Get Mystery Box with random crypto!

Educate Ethiopia

የቴሌግራም ቻናል አርማ educate_ethiopia — Educate Ethiopia E
የቴሌግራም ቻናል አርማ educate_ethiopia — Educate Ethiopia
የሰርጥ አድራሻ: @educate_ethiopia
ምድቦች: እውነታው
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 25.70K
የሰርጥ መግለጫ

A channel dedicated to brighten Ethiopia through education .
We share study tips, tricks motivations and resources that will help your academic carrier.
For any questions @EducateEthiopiaBot
For any resources @EducateEthResources

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 9

2022-10-03 21:19:10
በአማራ ክልል የ12ኛ ክፍል ፈተና በ10 የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ በሚገኙ 31 ማዕከላት ይሰጣል፡፡

ፈተናው ያለምንም የጸጥታ ችግር እንዲጠናቀቅ እየሠራ መሆኑን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ገልጿል።

በክልሉ ሁሉም የመፈተኛ ተቋማት እና ማዕከላት በቂ የጸጥታ ቅድመ ዝግጅት መደረጉን ምክትል ኮሚሽነር እንየው ዘውዴ ገልጸዋል፡፡

በተመሳሳይ ወረዳን ማዕከል አድርጎ ተማሪዎችን ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በተቀመጠው ጊዜ ለማድረስ በቂ የትራንስፖርት አገልግሎት ዝግጅት ማድረጉን የትራንስፖርት እና ሎጀስቲክ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ውቤ አጥናፉ ተናግረዋል፡፡

ተማሪዎች የወረዳ ትራንስፖርት ቢሮ በሚያወጣው መርሃ ግብር መሰረት በጊዜ እየተገኙ እንዲስተናገዱ ጠይቀዋል፡፡

ሀገራዊ ግዴታቸውን በአግባቡና በሀላፊነት የማይወጡ የትራንስፖርት ማህበራትና ባለሀብቶች በትራንስፖርት መመሪያ እና በሕግ ይጠየቃሉ ብለዋል፡፡

ተማሪዎች በሚጓጓዙባቸው ቀናት መደበኛ ትራንስፖርት ስለማይኖር ሕዝቡ ቅድመ ዝግጅት በማድረግ እንዲተባበር ጥሪ አድርገዋል፡፡

#አሚኮ
899 views18:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-03 20:31:56
የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በሰላም እንዲካሄድ በቂ ዝግጅት ማድረጉን ፌደራል ፖሊስ ገልጿል።

ፌደራል ፖሊስ ከሁሉም ክልሎች እና ከሁለቱ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽኖች ጋር በመቀናጀት ብሔራዊ ፈተናው በሰላም እንዲጠናቀቅ በቂ ዝግጅት ማድረጉን አሳውቋል።

ፈተናው ከማንኛውም የፀጥታ ችግር ነፃ ሆኖ ተፈታኞች ያለምንም ስጋት ተረጋግተው መፈተን እንዲችሉ የፀጥታ መዋቅሩ ፈተናውን አጅቦ ለማጓጓዝ እና ጠንካራ ፍተሻዎችን ለማድረግ በቂ ዝግጅት ማድረጉን
የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጄነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል ገልጸዋል።

ለበለጠ ትምህርታዊ መረጃ @educate_ethiopia ቤተሰብ ይሁኑ

Credit: tikvah
1.2K viewsedited  17:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-03 16:15:18
ጎንደር ዩኒቨርሲቲ አዲስ ሞዴል ፋርማሲ በይፋ ሥራ አስጀምሯል።

ሞዴል ፋርማሲው የአካባቢውን ማህበረሰብ ከማገልገሉ በተጨማሪ ለበርካታ ወጣቶች የሥራ ዕድል እንደሚፈጥር የጎንደር ዩኒቨርሰቲ ፕሬዝዳንት አስራት አጸደወይን (ዶ/ር) ገልጸዋል።

ለጎንደር ዩኒቨርሲቲ የፋርማሲ ትምህርት ቤት መማሪያነትም እንደሚያገለግል ጠቁመዋል።

ሞዴል ፋርማሲው ማህበረሰብን እያገለገለ ገቢ እንዲያመነጭ የተቋቋመው "እቴጌ ምንትዋብ ንግድና ማማከር አገልግሎት ኢንተርፕራይዝ" አካል መሆኑ ተመላክቷል።

የኢንተርፕራይዙ መጠናከር ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ለሚያደርገው ራስ ገዝ (ኦቶኖመስ) የመሆን ጉዞ ወሳኝነት ይኖረዋል ተብሏል።

ለበለጠ ትምህርታዊ መረጃ @educate_ethiopia ቤተሰብ ይሁኑ

Credit: tikvah
672 views13:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-03 12:48:13
በ12ኛ ክፍል ፈተና አሰጣጥ ዙሪያ ለጋዜጠኞች መግለጫ ተሰጠ
--------------------------------------------
ትምህርት ሚኒስቴር የ2014ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና አሰጣጥ ዙሪያ ማብራሪያና መግለጫ ሰጥቷል።

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ ፈተናውን በተሳካ ሁኔታ ለመስጠት አስፈላጊው ዝግጅት መደረጉን የገለጹ ሲሆን ሂደቱ ተማሪዎች በራስ ጥረት ብቻ ውጤታማ የሚሆኑበት ነው ብለዋል።

ከዚህም መካከል የፈተናው ዝግጅትና ህትመት በቴክኖሎጂ ታግዞ በከፍተኛ ጥንቃቄና ከደህንነት ስጋት ነፃ በሆነ መልኩ መከናወኑን በመግለጫቸው  ተናግረዋል።

እስከ አሁን በነበረው የቅድመ ዝግጅት ሂደትም ከሚመለከታቸው የፌደራል እና የክልል መንግስታት የስራ ሃላፊዎች ጋር በቅንጅት እየተሰራ እንደሆነም ሚኒስትሩ ገልፀዋል።

በመግለጫው ሀገር አቀፍ ፈተናው በሁለት ዙር የሚሰጥ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን በዚህም በመጀመሪያው ዙር  የሶሻል ሳይንስ ተማሪዎች  ከመስከረም 30,2015 ዓ.ም እስከ ጥቅምት 02,2015 ዓ.ም ፈተናውን ሲወስዱ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ከ ጥቅምት 8,2015 ዓ.ም እስከ 11,2015 ዓ.ም ፈተናውን ይወስዳሉ ተብሏል።

ተፈታኞችም  ፈተናው ከሚሰጥበት ቀን በፊት ባሉት ሶስት ቀናት በሚፈተኑበት ዩኒቨርስቲዎች መገኘት እና ኦረንቴሽን መውሰድ እንደሚጠበቅባቸውም ተነግሯል።

ከፈተናው ቀን በፊት ባሉት ቀናት ተማሪዎችን ወደ ፈተና ቦታ የማምጣት እና ፈተናው እንዳለቀም ተማሪዎችን ወደየመጡበት አካባቢ የመመለስ ስራ እንደሚሰራም ተገልጿል።

ለበለጠ ትምህርታዊ መረጃ @educate_ethiopia ቤተሰብ ይሁኑ
1.3K viewsedited  09:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-02 18:52:33
በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሳይንስ ኮሌጅ በ2015 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በቀን መርሃ ግብር በሁለተኛ እና በሦሥተኛ ዲግሪ ለመማር ያመለከታችሁ አመልካቾች የመግቢያ ፈተና መስከረም 25/2015 ዓ.ም እንደሚሰጥ ተገልጿል።

በዕለቱ ማንነትን የሚገልፅ መታወቂያ በመያዝ ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት በፔዳ ግቢ እንድትገኙ ኮሌጁ አሳስቧል፡፡

በአመልካች እጥረት በማይከፈቱ የሁለተኛ ዲግሪ ፕሮግራሞች ያመለከታችሁ ተማሪዎች ተዛማች ትምህርት ክፍሎችን በማናገር መፈተን እንደምትችሉ ተቋሙ ገልጿል።

ለበለጠ ትምህርታዊ መረጃ @educate_ethiopia ቤተሰብ ይሁኑ

Credit: tikvah
1.1K viewsedited  15:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-02 17:40:16
በሁሉም የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የኦንላይን ትምህርት ሊሰጥ ነው።

የትምህርት ሚኒስቴር በመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የኦንላይን ትምህርት ለመስጠት የዕውቅና ፍቃድ ጥያቄን ጨምሮ የተለያዩ ዝግጅቶች ማድረጉ ተገለጸ፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር ከማስተር ካርድ ፋውንዴሽን ጋር በመነጋገር ኢ-ለርኒንግን ለማስፋፋት ፕሮጀክት ቀርጾ የ22 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ማግኘቱንና በአሜሪካው አሪዞና ዩኒቨርሲቲ አማካይነት መርሃ ግብሩን ዕውን ለማድረግ ሥራዎች መጀመራቸው ታውቋል፡፡

በኢትዮጵያ የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች በርቀት የትምህርት መደብ የተወሰኑ ትምህርቶችን ቢሰጡም በመደበኛነት የኦንላይን ትምህርት ለመስጠት የትምህርትና ሥልጠና ባለሥልጣን ፈቃድ የሰጠው የትምህርት ተቋም የለም።

ትምህርት ሚኒስቴር በተያዘው ዓመት አምስት ዩኒቨርሲቲዎች በኦንላይን ትምህርት ለመስጠት ፈቃድ እንዲያገኙ ለማድረግ ማቀዱን የገለጸ ሲሆን ሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች ደረጃ በደረጃ የኦንላይን ትምህርት እንዲሰጡ መታቀዱ ተገልጿል፡፡

የኦንላይን/E-Learning ትምህርቱ ዋነኛ ትኩረቶች፦

ታዋቂ ዩኒቨርሲቲዎች የሚጠቀሙበት የትምህርት አማራጭ በሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች ማቅረብ።

ሁሉም መምህራን በኦንላይን የመማር ማስተማር የትምህርት ዘዴ ተጨማሪ ስልጠና ይወስዳሉ።

የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በኦንላይን ለመማር የሚችሉበት ሰልጠና ይሰጣቸዋል፡፡

የኦንላይን ትምህርትን ለማስፋፋት የትምህርትና ሥልጠና ባለስልጣን ከዚህ ቀደም ባወጣው መመርያ ፈቃድ የወሰዱ ውስን የግል ዩኒቨርሲቲዎች ብቻ እንደነበሩ ተገልጿል፡፡

የትምህርት ተደራሽነትን ለማስፋት ዩኒቨርሲቲዎች ቴክኖሎጂን ተጠቅመው የኦንላይንን ትምህርትን ለማጠናከር የመሠረተ ልማቶችንና ፋሲሊቲዎችን የማሟላት ሥራዎች መጀመራቸው ተገልጿል።

#ሪፖርተር

ለበለጠ ትምህርታዊ መረጃ @educate_ethiopia ቤተሰብ ይሁኑ
1.3K viewsedited  14:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-02 12:47:35
#ማስታወሻ

የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና መሰጠት ሊጀምር ቀናቶች ቀርተዋል።

የተፈታኝ ተማሪዎች ግዴታዎችን ይመልከቱ

ለበለጠ ትምህርታዊ መረጃ @educate_ethiopia ቤተሰብ ይሁኑ

Credit: tikvah
1.8K views09:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-01 13:33:54
2.6K views10:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-29 14:30:44
#ጥቆማ

የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት አስተዳደር ከ2013 ዓ.ም ጀምሮ በኮምፒውተር ሳይንስ፣ ሶፍትዌር ኢንጂነሪንግ፣ ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ፣ ማኔጅመንት ኢንፎርሜሽን ሲስተም እና ተዛማጅ የትምህርት መስኮች በመጀመሪያ ዲግሪ ለተመረቁ ተማሪዎች በልዩ ሁኔታ የስራ ቅጥር ለመፈፀም ማስታወቂያ አውጥቷል።

በዚህም፦

በሶፍትዌር ልማት ልዩ ተሰጥኦ ወይም አቅም ያላቸሁ ከዚህ በታች ያለውን ማስፈንጠሪያ (Link) በመጫን መሰረታዊ መረጃችህን የያዘ ሲቪ ከሁለት/2/ ገፅ ያልበለጠ እስከ መስከረም 30/2015 እንድታያይዙ ተቋሙ ጠይቋል።

https://www.insa.gov.et/web/guest/vacancy

መልካም ዕድል!

ለበለጠ ትምህርታዊ መረጃ @educate_ethiopia ቤተሰብ ይሁኑ

Credit: tikvah
1.3K viewsedited  11:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ