Get Mystery Box with random crypto!

#Addis_Ababa_Education_Bureau በ2014 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ የ12ኛ ክፍ | Educate Ethiopia

#Addis_Ababa_Education_Bureau

በ2014 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ የ12ኛ ክፍል ሀገር ዐቀፍ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎች ምዝገባ ነገ
ሚያዝያ 07/2014 ዓ.ም ይጀመራል።

በከተማዋ ዘንድሮ ከ50 ሺህ በላይ ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ለመውሰድ ይመዘገባሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በከተማዋ በሚገኙ 201 የመንግስት እና የግል 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች 50 ሺህ 504 ተማሪዎች በቀን፣ በማታ እና በግል እንደሚመዘገቡ ይጠበቃል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የፈተና ዝግጅትና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት የ12ኛ ክፍል ፈተና ለሚያስፈትኑ የመንግስትና የግል 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የሀገር አቀፍ ፈተና የምዝገባ ስርዓት ኦረንቴሽን ሰጥቷል።

በመድረኩ የፈተና እና አይሲቲ ባለሙያዎች፣ የአማርኛ እና አፋን ኦሮሞ ትምህርት ቡድን መሪዎች እንዲሁም የትምህርት ቤት ርዕሳነ መምህራን ተገኝተዋል፡፡

ለበለጠ ትምህርታዊ መረጃ @educate_ethiopia ቤተሰብ ይሁኑ