Get Mystery Box with random crypto!

ƝƲƦƲ ሳይቴክ

የቴሌግራም ቻናል አርማ nurudish — ƝƲƦƲ ሳይቴክ Ɲ
የቴሌግራም ቻናል አርማ nurudish — ƝƲƦƲ ሳይቴክ
የሰርጥ አድራሻ: @nurudish
ምድቦች: እውነታው
ቋንቋ: አማርኛ
ሀገር: ኢትዮጵያ
ተመዝጋቢዎች: 8.06K
የሰርጥ መግለጫ

ይህ ቻናል ፈጠራዎችን ፣ መረጃዎችን በአማርኛ& English፣የቴክኖሎጂ እውነታዎችን ፣ የወደፊቱን ቴክኖሎጂ እና የአይቲ ምክሮችን በማካተት የቴክኖሎጂ ዓለምን ያቀርባል፡፡
በተጨማሪም፦ ዌብሳይት በተመጣጣኝዋጋ እንሰራለን
🔷 ማህበራዊ ሚዲያን ለእውቀት ብቻ እንጠቀምበት !
🔺 ጥያቄ እና አስተያየት ካለ በዚህ ስልክ ያሳውቁን! 251945686310

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2021-02-14 04:43:50 SDና HD ሪሲቨር ልዩነት ምንድን ነው?
በሁለቱ መካከል ያለው ዋነኛው ልዩነት
Standard Definition (የመደበኛ ጥራት) (ኤስዲ) ወይም High Definition (ከፍተኛ ጥራት (ኤች ዲ)) ያላቸውን የቴሌቪዥን ስርጭቶችን ለማሳየት መቻላቸው ነው ፡፡
የኤስዲ(SD) ሪሲቨር ሣጥን መደበኛ ጥራት(Standard Definition) የቴሌቪዥን ቻናል ስርጭቶችን ብቻ ማሳየት ይችላል።
ኤችዲ(HD) ሪሲቨር High Definition (ከፍተኛ ጥራት) ደግሞ ሁለቱንም መደበኛ ጥራት እና ከፍተኛ ጥራት ቻናሎችን ያሳያል ፡፡ ኤችዲ ሪሲቨር እንደ HDTV ማሳያ እንዲጠቀሙባቸው ከኮምፒዩተር ማሳያዎች(ሞኒተር) ጋር ማያያዝም ይቻላል ፡፡
◄◄◄◄◄◄ ▻▻▻▻▻▻▻▻
ሪሲቨር ስንገዛ ምን ምን ነገሮችን ማየት አለብን ☜
መጀመሪያ ድ ሪሲቨር ለመግዛት ወደገበያ
ስንወጣ ማየት ያለብን ብዙ ነገሮች አሉ
አለበለዚያ በቸልተኝነት ያገኘነዉ ሪሲቨር ገዝተን
ሪሲቨሩ ወር ባልሞላ ጊዜ ዉስጥ የሚፈልጉት
ነገሮች ባይሰራ ወይም ሪሲቨሩ ብዙም
ሳይጠቀሙበት ቢበላሽ በተጨማሪ ወጪ መጋለጦ አይቀሬ ነዉ፡፡
1. መጀመሪያ ሪሲቨሮን ከሶኬት ጀምሮ ማየት ነዉ የሪሲቨሩ ስኬት ቶሎ ሚቆረጥ ሊሆን ስለሚችል ነዉ
2. በመቀጠል ሪሞቱን እናያለን እቤታችን ዉስጥ ህፃናት ካሉ ሪሞት አይበረክትም ስለዚህ የሪሞቱን ጥንካሬ ልብብሎ ማየት ነዉ ሪሞቱ ቢበላሽ ገበያ ላይ በቀላሉ ማግኘት መቻሎትንም ማረጋገጥ አለቦት
3. ሪሲቨሩ በአሁን ሰአት በሪሲቨር
ቴክኖሎጂ ዉስጥ ያሉትን አዳዲስ ነገሮች መያዙን ማየት ወይም መጠየቅ ነዉ
✿ለምሳሌ በቤትዎ ነፃ የኳስ
ቻናል ማየት ቢፈልጉ በቀላሉ ያለ ሶፍትዌር biss key , Tandbrge የመሳሰሉትን ያለ ሶፍትዌር ማየት አለቦት
4. ሌላኛዉ ነገር ሪሞታችን ባይሰራ ሪሲቨሩ ላይ ሙሉ በተን አለዉ ወይ ? ብላችሁ ማየት ጠቃሚ ነገር አለያቸዉ ላይ ምንም በተን የላቸዉ
✿ለምሳሌ እርሶ ቻናል
ለመቀየር ወይም ድምጽ ለመጨመር ፈልገው ሪሞቱ ምንም አልሰራ ቢለዎትስ ሪሲቨሩ ምንም በተን ባይኖረዉ በሰአቱ በጣም ይናደዳሉ በተን ካለዉ ግን ሪሞት እስክንገዛ ሪሲቨሩ ላይ ባለዉ በተን እየነካን እንጠቀማለን
5. እንደዚሁም ሪሲቨሩ
ሚያጫዉታቸዉ የvideo format ማየት ነዉ፡፡
✿ለምሳሌ FLV ,MPGMPG4 ,3GP , ETC
የመሳሰሉትን SUPPORT ማድረጉን ማየት
6. ሌላኛዉ በተለያዩ ጊዜዋች
አዳዲስ ነገሮች የመጡ ሶፍትዌሮች ቶሎየ ሚለቀቅለት ሪሲቨር መሆን አለበት
7. የሪሲቨሩ ግራፊክስ ማየት አለብን ሌሎች መረጃዎች እንዲደርስዎ ፔጁን like ያድርጉ
363 viewsƝƲƦƲ ሳይቴክ, edited  01:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-10 12:03:28 #የዳታ_መቆጣጠሪያ_አፕሊኬሽን_ልጠቁማችሁ

በሞባይል ስልካችን ኢንተርኔት ስንጠቀም የሚያሳስበን ዋናውና ትልቁ ነገር የዓየር ሰዓት(የሞባይል ካርድ) ወጪ ነው፡፡ የሞባይል ካርድ እየሞላን #ፌስቡክ፤#ዩቲዩብ፤#ኢንስተግራም፤#ቴሌግራም እና አንድ አንድ መረጃዎችን ብራውዝ እናደርጋለን፡፡

ነገር ግን ይበቀኛል ብለን የሞላነው የሞባይል ካርድ(በጥቅል መልኩም ይሁን በመደበኛ) ድንገት ሙልጭ ብሎ ያልቅና ያበሳጨናል፡፡

ለምንድን ነው የሞላነው ሞባይል ካርድ ቶሎ የሚያልቅብን?

1ኛ፡- የዓየር ሰዓትና የኢንተርኔት ጥቅል ዋጋ ውድ በመሆኑ፣

2ኛ፡- የኛ የአጠቃቀም ችግር፦

የመጀመሪያው ችግር አሁን ለግዜው ምንም ማድረግ አንችልም፡፡ ሁለተኛው ምክንያት ማለትም የኛ የአጠቃቀም ችግር ግን ማስተካከል ይቻላል፡፡

የአጠቃቀም ችግር ማለት ምን ማለት ነው?

ኢንተርኔት ስንጠቀም ቢያንስ 4 ዓይነት ኮንተንቶችን ብራውዝ እናደርጋለን፡፡ እነሱም #ቪዲዮ፤#ፎቶ፤#ሙዚቃ(ድምፅ)፤#ፁሁፍ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡እነዚህ ኮንተንቶች ዳታ አጠቃቀማቸው ይለያያል፡፡ ለምሳሌ #ቪዲዮና #ፎቶ እኩል ዳታ አይጠቀሙም፡፡#ቪድዮ የበለጠ ዳታ ይጠቀማል፡፡ስለዚህ #ቪዲዮ ውድ ነው ማለት ነው፡፡በተመሳሳይ መልኩ በኢንተርኔት #ሙዚቃ ከማዳመጥ እና የተለያዩ #ፁሆፎች ከማንበብ፤ሙዚቃ ማዳማጥ ይበልጥ ሞባይል ካርዳችንን ይበላል፡፡

ስለዚህ ኢንተርኔት ስንጠቀም የሞላነውን ካርድ የሚበሉብን ኮንተንቶች በቅደም ተከተል የሚከተለውን ይመስላሉ፡-

1ኛ፡- #ቪዲዮ
2ኛ፡- #ፎቶ
3ኛ፡- #ፁሁፎች…

የሆነ ፁሁፍ ለማንበብ ብለን ሞባይል ካርድ ሞልተን ኢንተርኔት መጠቀም ስንጀምር ፁሁፉን ትተን ቪዲዮ ማየት ከጀመርን(ቪዲዮ ብዙ ይበላል) ካርዱ ሲያልቅ ያሰብነውን ስላላረግን ያበሳጨናል፡፡

ስለዚህ ማቀድ ያስፈልጋል፡፡ከዚያም ያቀድነውን ማድረግ ያስፈለጋል ማለት ነው፡፡

ሞባይል ካርድ ሞልተን ኢንተርኔት ብራውዝ ስናደርግ ያቀድነውን ለማድረግ ዳታችንን መቆጣጠር ይኖርብናል፡፡ዳታ መቆጣጠር ማለት ለምሳሌ 1Gb ኢንተርኔት ጥቅል ሞልታችሁ ከሆነ ኢንተርኔት መጠቀም ስትጀምሩ ለምሳሌ ፌስቡክ ብራውዝ አድርጋችሁ ስትጨርሱ ከ1Gb ውስጥ ምን ያህል ቀረኝ የሚለውን መቆጣጠር ማለት ነው፡፡

የሞላችሁት የኢንተርኔት ጥቀል ለመቆጣጠር “Internet Speed Meter Lite” የሚባል አፕሊኬሽን አለ፡፡ ነፃ ነው፡፡ አፕሊኬሽኑን ዳውንሎድ ታደርጉታላችሁ፡፡ ከዚያ ስታስነሱት ዳታችሁን ይቆጣጠርላችኋል ፡፡

ይህ አፕሊኬሽን ፡-

1ኛ፡-ምን ያህል ዳታ እንደተጠቀማችሁ ወይም እየተጠቀማችሁ መሆኑን ይነግራችኋል፣

2ኛ፡-የትኛው አፕሊኬሽን ብዙ ዳታ እየበላባችሁ እንደ ሆነ ይነግራችኋል፡፡..ወዘተ

ስለዚህ በዚህ ዓይነት መልኩ ዳታችሁን እየተቆጣጠራችሁ እና እየቆጠባችሁ በመጠቀም ቢያንስ የሞላችሁትን ሞባይል ካርድ ድንገት ሙልጭ ብሎ ከማለቅ ትድናላችሁ፡፡

የአፕሊኬሽኑ ሊንክ ይሄው፡-
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.internet.speed.meter.lite

#ሼር_ይደረግ
1.6K viewsƝƲƦƲ ሳይቴክ, 09:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-05 10:39:01 ቅድመ ማስጠንቀቅያ for smart phone users
"""""""""""""""""""""""""""""
የጠፋብን ወይም የተሰረቀ ሞባይል በቀላሉ ማግኘት
የምቻልበት መንገድ።
ሞባይላችን ከጠፋ ወይም ከተሰረቅን በኋላ ወደ ፖሊስ
ከመሄድ፥ እግራችን እና እጃችን ሰብስብን ከመቀመጥ፥
በሞባይላችን ያስቀመጥናቸው ኣስፈላጊ የሆኑ መረጃዎች
ከጥንቃቄ ጉድለት ጠፍቶብን ወይኔ ከማለት የምያድነን ቀላሉ
መንገድ።
ሞባይል የተለየ የራሱ የሆነ IMEI ኣለው፡
ማለትም international mobile equipment Identity
የይህንን ቁጥር በመጠቀም ሞባይላችን ያለበት ቦታ ማወቅ
እንችላለን።
የሚከተለው መንገድ መከተል እንችላለን።
1) *#06# ይደውሉ
2)የሞባይላች የተለየ 15 ቁጥሮች ወይም ልዩ ኮድ IMEI
ያሳየናል።
3) የይህንን ቁጥር ማስታወሻችን ላይ ማስፈር ፡
ምክንያቱም የይህንን ቁጥር ሞባይላችን ከጠፋብን ወይም
ከተሰረቅን የምንፈልግበት መንገድ ኣንዱ ዘዴ ነው ።
ሞባይላችን ከጠፋ ወይም ከተሰረቀ ይህንን ምስጥራዊ ኮድ
IMEI በ ኢሜል( e mail ) ወደ
cop@vsnl.net ከምከተለው ዝርዝር ጋር እንልካለን።
# Your name .......................
# Address .......
# Phone model ....
# Make ..........
# Last used number ,................
# E mail for comunication .........
# Missed date ....
#.IMEI number
# በ24 ሰዓታት ውስጥ በተራቀቀው GPRS system
በመጠቀም ኣድራሻውን ማግኘት እንችላለን፡ ሞባይላችን ከማን እጅ ጋር እንዳለና ማን እየተጠቀመበት እንዳለ ፡ እየተጠቀመበትያለው ግለሰብ ቁጥር በ email ይላካል ማለት ነው።
ወደ ሁሉም እንድደርስ share and like ።
2.6K viewsƝƲƦƲ ሳይቴክ, 07:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-04 10:05:07 ጥቁር መረብ (Dark web)

ጥቁር መረብ የጥልቅ መረብ(Deep web) ትንሹ አካል ሲሆን ከሌላው መረብ( Standard Web) ወይም ኔትዋርክ የተደበቀ ሲሆን በተለመዱት አሳሽ ሶፍትዌር (Browser) ማልትም ፋየር ፋክስ፤ጎግል ክሮም፤ኦፔራ የመሳሰሉት ጥቁር መረብን ማግኘት #አይቻሉም፡፡ ጥቁር ድር ብዙን ግዜ በህግ የተከለከሉ እቃዋች የሚሸጡበት እና ከፍተኛ የሆነ የጥቁ ገበያ (Black Market) የሚካሄድበት ቦታ ነው። በጥቁር ድር እንደ ናርኮቲክ, (Child porn), የተሰረቁ ክሬዲት ካርዶች, እና ሌሎች ህገወጥ እቃዎች በቀላሉ ማግኘት ይችላሉ። በጨለማ(ጥቁር) ድር ውስጥ የሚደረጉ አብዛኛዎቹ ግብሮች #በቢትኮይን (Bitcoin) እና በሌላ ኤሌክትሮ ሜል-መገበያያ ይከናወናሉ።

ጥቁር ድር የጥቁር መረብ ትንሽ አካል ሲሆን ሁለት አይነት ነትዋርክ ይጠቀማል።አንደኛው አቻ- ለ-አቻ-ኔትወርኮች(peer to peer network) እና ሁለተኛ ታዋቂ አውታረ መረቦች ያሉ ቶር(Tor)፣ ፍሪኔት(Freenet)፣ አይቱፒ( I2P)፣ ሪፍል(Riffle ) ፣በህዝባዊ ድርጅቶች እና ግለሰቦች የሚተዳደሩ ነትዋርክ ያካታል።የጨለማው ድር ተጠቃሚዎች መደበኛ ድርን(standard web) እንደሚከተለው ይገልጹታል፦" ሚስጥራዊ ባለመሆኑ ምክንያት ማንም ሰው ልያጠቃን ወይም መረጃ ልንተውለት እንችለን" ብለው ያምናሉ።

ጨለማ ድር ከሚያስጠቅም ሶፍትዌር መካከል ዋናው እና ተዋቂው አንዱ ቶር ብሮዘር ነው። ቶር ብሮዘር ኦውየንላንድ በመባል የሚታወቀው የኔትወርክ ከፍተኛ ደረጃን (top domain) ቅጥያ(suffix) የሚጠቀም ሲሆን ከፍተኛ የሆነ መመስጠሪያ ስልተ ቀመር (encryption algorithm ) ይጠቀማል። ይህ ብሮዘሩን ተጠቃሚውን ለማግኘት ወይም ጠለፋ(hacking) ለማድረስ የተወሳሰበ ያረገዋል።

በጥቁር ድር ያሉ #አገልግሎቶች፡

ቦትኔት(botnet)
የብትኮይን አገልግሎቶች
የጥቁር ገብያ
የጠለፋ አገልግሎቶች(hacking Service)
ማጭበርበር አገልግሎቶች
ሽብርተኝነት
አደገኛ እጽ እና ሌሌችም

   ❖ ውድ የ ኑሩ ሳይቴክ ቤተሰቦች ድጋፋችሁን ቻናላችንን ሼር በማድረግ እንድትተባበሩን በትህትና እንጠይቃለን።
Please Give me credit when you make copy paste!
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
የቴሌግራም  ቻናላችን
╔═══════════╗
@nurudish 
@nurudish 
@nurudish 
╚═══════════╝
━━━━━━⊱✿⊰━━━━━━

🇳 🇺🇷 🇺 Sci-Tech
2.3K viewsƝƲƦƲ ሳይቴክ, 07:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-03 10:56:53 የኮምፒውተር ቫይረስ ሰለባ መሆንዎን እንዴት ማወቅ ይችላሉ
1 ድንገተኛ የሆነ የአገልግሎት መቋረጥ፡ ከዚህ ቀደም ድንገተኛ የሆነ የአገልግሎት መቆራረጥ አጋጥሞዎት በተደጋጋሚ ሰማያዊ ቀለም ያለው ገጽታ የሚያሳይ ከሆነ ኮምፒውተርዎ አደጋ ላይ መውደቁን ጠቋሚ ነው፡፡
2. የኮምፒውተር ስርዓት ማዝገም /Slow System/፡ በሲስተምዎ ላይ ብዙ ቦታ የማይፈልጉ መተግበሪያዎችን(applications)
ሳይጠቀሙ የኮምፒውተር ስርዓቱ ዝግ ማለት የኮምፒውተርዎ ስርዓት በቫይረስ መጠቃትን ሊያመለክት ይችላል።
3. ከልክ ያለፈ የሃርድ ድራይቭ እንቅስቃሴ( 3. Excessive Hard Drive Activity) ምንም እንኳን ኮምፒተርዎ ስራ እየሰራ ባይሆንም ጥቂት የማይባሉ የሃርድ ድራይቭ እንቅስቃሴን ካስተዋሉ ይህ ምናልባትም በቫይረስ ስለመጠቃትዎ የማስጠንቀቂያ ምልክት ሊሆን ይችላል፡፡
4. ያልተለመዱ የዊንዶው ምልክቶች ሲስተዋሉ፡ ኮምፒውተርዎን በሚከፍቱበት ወቅት እንግዳ የሆኑ ነገሮች ብቅ ካሉ እና በተለይ በኮምፒተርዎ ላይ የተለያዩ ድራይቭዎች /drive/ ከጠፉ ችግር መፈጠሩን አመላካች ነው፡፡
5. የተለዩ መልእክቶች፡ በተለያዩ መልእክቶች ወደ እርስዎ የመልእክት መለዋወጫዎች ሲገቡ እና ፋይሎችን በሚከፍቱበት ጊዜ ካልተከፈተ የተፈጠረ ችግር አለ ማለት ነው፡፡
6. መጥፎ የፕሮግራም እንቅስቃሴ፡- ፕሮግራሞችዎ ከጠፉ ፣ ከተበላሹ ፣ ወይም ያለ እርስዎ ፍቃድ እራሳቸውን በራሳቸው መክፈት ከጀመሩ ፣ እንዲሁም ያለ እርስዎ ትእዛዝ ኢንተርኔት ለመድረስ እየሞከረ መሆኑን የሚገልጽ ማሳሰቢያ ከደረሰዎ ይህም የቫይረስ ሰለባ መሆንዎን ጠቋሚ ነው፡፡
7. የዘፈቀደ አውታረ-መረብ እንቅስቃሴ /Random Network Activity/ ምንም ጉልህ የሆኑ ፕሮግራሞችን ወደስራ ሳያስገቡ አልያም ከፍተኛ የበይነ-መረብ ዳታን በማይጠቀሙበት ጊዜ የእርስዎ ራውተር በቋሚነት ብልጭ ድርግም የሚል ምልክት የሚያሳይ ከሆነ ፣ የሆነ ችግር መፈጠሩን አመላካች ነው፡፡
8. የተሳሳቱ የኢሜይል መልእክቶች፡- እርስዎ ለማንም ኢ-ሜይል ባይልኩም ከእርስዎ የኢሜይል አድራሻ ለእርስዎ ኢ-ሜይል መልእክት ከደረስዎ የእርስዎ ስርዓተ ኮምፒውተር ተጥሷል (ወይም የኢ-ሜይል የይለፍ ቃልዎ እንደተሰረቀ የሚያሳይ ጠንካራ ማስረጃ ነው)
9. የአይፒ አደራሻዎ በበይነመረብ ፕሮቶኮል አድራሻ በጥቁር መዝገብ ከተቀመጠ/
Blacklisted IP Address/ የእርስዎ የአይፒ አድራሻ በጥቁር መዝገብ መያዙን የሚገልጽ ማስታወቂያ ከደረሰዎት ኮምፒተርዎ በጥሩ ሁኔታ ላይ አለመሆኑን የሚያሳይ ምልክት፡፡
10. ያልተጠበቀ የፀረ-ቫይረስ አገልግሎት መቆም፡- ብዙ ተንኮል-አዘል ሶፍትዌር /malware/ ፕሮግራሞች ፀረ-ቫይረስ አገልግሎት የማስተጓጎል ወይም ከጥቅም ውጪ የማድረግ ተልእኮ በመያዝ የተቀየሱ ናቸው፡፡ ስለሆነም የፀረ-ቫይረስ ስርዓትዎ በድንገት የማይሠራ ከሆነ የኮምፒውተር ስርዓቱ ትልቅ ችግር ላይ መውደቁን የሚያሳይ በመሆኑ የመፍትሄ እርምጃዎችን መውሰድ የግድ ይላል፡፡
2.1K viewsƝƲƦƲ ሳይቴክ, 07:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-02 10:09:34 ሞባይል ዳታ በሚከፈትበት ጊዜ ካርድ ወይም የተሞላውን የዳታ ጥቅል በቶሎ የሚጨርስበት ምክንያትቶችና መፍትሔዎች:

ምክንያቶች :-
1.የሞባይል ዳታ ተከፍቶ ሲረሳና ሳይዘጋ ሲቀር
2.ኢንተርኔት ክፍት ሆኖ ከተለያዩ ደህረ ገፆች ላይ ቀጥታ ቪዲዮች ሲታዩ
3.System settings እና Applications በራሳቸው ጊዜ አፕዴት ሲያደርጉ
4.በሞባይሉ ላይ የሚገኙ አፕሊኬሽኖች ተጠቃሚው በማያቸው መንገድ ከበስተጀርባ ሲሰሩ
5.በሞባይል ስልኩ ውስጥ ቫይረስ ሲኖር
---------------------------
መፍትሔዎች :-
ሞባይል ዳታ ተከፍቶ ሲረሳና ሲቆይ እንደ ሶሻል ሚዲያና ኦንላይን የሚሰሩ አፕሊኬሽኖች ከተጠቃሚው እይታ ውጪ ስራቸውን ያከናውናሉ። በዚህ ጊዜ በሞባይሉ ላይ የተሞላው ክሬዲት ሰዓት ይቀንሳል ወይም ያልቃል ስለዚህም ኢንተርኔት ተጠቅመው ከጨረሱ በኋላ የሞባይሉን ዳታ ያጥፉ።

በሞባይል ዳታ ኢንተርኔት ከፍቶ ከተለያዪ ድህ ገፆች ላይ በቀጥታ ቪዲዮ መመልከት የተሞላውን ካርድ መጠን በጊዜ ከሚያሳጥሩት ነገሮች ወስጥ አንደኛው ሲሆን ለዚህም ዋነኛው
ምክንያት በኢንተርኔት ቪዲዮ ቀጥታ መመልከት የሚቆጥረው የዳታ መጠን ከፍተኛ ስለሆነ ነው ስለዚህ ቪዲዮ ማየቱ ግዴታ ከሆነ በ Vidmate እና በሌሉች ቪዲዮ ዳውሎደር አፕሊኬሽኖች የቪዲዮ ይዘት በመቀነስ ጭኖ መመልከቱ ወጪን
ይቆጥባል።

System settings እና Application በራሳቸው ጊዜ አፕዴት ሲያደርጉ የተሞላውን ዳታ(ካርድ) ይወስዳሉ ታዲያ ይህን ለማስቀረት Free wifi ከተገኘ አፕዴት ማድረግ ይህ ማድረግ የማይቻል ከሆነ system settings አፕዴት እንዳያደርግ ማስቆም:
Settings ----About----Software Update---
Automatic update የሚለውን ማጥፋት
Applications አፕዴት እንዳያደርጉ ከተፈለገ ደግሞ
-Google Play መክፈት.
- hamburger የሚመስለውን በለ ሶስት ሆሪዞንታል ምልክት ያለበትንም አናት ላይ በስተግራ በኩል Settings በመንካት
Auto-update apps.- disable automatic app updates, የሚለውን በመክፈት እና በመምረጥ መዝጋት
ይቻላል

በሞባይሉ ላይ የሚገኙ አፕሊኬሽኖች ተጠቀሚው በማያቸው መንገድ ከበስተጀርባ ሲሰሩ ከእይታ ውጪ በመሆን የክሬዲት መጠን ይቀንሳሉ ታዲያ ይህን ለመከላከል:
Settings----
data usage ---Restricted Background data
የሚለውን መክፈት... ከዚህ ይበልጥ ደግሞ Mobile data
saver አፕሊኬሽኖች በመጫን መጠቀም

በሞባይል ሰልክ ውስጥ ቫይረስ ሲኖር የተሞላውን ሞባይል
ዳታ ከመቅስፈት እድሜው እንዲያጥር ያደርጋል ብሎም ቫይረሱ በራሱ ጊዜ የሞባይሉን ኦፕሬቲንግ ሲስተም በማዘዝ ያለማንም ትዕዛዝ ዳታ ይከፍታል ዳውንሎድ ያደርጋል አላስፈላጊ ነገሮችና ማስታወቂያዋች ይለቃል ከዚህም የተነሳ በፍጥነት የሞባይል ካርድ( ዳታ ጥቅል) ይጨርሳል ይህ ነገር በሞባይሉ ላይ ቢከሰት አንቲ ቫይረስ በመጫ ሰካን ማድረግ ይህ መፍትሔ የማይሆን ከሆነ ለባለሙያ ማሳየቱ ተገቢ ነው::

መረጃዎች ቶሎ ቶሎ እንዲደርሳችሁ ቻናላችንን #Mute ያደረጋችሁት #UNMUTE በማድረግ ተባበሩን "

የዩቲዩብ ቻናላችንን Subscribe በማድረግ የቴክኖሎጂ እውቀትዎን ያሳድጉ!



https://www.youtube.com/channel/UCr1PSR41Dom6j2qYe80LxjQ?

▬▬▬ Share ▬▬▬▬
2.2K viewsƝƲƦƲ ሳይቴክ, 07:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-01-31 14:42:46 #አሮጌ_ስልክን_እንደ_ሴኩይሪቲ_ካሜራነት_እንዴት_መጠቀም_እንችላለን?

አዲስ ሞባይል ስልክ ስንገዛ አሮጌው ስልክ ይቀመጣል(ካልሸጥነው)። ነገር ግን አሮጌውን ስልክ እንደ ሴኩሪቲ ካሜራነት ልንጠቀምበት እንችላለን።

ለምሳሌ አንድ ጨቅላ ህፃን ያላት እናት ልጇን ቤት ለሰራተኛ ትታ ወደ ስራ ስትሄድ ትጨነቃለች። ስራ ላይ ሆኗ "ልጄ እንዴት ይሆን..." እያለች ስትጨነቅ ትውላለች። ነገር ግን አሮጌ ስልክ ካላት አሮጌውን ስልክ ቤት አንድ ጥሩ ቦታ ታስቀምጠውና አሁን በምትጠቀምበት ስልኳ አማካኝነት ስራ ቦታዋ ሆና የልጇን ሁኔታ መከታተል ትችላለች። ይህ ብቻ አይደለም ቤቷ ማን መጥቶ እንደነበረ፣ቤቷ ውስጥ ምን እየተካሄደ እንደሆነ መከታተል ትችላለች።

ይህ አንድ ምሳሌ ነው። አሮጌው ስልክ ሴኩሪቲ ካሜራ በማድረግ ለተለያዩ ጉዳዬች ልትጠቀሙበት ትችላላችሁ።

እንዴት? ቀላል ነው። እነዚህን ስቴፖች በመከተል አሮጌውን ስልክ ሴኪዩሪቲ ካሜራ ማድረግ እንችላለን።

1ኛ፦ Seecitv የሚል አፕሊኬሽን አለ። ነፃ ነው።ይህንን አፕሊኬሽን ሁለቱም ስልኮች(አሮጌው እና አዲሱ) ላይ እንጭነዋለን።

የአፕሊኬሽኑ ሊንክ ይሄው፦ https://play.google.com/store/apps/details?id=com.code.bluegeny.myhomeview

2ኛ፦ አፕሊኬሽኑ ዳውንሎድ አድርጎ ሲጨርስ #Start ላይ ክሊክ ማድረግ።ከዚያም #Viewer የሚለውን መምረጥ። በመጨረሻ #Next የሚለውን ክሊክ ማድረግ ።

3ኛ፦ 2ኛውን ስቴፕ ስትጨርሱ "Sign in with google" የሚል ይመጣል።በጎግል አካውንታችሁ Sign in ማድረግ

4ኛ፦ 2ኛ ስቴፕ ላይ የተጠቀሱትን አሮጌው ስልክ ላይም ታደርጋላችሁ። ነገር ግን አዲሱ ስልክ ላይ #Viewer ብለን መርጠናል።አሁን አሮጌው ስልክ ላይ #Camera የሚለውን እንመርጣለን

5ኛ፦ በቃ አለቀ።አሁን አሮጌውን ስልክ አንድ ጥሪ ቦታ መርጦ ማስቀመጥ።

የቴሌግራም ቻናላችን https://t.me/nurudish
Via dotcomshow
2.7K viewsƝƲƦƲ ሳይቴክ, 11:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-01-26 23:30:57 የባትሪ እድሜ (Battery life)

በዚህ ዘመን በርካቶች የዘመናዊ ተንቀሳቃሽ ስልክ ተጠቃሚዎች መሆናቸው ይታመናል። ዘመናዊ ስልኮች ከስሪታቸው አንጻር ባትሪያቸው ቶሎ የሚያልቅና አጭር ጊዜን የሚያስጠቅሙ ናቸው። ከዚህ አንጻርም ተጠቃሚዎች ባትሪውን ቶሎ ቶሎ ሃይል ለመሙላት (ቻርጅ ለማድረግ) ሲሞክሩ ይስተዋላል። ይህ ሁኔታ ደግሞ ምናልባትም የባትሪን እድሜ ሊያሳጥር እና ሙሉ በሙሉ ሊያበላሸውም ይችላል።

ስልክን ከመጠቀም ባለፈ ግን የባትሪ እድሜን ማራዘምና በአግባቡ ቻርጅ በማድረግ መጠቀም ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ ነው። እርስዎ ከእነዚህ ተጠቃሚዎች አንዱ ከሆኑ ስልክዎን ቻርጅ በሚያደርጉበት ጊዜ ምናልባት ያላስተዋሏቸው ነገሮች ይኖራሉና እነዚህን የባለሙያ ሃሳቦች እናካፍልዎ፡

ቻርጅ እያደረጉ ስልክን በጭራሽ አለመጠቀም፦

አንዳንድ ጊዜ አስቸኳይ ጉዳይ ቢያጋጥም እንኳን ስልክን ቻርጅ እያደረጉ ባይጠቀሙ ይመረጣል። ምናልባት የግድ ከሆነ ደግሞ ስልኩ ከተሰራበት ኩባንያ አብሮ የተዘጋጀን ቻርጀር እየተጠቀሙ ቢሆን ይመረጣል ይላሉ ባለሙያዎች።

ጥራት ያላቸውን ባለማራዘሚያ ቻርጀሮች መጠቀም፦

ባለማራዘሚያና በአብዛኛው በነጭ መደብ የተሰሩ እውነተኛ ቻርጀሮችን መጠቀም የባትሪን እድሜ ለማራዘም ይረዳልና ይጠቀሙበት።

ሌሊቱን ሙሉ ቻርጅ ከማድረግ መቆጠብ፦

ወደ መኝታ ሲያመሩ ስልክዎን ቻርጀር ላይ ሰክቶ መተው አደጋ አለው። ይህም ባትሪው ከመጠን በላይ ቻርጅ በማድረግ ማዳከም ይጀምራል፥ በአብዛኛው ስልክን በ40 እና በ80 ፐርሰንት መካከል ቻርጅ ማድረግ መልካም መሆኑንም ይመክራሉ። ምክንያታቸው ደግሞ 40 ፐርሰንት ከደረሰ ቻርጅ ማድረጉ ግዴታ ሲሆን 80 ከሆነ በኋላ ነቅለው ቢገለገሉበት ችግር የለውም የሚል ነው።

ስልክን ለተወሰነ ጊዜ ማጥፋት፦

ሰው ሰርቶ ማረፍ እንደሚፈልገው ሁሉ ስልክን ማጥፋትም ለባትሪው መልካም እንደሆነ ነው ባለሙያዎች የሚገልጹት። ለዚህ ደግሞ ቢያንስ በሳምንት አንድ ቀን በተለይም ወደ መኝታ ሲያመሩ በማጥፋት እረፍት መስጠት። ይህ ሲሆን ደግሞ የስልኩ ባትሪ እድሜ እንዳያጥርና ረዘም ላለ ጊዜ እንዲያገለግልዎ ይረዳል።

ባትሪው እስከሚያልቅ ጠብቆ ቻርጅ አለማድረግ፦

ሌላውና በብዙ ሰዎች የተለመደው ጉዳይ ደግሞ የስልክ ባትሪ እስከሚያልቅ ጠብቆ ቻርጅ ማድረግ ነው። ይህ ደግሞ ለባትሪ እድሜ የመጀመሪያውና ዋናው ጠር ነውና ባትሪው 40 ፐርሰንት ላይ ሲደርስ ቻርጅ ማድረጉን ይመክራሉ። ይህ ባይሆን እና በጣም ከወረደ በኋላ ቻርጅ ለማድረግ መሞከሩ ግን ባትሪን በመግደል ከፍተኛ ጉዳት ያስከትላልና ይህን ልማድ ያስወግዱም ይላሉ።

ከዚህ ባለፈም ቻርጀሩን ከቀጥተኛው ሶኬት ላይ አለመሰካት እና ከፍተኛ ሙቀት ባላቸው ቻርጀሮች አለመጠቀም መልካም ነው። እርስዎም ከላይ የተጠቀሱትን የባለሙያ ምክረ ሃሳቦች በመተግበር የስልክዎን ባትሪ እድሜ ያራዝሙ።
3.3K viewsƝƲƦƲ ሳይቴክ, 20:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-01-21 09:06:55 የኢሜል password ብንረሳዉስ ?
የኢሜል ፓስዋርዳችሁ ከጠፋባችሁ ከዚህ በታች ያሉትን እስቴፖች በመከተል የጠፋባችሁን የኢሜል ፓስዋርድ
አጥፍታችሁ #reset በማድረግ በአዲስ መቀየር ትችላላችሁ ።

ይከከን ማስፈንጠሪያ

https://accounts.google.com/signin/recovery

ተጭናችሁ ወደ #Google account recovery ፔጅ ግቡ።

ፖስዋርዱ የጠፋባችሁን ኢሜል አድራሻ (email address) አስገብታችሁ #forget password የሚለዉን በተን ተጫኑ።

የምታስታዉሱትን የ ኢሜል ፓስዋርድ እንድታስገቡ ይጠይቃችሗል።

እዚህ ላይ ያስታወስችሁትን የጠፋዉን ፖስዋርድ አስገቡ እና #Next የሚለዉን በተን ተጫኑ።

ብትሳሳቱም አትጨነቁ አካዉንታችሁን አይዘገሠዉም።

ከዛ #Google የሜረጋገጫ #Verification code
ኢሜሉን ስትከፍቱ ባስገባችሁት ስልክ ቁጥር ይልክላችሗል።

በምን ይልካል?

#Text or Call የሚል ሲመጣ የሚፈልጉትን የመቀበያ መንገድ ይምረጡ።

የተላከላችሁን ባለ 6 #digit የማረጋገጫ ኮድ አስገቡ።

ከዛ አዲስ ፖስዋርድ እንድታስጋቡ ይጠይቃችሗላ።

የፈለጉትን ፖስዋርድ እና ኮንፌርሜሽን ፓስዋርድ(መጀመሪያ ያስገባችሁትን ደግማችሁ አስገቡ) አስገብታችሁ
#Next የሚለዉን ሲጫኑ የጠፋዉ ፖስዋርድ በአዲስ ፓስወርድ ተቀየረ ማለት ነዉ።


በነገራችን ላይ ፖስዋርዳችሁን እስልካችሁ #Note book ላይ ብትጽፉት አሪፋ ነዉ ያዉ ደሞ እንዳይጠፉ ።

የዩቲዩብ ቻናላችንን Subscribe ያድርጉ



https://www.youtube.com/channel/UCr1PSR41Dom6j2qYe80LxjQ?
3.7K viewsƝƲƦƲ ሳይቴክ, 06:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-01-18 10:19:07 በስልካችን ኢንተርኔት በምንጠቀምበት ሰዓት ብዙ ብር እየወሰደ ካስቸገሮት ይሚከተለውን መፍትሄ ያንብቡ። ያነበቡትንም ለሌሎች ያጋሩ።
****  ሼር ማድረግ አይርሱ!!
*
መጀመሪያ የስልኮን በመክፈት Setting  Connection ( Wireless and networks) ከሚለው ስር Data usage የሚለው ውስጥ ስንገባ ኢንተርኔት በጣም የሚጠቀሙ አፕሊኬሽኖችን በደረጃ ተዘርዝረው ያገኟቸዋል። ሁሉንም አፕ በየተራ ይክፈቷቸው። Foreground (ከፍተው የተጠቀሙት) እና Background (ሳይታዩ አፕሊኬሽኑ በራሱ የተጠቀመው) ምን ያህል Mega Bytes እንደሆነ ይነግረናል፤ ከታች ደግሞ Limit background process የሚል አማራጭ አለ። ከእሱም ፊት ያለውን [ √ ] በማድረግ ካለ እኛ ፈቃድ አፑ ኢንተርኔት እንዳይጠቀም መከልከል እንችላለን። ወደ ሗላ እየተመለስን ሁሉንም Data usage ውስጥ የተዘረዘሩ አፖች እየከፈትን መዝጋት (Limit) ማድረግ የሚወስድብንን ብር መቀነስ እንችላለን። በተጨማሪም ሁሌም አዲስ አፕ በጫን ቁጥር እየገባን መዝጋት ይኖርብናል።
አንድሮይዳቸው ከ 4.0 በታች ለሆኑ Data usage የላቸውም፣ በዚህ ምትክ Setting  Accounts and Sync ገብተን Background data የሚለውን አለመምረጥ ።
በተጨማሪም Setting  Privacy የሚለውን በመክፈት Back up my data የሚለውን እንዲሁ አለመምረጥ።
ለHuawei ስልኮች Data usage
ለመግባት፣ Setting  wireless & Networks  more..  Data Usage ->
Restrict background data የሚለውን [ √ ] በማድረግ መምረጥ
Setting -> personal ከሚለው ስር Location access የሚለው ውስጥ ገብተን እሱን መዝጋት።
ይሄም ስልካችን ያለንበትን ቦታ ለማወቅ ኢንተርኔት እንዳይጠቀም ያደርጋል።
Setting -> Developer option (About phone ከሚለው ከፍ ብሎ ያገኙታል) የሚለውን ከፍተን ወደ ታች ስንወርድ Background Process limit የሚለውን እንክፈት። ይሄ ሁሌም ስልኩ በራሱ Standard Limit የሚለውን ይመርጠዋል። እዚህ ላይ No background process የሚለውን እንምረጥ። ሁሌም ስልካችንን አጥፍተን ካበራነው በራሱ ወደ Standard limit ስለሚቀየር እየገባን መቀየር ይኖርብናል። Standard Limit ላይ ከሆነ ቢያንስ እስከ 10 አፕሊኬሽኖች ያለ እኛ ፈቃድ ኢንተርኔት ጋ ይገናኛሉ ማለት ነው። ይሄም ከፍተኛ ገንዘብ ይወስዳል።
Developer option የሚለውን Setting ውስጥ ካጡት
የሚከተለውን ያድርጉ። Setting  About phone የሚለው ውስጥ እንግባና Build number የሚለውን 7 ጊዜ በፍጥነት እንካው። ከዚያ ሲመለሱ Setting ውስጥ About Phone ከሚለው ከፍ ብሎ Developer option ያገኙታል።
የስልካችን ሶፍትዌር ራሱን እንዳያድስ (update) መዝጋት።
ለዚህም Setting  About phone (device)  Software update ገብተን Auto update የሚለው
የተመረጠ ከሆነ [√] እሱን ማንሳት ወይንም አለመምረጥ።
GPS መዝጋት.
ኢንተርኔት ክፍት እንዳደረግን ኢንተርኔት የማይጠይቁ አፖችን (ጌም) አለመጠቀም። ይሄም አፖቹ ከአምራቻቸው ጋ በመገናኘት ፣ ማስታወቂያ እንዲመጣ በማድረግ የሚጠቀሙትን ኢንተርኔት ያስቀራል።
Play store በ Wi–fi ካልሆነ በስልካችን ኢንተርኔት አለመግባት።
Opera Mini የምንጠቀም ከሆነ Opera Setting ውስጥ Image quality የሚለውን Low quality ማድረግ። ይሄም ኦፔራ ፈጣን እንዲሆን እና ብዙ ገንዘብ እንዳይወስድ ያደርጋል።

የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ  https://t.me/nurudish
3.6K viewsƝƲƦƲ ሳይቴክ, edited  07:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ