Get Mystery Box with random crypto!

' ከፍተኛ ጫና እያሳደረብን ነው ' የ2013 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ፈተና ተፈትነው ምደባ የሚጠባ | Educate Ethiopia

" ከፍተኛ ጫና እያሳደረብን ነው "

የ2013 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ፈተና ተፈትነው ምደባ የሚጠባበቁ ተማሪዎች እና የተማሪ ወላጆች ምደባው እንዲፋጠንለቸው በድጋሚ ጠይቀዋል።

የመጀመሪያውን ዙር ፈተና ተፈትነው እና ውጤታቸውን አውቀው ቤታቸው የተቀመጡ ተማሪዎች 6ኛ ወራቸውን ሊደፍኑ እየተቃረቡ ይገኛሉ።

እስካሁን ምደባ ይፋ የሚሆንበት ቀን ይፋ ያልተደረገ ሲሆን ይህ ሁኔታ ተማሪዎችና ወላጆችን ጫና ውስጥ እየከተተ ነው።

መልዕክታቸውን የላኩ የቲክቫህ ቤተሰብ አባል የሆኑ አንድ ወላጅ ልጃቸው ብሄራዊ ፈተና ወስዳ ወራት ቢቆጠሩም እስካሁን የምትማርበትን ተቋም ባለማወቋ ጫና እየደረሰባት፤ በግል እንኳን ለማስተማር ውሳኔ ላይ ለመድረስ እንደተቸገሩ፤ አመቱም እየተጠናቀቀ በመሆኑ ከእሷም አልፎ ቤተሰብ ላይ ጫናው እየበረታ መምጣቱን ገልፀዋል።

ከትምህርት እንዳትርቅ ጥረት እያደረጉ መሆኑ የገለፁት ወላጅ ፤ ነገር ግን ከመደበኛው ትምህርት ስርዓት ተማሪ መነጠሉ የሚያሳድረው ጫና ከባድ ነው ብለዋል።

መንግስት ምናልባት የሚስተካከሉ የቀረቡ ቅሬታዎች ካሉ በፍጥነት አስተካክሎ እና መፍትሄ ሰጥቶ ተማሪዎችን በፍጥነት ምደባቸውን እንዲያሳውቅ ጠይቀዋል።

ሌሎች መልዕክታቸውን የላኩ የቤተሰቡ አባላት ተማሪዎች ከመደበኛው ትምህርት ውጭ ሆነው የሚያሳልፉት ጊዜ ከፍተኛ የስነልቦና ጫና ውስጥ እየጣላቸው በመሆን መንግስት መፍትሄ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል።

የ2013 ዓ/ም ፈተና የመጀመሪያ ዙር #ከጥቅምት 28/2014 ጀምሮ ለ4 ተከታታይ ቀናት የ2ኛው ዙር ፈተና #ከጥር 24 ጀምሮ ለተከታታይ 4 ቀን መሰጠቱትና ውጤትን ጨምሮ መቁረጫ ነጥብ ይፋ መደረጉ ይታወሳል።

ለበለጠ ትምህርታዊ መረጃ @educate_ethiopia ቤተሰብ ይሁኑ