Get Mystery Box with random crypto!

በሁሉም የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የኦንላይን ትምህርት ሊሰጥ ነው። የትምህርት ሚኒስቴር በመንግሥ | Educate Ethiopia

በሁሉም የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የኦንላይን ትምህርት ሊሰጥ ነው።

የትምህርት ሚኒስቴር በመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የኦንላይን ትምህርት ለመስጠት የዕውቅና ፍቃድ ጥያቄን ጨምሮ የተለያዩ ዝግጅቶች ማድረጉ ተገለጸ፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር ከማስተር ካርድ ፋውንዴሽን ጋር በመነጋገር ኢ-ለርኒንግን ለማስፋፋት ፕሮጀክት ቀርጾ የ22 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ማግኘቱንና በአሜሪካው አሪዞና ዩኒቨርሲቲ አማካይነት መርሃ ግብሩን ዕውን ለማድረግ ሥራዎች መጀመራቸው ታውቋል፡፡

በኢትዮጵያ የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች በርቀት የትምህርት መደብ የተወሰኑ ትምህርቶችን ቢሰጡም በመደበኛነት የኦንላይን ትምህርት ለመስጠት የትምህርትና ሥልጠና ባለሥልጣን ፈቃድ የሰጠው የትምህርት ተቋም የለም።

ትምህርት ሚኒስቴር በተያዘው ዓመት አምስት ዩኒቨርሲቲዎች በኦንላይን ትምህርት ለመስጠት ፈቃድ እንዲያገኙ ለማድረግ ማቀዱን የገለጸ ሲሆን ሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች ደረጃ በደረጃ የኦንላይን ትምህርት እንዲሰጡ መታቀዱ ተገልጿል፡፡

የኦንላይን/E-Learning ትምህርቱ ዋነኛ ትኩረቶች፦

ታዋቂ ዩኒቨርሲቲዎች የሚጠቀሙበት የትምህርት አማራጭ በሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች ማቅረብ።

ሁሉም መምህራን በኦንላይን የመማር ማስተማር የትምህርት ዘዴ ተጨማሪ ስልጠና ይወስዳሉ።

የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በኦንላይን ለመማር የሚችሉበት ሰልጠና ይሰጣቸዋል፡፡

የኦንላይን ትምህርትን ለማስፋፋት የትምህርትና ሥልጠና ባለስልጣን ከዚህ ቀደም ባወጣው መመርያ ፈቃድ የወሰዱ ውስን የግል ዩኒቨርሲቲዎች ብቻ እንደነበሩ ተገልጿል፡፡

የትምህርት ተደራሽነትን ለማስፋት ዩኒቨርሲቲዎች ቴክኖሎጂን ተጠቅመው የኦንላይንን ትምህርትን ለማጠናከር የመሠረተ ልማቶችንና ፋሲሊቲዎችን የማሟላት ሥራዎች መጀመራቸው ተገልጿል።

#ሪፖርተር

ለበለጠ ትምህርታዊ መረጃ @educate_ethiopia ቤተሰብ ይሁኑ