪዎች አስፈላጊዉን ዝግጅት እንዲያደርጉም ሚኒስቴሩ ጥሪ ያቀርባል፡፡
ትምህርት ሚ/ር
@educate_ethiopia
7.7K views05:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-24 18:40:40 Educate Ethiopia pinned Deleted message
15:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-18 18:54:09 በአዲሱ ሴሚስተር አሪፍ ውጤት ለማምጣት አንዱ ማድረግ ያለባችሁ ነገር ለስኬት የሚያበቃ እቅድ ማውጣት ነው። ይህን እንዴት ማድረግ እንደሚቻል ለማወቅ ከታች ያለውን ቪዲዮ ተመልከቱ።

@educate_ethiopia







11.2K views15:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-14 17:17:31
#Addis_Ababa_Education_Bureau

በ2014 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ የ12ኛ ክፍል ሀገር ዐቀፍ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎች ምዝገባ ነገ
ሚያዝያ 07/2014 ዓ.ም ይጀመራል።

በከተማዋ ዘንድሮ ከ50 ሺህ በላይ ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ለመውሰድ ይመዘገባሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በከተማዋ በሚገኙ 201 የመንግስት እና የግል 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች 50 ሺህ 504 ተማሪዎች በቀን፣ በማታ እና በግል እንደሚመዘገቡ ይጠበቃል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የፈተና ዝግጅትና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት የ12ኛ ክፍል ፈተና ለሚያስፈትኑ የመንግስትና የግል 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የሀገር አቀፍ ፈተና የምዝገባ ስርዓት ኦረንቴሽን ሰጥቷል።

በመድረኩ የፈተና እና አይሲቲ ባለሙያዎች፣ የአማርኛ እና አፋን ኦሮሞ ትምህርት ቡድን መሪዎች እንዲሁም የትምህርት ቤት ርዕሳነ መምህራን ተገኝተዋል፡፡

ለበለጠ ትምህርታዊ መረጃ @educate_ethiopia ቤተሰብ ይሁኑ
12.0K viewsedited  14:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-14 11:31:33
" ከፍተኛ ጫና እያሳደረብን ነው "

የ2013 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ፈተና ተፈትነው ምደባ የሚጠባበቁ ተማሪዎች እና የተማሪ ወላጆች ምደባው እንዲፋጠንለቸው በድጋሚ ጠይቀዋል።

የመጀመሪያውን ዙር ፈተና ተፈትነው እና ውጤታቸውን አውቀው ቤታቸው የተቀመጡ ተማሪዎች 6ኛ ወራቸውን ሊደፍኑ እየተቃረቡ ይገኛሉ።

እስካሁን ምደባ ይፋ የሚሆንበት ቀን ይፋ ያልተደረገ ሲሆን ይህ ሁኔታ ተማሪዎችና ወላጆችን ጫና ውስጥ እየከተተ ነው።

መልዕክታቸውን የላኩ የቲክቫህ ቤተሰብ አባል የሆኑ አንድ ወላጅ ልጃቸው ብሄራዊ ፈተና ወስዳ ወራት ቢቆጠሩም እስካሁን የምትማርበትን ተቋም ባለማወቋ ጫና እየደረሰባት፤ በግል እንኳን ለማስተማር ውሳኔ ላይ ለመድረስ እንደተቸገሩ፤ አመቱም እየተጠናቀቀ በመሆኑ ከእሷም አልፎ ቤተሰብ ላይ ጫናው እየበረታ መምጣቱን ገልፀዋል።

ከትምህርት እንዳትርቅ ጥረት እያደረጉ መሆኑ የገለፁት ወላጅ ፤ ነገር ግን ከመደበኛው ትምህርት ስርዓት ተማሪ መነጠሉ የሚያሳድረው ጫና ከባድ ነው ብለዋል።

መንግስት ምናልባት የሚስተካከሉ የቀረቡ ቅሬታዎች ካሉ በፍጥነት አስተካክሎ እና መፍትሄ ሰጥቶ ተማሪዎችን በፍጥነት ምደባቸውን እንዲያሳውቅ ጠይቀዋል።

ሌሎች መልዕክታቸውን የላኩ የቤተሰቡ አባላት ተማሪዎች ከመደበኛው ትምህርት ውጭ ሆነው የሚያሳልፉት ጊዜ ከፍተኛ የስነልቦና ጫና ውስጥ እየጣላቸው በመሆን መንግስት መፍትሄ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል።

የ2013 ዓ/ም ፈተና የመጀመሪያ ዙር #ከጥቅምት 28/2014 ጀምሮ ለ4 ተከታታይ ቀናት የ2ኛው ዙር ፈተና #ከጥር 24 ጀምሮ ለተከታታይ 4 ቀን መሰጠቱትና ውጤትን ጨምሮ መቁረጫ ነጥብ ይፋ መደረጉ ይታወሳል።

ለበለጠ ትምህርታዊ መረጃ @educate_ethiopia ቤተሰብ ይሁኑ
9.8K viewsedited  08:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-07 21:02:01
#MoE

ትምህርት ሚኒስቴር የፈተና ስርቆትን ለመከላከል ፈተና በኦንላይን የማስፈተን ፤ ይህ ባይሆን እንኳን ተማሪዎችን ወደ ማዕከል ዩኒቨርሲቲዎች በማስመጣት ፈተና ለመስጠት እያሰበ ነው።

የትምህርት ሚኒስትር ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ዛሬ ለህ/ተ/ም/ቤት በሰጡት ማብራሪያ ባለፈው ዓመት ተጀምሮ የነበረውን የ12ኛ ክፍል ፈተናን በታብሌት ለመስጠት የተጀመረውን ስራ በከፍተኛ ደረጃ እየገፋንበት ነው ብለዋል።

ሂደቱ አሁን ላይ በአቅም ጉዳይ መቆሙን የገለፁት ሚኒስትሩ " ሁሉንም ሂደት ከጨረስን በኃላ ይሄ የሚጠይቀውን ወደ 1 ሚሊዮን ታብሌት ሃገር ውስጥ ለማስገባት ወደ 460 ሚሊዮን ዶላር ይጠይቃል፤ ይሄን ከቻይና መንግስት ጋር በሚደረግ ንግግር በእርዳታ ሊመጣ የሚችልበትን መንገድ በብዙ መንገድ ጠ/ሚኒስትሩም ገብተውበት እየገፋን ነው " ብለዋል።

" እሱ እንኳን ቢያቅተን በዚህ ዓመት የምንችለውን ሁሉ ሞክረን የምንወስደው እርምጃ ግን አንዱ በየትምህርት ቤቶቹ ፈተናን መፈት ትተን የሚያስወጣንን ወጪ አውጥተን ተማሪዎቹን ከየትምህርት ቤታቸው አምጥተን በየዩኒቨርሲቲ ማዕከላት ውስጥ ፈተናዎቹን እንዲወስዱ ማድረግ ነው ፤ ይሄን ነው አንዱ ልንሄድበት እያሰብን ያለነው " ብለዋል።

ሚኒስትሩ በአንድም ይሁን በሌላ መንገድ የፈተና ስርቆት መቆም አለበት ያሉ ሲሆን " ስርቆት መቆም ያለበት ሰነፍ ተማሪን እና ጎበዝ ተማሪን ለመለየት ብቻ ሳይሆን አጠቃላይ የሞራል መሰረታችንን እየበላው በመሆኑ ነው " ሲሉ ገልፀዋል።

አክለውም ፤ በቀጣይ አመት የሚጀመረው የመውጫ ፈተና የተገባበት አንድ ተማሪ ከታችን ያለውን አጭበርብሮ አልፎ ቢመጣ ኮሌጅም ከገባ በኃላ እንደገና ፈተና እንደሚጠብቀው አውቆ ቢያንስ ኮሌጅ ከገባ በኃላ በደንብ ተምሮ እንዲያውቅ ነው ብለዋል።

ለበለጠ ትምህርታዊ መረጃ @educate_ethiopia ቤተሰብ ይሁኑ
14.5K viewsedited  18:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-04 08:36:46
#MoE

የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና በ2015 ዓ/ም ተግባራዊ መሆን ይጀምራል።

ከዚህ ፈተና ጋር በተያያዘ በትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ልማት ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ የተናገረቱ ፦

" የመውጫ ፈተና ስትራተጂ የማዘጋጀት ስራ ተጠናቋል። ስትራቴጂውን ማስተግበሪያ መመሪያ በትምህርት ሚኒስቴር ተዘጋጅቷል።

ዝርዝር እቅድ ይህ የመውጫ ፈተና እንዴት ? ፤ መቼ ? ፤ በማን ? እንደሚሰጥ ፤ ፈተናው በማን እንደሚዘጋጅ ፤ የትምህርት ሚኒስቴር ሚና የዩኒቨርሲቲዎች ሚና ምን እንደሚመስል በዝርዝር ምላሽ የሚሰጥ የድርጊት መርሃ ግብር ተዘጋጅቷል።

የመውጫ ፈተና ሌላ ከውጪ የሚጫን ፈተና አይደለም። በስርአተ ትምህርቱ ውስጥ የተቀመጡትን የምሩቃኑን ፕሮፋይል መሳካት አለመሳካቱን ፤ መጨበጥ አለመጨበጡን የሚያረጋግጥ ነው። "

ለበለጠ ትምህርታዊ መረጃ @educate_ethiopia ቤተሰብ ይሁኑ
12.3K viewsedited  05:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-25 19:03:41
" በደብዳቤው ላይ የተገለጹት ሁለት መልዕክቶች በ2014 ዓ/ም የሁለተኛ ደረጃ ማጠቃለያ ፈተና ላይ ይተገበራሉ " የትምህርት ሚኒስቴር

ከላይ ደብዳቤ የ2014 ዓ/ም የሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ያለውን የትምህርት ይዘት እንደሚሸፍን እንዲሁም የኢኮኖሚክስ ትምህርት ፈተና እንደማይሰጥ ይገልጻል።

በትምህርት ሚኒስቴር የስርዐተ ትምህርት ዝግጅትና ምርምር ጄነራል ዳይሬክተር ዶክተር ቴዎድሮስ ሸዋርገጥ ደብዳቤው ትክክለኛ መሆኑንና ለክልሎችና ለከተማ አስተዳደሮች መላኩን አረጋግጠዋል።

ዳይሬክተሩ በደብዳቤው ላይ የተገለጹት ሁለት መልዕክቶች በ2014 ዓ/ም የሁለተኛ ደረጃ ማጠቃለያ ፈተና እንደሚተገበሩም አጽኖት ሰጥተዋል።

በደብዳቤው ላይም ተማሪዎች ይህን አውቀው መዘጋጀት እንዳለባቸው ተጠቅሷል።

Credit : ኢትዮጵያ ቼክ

ለበለጠ ትምህርታዊ መረጃ @educate_ethiopia ቤተሰብ ይሁኑ
15.2K viewsedited  16:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-25 10:34:07
#SPHMMC

በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌኒየም ሜዲካል ኮሌጅ በ2014 ዓ.ም ለመማር ያመለከታችሁ የጽሁፍ ፈተና እሁድ መጋቢት 18/2014 ዓ.ም ጠዋት 2:00 እንደሚሰጥ ተገልጿል።

ፈተናው የሚሰጠው በመድኃኒዓለም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ይሰጣል።

ማሳሰቢያ፦

• ሙሉ ስምና ፎቶ የሚያሳይ ሕጋዊ መታወቂያ
ፈተናውን ለመውሰድ ያስፈልጋል።
• ለፈተናው የሚጠቀሙት መለያ ቁጥር ለምዝገባ
የተሰጠዎትን መለያ ቁጥር ነው።
• እርሳስ፣ መቅረጫ እና ላፒስ መያዝ የግድ ነው።
እስክሪብቶ መጠቀም አይቻልም።
• ሞባይል ስልክ፣ ካልኩሌተር እና ቦርሳ ይዞ ወደ
ፈተና ክፍል መግባት አይቻልም።
• የተመደቡበትን የፈተና ክፍል ቀድመው
ይመልከቱ።
• ፈተናው ከተጀመረ ከ30 ደቂቃ በኋላ ወደ ፈተና
ክፍል መግባት አይቻልም።
• ፈተናው ተጀምሮ ከ40-50 ደቂቃ እስከሚሆን
ከፈተና ክፍል መውጣት አይቻልም።
• ማንኛውም አይነት የጤና ችግር ያለበት ተፈታኝ
አስቀድሞ ለአስተባባሪዎች ማሳወቅ ይኖርበታል።

ለበለጠ ትምህርታዊ መረጃ @educate_ethiopia ቤተሰብ ይሁኑ
10.1K viewsedited  07:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ