Get Mystery Box with random crypto!

ƝƲƦƲ ሳይቴክ

የቴሌግራም ቻናል አርማ nurudish — ƝƲƦƲ ሳይቴክ Ɲ
የቴሌግራም ቻናል አርማ nurudish — ƝƲƦƲ ሳይቴክ
የሰርጥ አድራሻ: @nurudish
ምድቦች: እውነታው
ቋንቋ: አማርኛ
ሀገር: ኢትዮጵያ
ተመዝጋቢዎች: 8.06K
የሰርጥ መግለጫ

ይህ ቻናል ፈጠራዎችን ፣ መረጃዎችን በአማርኛ& English፣የቴክኖሎጂ እውነታዎችን ፣ የወደፊቱን ቴክኖሎጂ እና የአይቲ ምክሮችን በማካተት የቴክኖሎጂ ዓለምን ያቀርባል፡፡
በተጨማሪም፦ ዌብሳይት በተመጣጣኝዋጋ እንሰራለን
🔷 ማህበራዊ ሚዲያን ለእውቀት ብቻ እንጠቀምበት !
🔺 ጥያቄ እና አስተያየት ካለ በዚህ ስልክ ያሳውቁን! 251945686310

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2021-01-06 10:15:35 የተዘጉ ስልኮችን መክፈት ማለት ምን ማለት ነው?
መፍትሄ 1

PART ONE
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

የተዘጉ ስልኮችን መክፈት ማለት ምን ማለት ነው?
Network ሰጪ ድርጅቶች በመላው አለም ላይ ይገኛሉ። በሀገራችንም ethio telecom ይገኛል። በሌሎች ሀገራት ደግሞ ከ አንድ በላይ network አቅራቢ ድርጅቶች ሊኖሩ ይችላሉ። ይህም የሆነበት ምክንያት በመንግስት ስር ሳይሆን በግል ተቋማት ስር ስለሆኑ ነው።ለዚህም ጎሮቤታችን Kenya ጥሩ ማሳያ ናት። ከአንድ በላይ የመኖሩ ጥቅም ህዝቡ የተሻለ አማራጭ ያገኛል ድርጅቶቹም የተሻለ ነገር ለማቅረብ ፉክክር ዉስጥ ይገባሉ። አንድ አንድ network ሰጪ ድርጅቶች ደግሞ አለም አቀፍ እውቅና አላቸው።
ለምሳሌ T-mobile, verizon, orange, vodafone.....
እነዚህ ድርጅቶች ከሚፎካክሩቸው መንገዶች አንዱ ደንበኞችን ለመሳብ ሲሉ የስልክ ቀፎዎችን በቅናሽ ዋጋ ያቀርባሉ። ይህን የሚያደርጉት ደንበኞቻቸው የአየር ሰአት በገዛቸዉ ቁጥር ተጠቃሚ ስለሚሆኑ ነው። ነገር ግን በዚህ መንገድ የተገዙ የስልክ ቀፎዎች ከተገዙበት የnetwork ሰጪ ተቋማት ውጪ ያሉ sim cardoችን አይቀበሉም ይህም ምክንያቱ በ security code ስለሚቆለፉ ነው። እንደዚህ አይነት ስልኮች ሀገር ስለቀየሩ ሳይሆን እንቢ የሚሉት ከተገዙበት የ network ሰጪ ድርጅት ዉጪ ባሉ network ሰጪ ድርጅቶች sim card ስለማይሰሩ ነው።

የተዘጉ ስልኮች የሚከተሉትን ምልክቶች ያሳያሉ።
Sim not valid, wrong sim,unknown sim, phone restricted, contact service provider.....

ከ network ሰጪ ድርጅቶች የተገዛ ስልክ ለመክፈት ሁለት መንገድ አለ።

1. Computer , flasher box, እና flasher file በመጠቀም መክፈት ይቻላል።
ይህ ዘዴ አሁን ላይ ethio telecome የሚዘጋቸውን ስልኮችንም ይመለከታል ነገር ግን በዚህ Method ለመክፈት Computer, flasher box እና flasher file ያስፈልገናል።
ስለ Computer ማብራራት አያስፈገኝም ነገር ግን በዚህ Method ትንሽ አሸጋሪ የሚሆነው Universal flasher box ማግኘት ነው ይሄ box የተለያዩ ጥቅሞች ሲኖሩት ከዚህም ውስጥ በስልኩ ሞዴል የራሱን flasher file ከ Google ላይ በማወረድ ከስልኮቻችን ጋር በማገናኘት የትኛውንም ስልክ ማስተካከል እንችላለን ከ hardware ውጪ ምንም አይነት ችግሮችን እንድናስተካክል ያስችለናል።
ይህ universal flasher Box orginale ስልኮችን IMEI create በማድረግ አሁን ላይ ላለው ethio telecome ለሚዘጋቸው ስልኮች ፍቱን መድሃኒት ሲሆን የ flasher box ዋጋ በ Ethiopia 4326birr አከባቢ ሲሆን የተወሰኑ ሞባይል ቤቶች በ addis abeba እየተጠቀሙበት ይገኛሉ።
ለምሳሌ ለመጠቆም ያህል መርካቶ ይርጋ ሃይሌ building ላይ በኛ በኩልም ይህን flasher box ማግኘት ይችላሉ።

2. ለ ድርጅቱ መጠነኛ ክፍያ በመፈጸም ማስከፈት ሲሆን:-
ለምሳሌ iphone በ icloud የተዘጉ ስልኮችን መጥቀስ ይቻላል እንደዚህ አይነት ስልኮች የ e-commerce እንዲሁም credit card ይጠይቃሉ። ይሄ አገልግሎት ደግሞ እኛ ሀገር ስለሌለ ያለው አማራጭ ውጭ ሀገር በምናቀው ሰው ማስከፈት ነው። ይህ ማለት ድህረ ገፁ ላይ ግብተን የስልኩን ሞዴል ስናስገባ ክፍያ ይጠይቀናል ክፍያውም የሚከናወነው በ ማስተር ካርድ ስለሆነ ክፍያውን ውጪ ሃገር ማስተር ካርድ ባለው ሰው ከባላንሱ ላይ እንዲፈፅምልን በማድረግ ክፍያው ከተፈጸመላቸው ድርጅቱ ኮዱን በሚያስገባው Email አድሬስ ስለሚልክልን ወድያውኑ መክፈት ይቻላል።
በ icloud የተዘጉ ስልኮች በማስተር ካርድ በ አሁን ጊዜ የሚያስከፈለው 104$ ዶላር ነው ለዚህም ነው በአዲስ አበባ በተለያዩ የ ሞባይል ቤቶች በተለይ መርካቶ ላይ ከ200$ ዶላር በላይ የሚጠይቁት ጥቅማቸውን በማሰብ ማለት ነው። እዚህ ላይ ማስተዋል ያለባችሁ ውጪ ሃገር ላይ የ ማስተር ካርድ ቪዛ ኮዱን አስገብቶ ክፍያውን ሊፈፅምላችሁ እና በ Email የሚላክለትን Code ሊልክላችሁ የሚችል ወዳጅ ከሌላችሁ ምንም አይነት አማራጭ የላችሁም ከ200$ ዶላር በላይ ከፍለን ከማስከፈት ውጪ ስልኩን መጠቀም አንችልም።
በ i Cloud ያልተዘጉ ስልኮችን እና እንዲሁም የተወሰኑ icloud locked የሆኑ iphone ስልኮችን DNS method በመጠቀም መክፈት የምንችልበትን ዘዴ ሰፋ ባለ Program ከዚህ በፊት አቅርበንላችኋል ወደኋላ በመመለስ Check ማድረግ ትችላላችሁ።

መፍትሄ 2

PART two
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

ይሄ መንገድ ስላካችንን በመጀመሪያ ሩት ማድረግ ይጠበቅብናል። ስለ ሩት ከዚህ በፊት Post ላይ ማብራሪያ ስለሰጠን ከዛ ላይ ገብተው ያንብቡ። ሩት የሆነ ቀፎ ካለን እንደሚከተለው በማድረግ imei መቀየር እንችላለን ።

ይህን ዘዴ ለመጠቀም ሁለት ፕሮግራሞች እንጠቀማለን የመጀመሪያው:-

1.Mobileuncle MTK IMEI Write Tool የሚለውን ሶፍትዌር ኮምፒውተራችን ላይ ዳውንሎድ እናደርጋለን ከዛ በዚፕ ያለውን ፕሮግራም ስንከፍት የሚያመጣልን ዊንዶው ላይ Y ብልን ፅፈን enter እንጫናለን ከዛ የሞባይላችንን imei እንፅፍና
create IMEI .BAK ብለን አዲስ የተፈጠረውን imei.bak ፋይል ወደ ሜሞሪ ካርድ እንልከዋለን።

ሜሞሪ ካርዱን ቀፎ ውስጥ ካስገባን በኋላ...

2.ይህን አፕሊኬሽን ቀፏችን ላይ እንጭናለን mobileuncle_MTK_toolv2.9.9.apk

3.ከዛ የጫነውን አፕሊኬሽን ስንከፍት ሩት ኣክሰስ ጥያቄ ሲጠይቅ grant ብለን ፍቃድ እንሰጠዋለን።

ከዛ IMEI backup and restore የሚለውን ከፍተን ,restore IMEI.bak. ስንል ቅድም ሜሞሪ ላይ ያስቀመጥነውን ፋይል ወደ ቀፏችን ይፅፍልናል።

ሲጨርስ ቀፏችንን Restart አድርገን መደወያው ላይ *#06# አስገብተን በትክክል መፃፉን እናረጋግጣለን።
ነገር ግን ሚሞሪ የማይወስዱ ስልኮች እና የተወሰኑ ሞባይሎች ለምሳሌ iphone...etc በmobile Uncle tools ImEI backup restore የሚለው not supported ካላችሁ ከላይ ለመግለፅ እንደሞከርንው በ method one የሚከፈቱ ስለሆኑ የግድ Flasher box መግዛት ይጠበቅባችኋል።


የዩቲዩብ ቻናላችንን Subscribe በማድረግ የኤሌክትሮኒክስ ጥገናዎችን ይማሩ



https://www.youtube.com/channel/UCr1PSR41Dom6j2qYe80LxjQ?

▬▬▬ Share ▬▬▬▬
3.1K viewsƝƲƦƲ ሳይቴክ, 07:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-01-04 15:42:40 አይ ሲ ማለት ምን ማለት ነው ? ከሞባይል ጋርስ ምን ያገናኛዋል?
አይ ሲ ማለት ብዙ ኮመፖነቶች የሚገኙበት ክፍል ነው::
በውሰጡም Resistor capacitor inductor diode ሌሎቹም ኮምፖነቶች ሊኖሩበት ይችላሉ::
የአይሲ ስራው ብዙ ነው ብቻ ኮምፖነቶችን በመሰብሰብ አንድና ክዛ በለይ የሆነን ስራ ይሰራልናል ለምሳሌ ሞባይል ላይም ሆነ ቲቪ ላይ ኦዲዬ አይ ሲ፣ ፓወር አይሲ እና ሌሎች አይሲወች ይኖራሉ:: እነዚህ አይሲዎች የራሳቸው ስራ አላቸው ለምሳሌ ፓወር አይሲ የፓወርን አክቲቪቲ ይቆጣጠራል ኦዲዬ አይሲ ደሞ የኦዲዬ አክቲቪቲ ይቀጣጠራል ስለ አይሲ ይህን ካለን ይበቃናል ወደ ሞባይል ስንገባ ሞባይል ላይም አይሲዎች በብዛት ይገኛሉ::
ማንኛውም ሞባይል ማለትም ሞባይል ከተፈጠረ ጀመሮ እስካሁን ያሉት ሞባይል 9 አይ ሲች አሉት ከድሮ ዳስተር ሞባይል አንስቶ እስከ አይፎን 6+ ደርስ ካሁን በሆላም ለሚፈጠሩት ስልኮች 9 አይሲዎች አሉት ዘጠኙ አይሲ ደሞ ለ3 እንከፍላቸዋለን
1 ) power and logic part ላይ (6 ic)
2) transmition part of ላይ (2 ic)
3) reception part of ic ላይ (1 ic)
4) power and logic part of ic
5) cpu ic (central processing unit )
ሲ ፒ ዩ ማለት የሞባይላችን ሁሉንም እንቅስቃሴ የሚቆጣጠር የሞባይል አይሲ ነው በአጭሩ የሞባይላችን አእምሮ ይባላል
*የሲፒዩ መበላሸት
Dead phone ,no net work ,no audio out put and
etc….
*እንዴት መጠገን ይቻላል?
አይሲውን ማሞቅ ወይም መለወጥ
* የሲፒዩ ቦታ
በኖኪያ እና በሳምሰንግ ላይ አይሲው በወርቃማ ፍሬም ተከቦ ይገኛል በቻይና ስልክ ደሞ እላዩ ላይ M ወይም speed trum ተብሎ ይጻፍበታል
6) memory ic
ሚሞሪ አይሲ ዳታ እስቶሬጅ ዲቫይስ ነው ለሁለት ይከፈላሉ
a) ROM ( read only memory ) it is permanent data storage ሮም ማለት የስልካችን ዋናው ፕሮግራም ወይም operating system የሚቀመጥበት ማለት ነው buraakiller
* የሮም መበላሸት
Dead phone, black or white screen, dim light
እንዴት መጠገን ይቻላል?
ሶፍትዌሩን ስንጠግን - ፍላሽ ወይም ፎረማት
ሃርድውሩን ስንጠግን - አይሲውን ማሞቅ ወይም መለወጥ
* የሮም ቦታ
ሮም ኖኪያ እና ሳምሰንግ ላይ ብዙ ጊዜ የሚገኘው ከሲፒዩ አጠገብ ነው እና የአይሲው ቅርጽ ሁሌም rectangle ነውይገኛል square ያልሆነ ቻይና ላይ ደግሞ ከሲፒዩ ጋር አብሮ buraakiller
b) RAM (randomly access memory) it is
temporary data storage ራም ማለት የስልካችን ሚሴጅ ኮንታክቶች ሚስኮሎች ሌሎችም ልንደልታቸው የምንችላቸው ነገሮች የሚቀመጥበት ነው
* የራም መበላሸት
No miscall. no dilledcall. no received call . no store photo and music etc…
*እንዴት መጠገን ይቻላል?
ሶፍትዌሩን ስንጠግን - ፍላሽ ወይም ፎረማት
ሃርድውሩን ስንጠግን - አይሲውን ማሞቅ ወይም መለወጥ
* የራም ቦታ ሮም ኖኪያ እና ሳምሰንግ ላይ ብዙ ጊዜ የሚገኘው ከሲፒዩ አጠገብ ነው እና የአይሲው ቅርጽ ሁሌም rectangle ነው square ያልሆነ ቻይና ላይ ደግሞ ከሲፒዩ ጋር አብሮ ይገኛል *note ---- ኖኪያ ስልክ ለይ 1 እሰከ 5 ሮም እና ራም አይሲዎች ይገኝሉ በብዛት ከሮም ራም ያንሳል ልላው ደግሞ ለሰፒዩ በጣም የሚቀርበው ሮም ነው ራም ደግሞ በሳይዝ ከሮም ያንሳል ራም እና ሮም ሚቀመጡበት ቦታ ከኮምፖነት የጸዳ ነው
3) POWER IC
ፓወር አይሲ ዋናው ስራ ከባትሪ ቮለቴጅ ተቀብሎ ለተለያዩ አይሲዎች ፓወር መስጠት ነው
ለምሳሌ ከባትሪ 3.7 ቮልቴጅ ይቀበልና ለሲፒዩ 1.5 ቮልቴጅ ለሚሞሪ አይሲ ደግሞ 2.8ቮልቴጅ ያከፋፍላል
*የፓወር አይሲ መበላሽት
Dead phone ,no net work ,no audio out put and etc….
*እንዴት መጠገን ይቻላል?
አይሲውን ማሞቅ ወይም መለወጥ
***የፓወር አይሲ ቦታ
በኖኪያ ስላክ ለይ ለሁለት ዕንከፍለዋለን
a) የድሮ ኖኪያዎች ከሆኑ ማለትም 1st generation ከሆነ ብቻ ፓወር አይሲ ለብቻው ተነጠወሎ እናገኘዋለን ከአጠገቡም RTC የተባለ ኮሞፖነት እናገኛለን::
b) አሁን የሚገኙ ኖኪያዎች ደግሞ አራት አየሲዎች በአንድ አይሲ ተጠቃለው ይገኛሉ የዚ አይሲ ስም UEM(universal energy management) ይባላል እዚ አይሲ ላይ አራት አይሲዎች ይገኛሉ እነሱም Power ic, audio ic, charge ic, ui ic ይገኛሉ ይሄ አይሲ የምነለየው RTC አጠገቡ በመኖሩ ነው::
ቻይና ስልክ ላይ ደሞ አሁንም ልክ እንደ ሚሞሪ አይሲ ከሲፒዩ ጋር አብር ይገኛል ብቻ ሁሉም ስልክ ላይ RTC የተባለው ኮምፖንት አብሮት ይገኛል ጥያቄ ካለ ኢንቦክስ አድርጉልን::

ቴሌግራማችን https://t.me/nurudish/
3.2K viewsƝƲƦƲ ሳይቴክ, 12:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-01-01 10:44:32 ኦንላይን ትምህርት የሚሰጡ ምርጥ ዌብሳይቶች

#ሼር_ይደረግ

እድሜያችን 9 ይሁን 95 ኢንተርኔት ተዝቆ የማያልቅ ስፍር ቁጥር የሌለው እድሎችን ይሰጠናል፡፡ ከተጠቀምንበት፡፡

ትምህርትን በተመለከተ ኢንተርኔት ለተማሪዎች በጣም ብዙ የመማር እድሎችን ይዟል፡፡ከታሪክ እስከ ኮምፒውተር ሳይንስ የትምህርት ዘርፎች ላይ #ኦንላይን_ትምህርት የሚሰጡ #ዌብሳይቶች አብዛኛዎቹ ነፃ ናቸው፡፡

ከነዚህ #ኦንላይን_ትምህርት ከሚሰጡ #ዌብሳይቶች መካከል ታዋቂ የሁኑትን ላስተዋውቃችሁ፡፡

1ኛ፦Coursera.org

ይህ #Coursera ዌብሳይት ከ200 በላይ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር በጋር የሚሰራ ምርጥ የኦንላይን ትምህርት ዌብሳይት ነው፡፡
ለምሳሌ፡፡ ILLINOIS university, Duke University, Google,University of Michigan,IBM, Imperial College London,Stanford,University of Pennslavania እና የመሳሰሉ ትልልቅ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር በጥምረትና በጋራ የሚሰራ ዌብሳይትነው፡፡

o ከ3,900በላይ ኮርሶችና ስፕሺያላይዜሽኖች፤ከ13 በላይ ፕሮፌሽናል ሰርተፊኬቶች፤ ከ 20በላይ የመጀመሪያ ድግሪዎች፤ ማስተር ትራክ ሰርተፊኬቶች ያሉት ነው፡፡

o በመጀመሪያ ድግሪ ከሚሰጣቸው የትምህርት ዘርፎች መካከል፡-

ComputerScience
Business
PublicHealth
DataScience
Management
Accounting

o በተመሳሳይ መልኩ በተለያዩ የትምህርት ሙያዎች በማስተርስ ድግሪና በፕሮፌሽናል ሰርቲፊኬት ያሰለጥናል፡፡

o በነፃ የሚሰጡ የትምህርት ዓይነቶች አሉ፡፡ የሚያስፈከፍሉ የትምህርት ዓይነቶችም አሉ

https://www.coursera.org/

2ኛ፦Open Culture Online COURSES

o ይህ ዌብሳይት ከ 1500 በላይ ኦንላይን ኮርሶችን ይሰጣል፡፡

o ከStanford,Yale,MIT,Harvard,Oxford እና የመሳሰሉ ትልልቅ ዩኒቨርሲቲዎች በጋራ የሚሰራ ዌብሳይት ነው፡፡

የሚሰጣቸው ኮርስ ዓይነቶች፡-
oህግ
oህክምናና ጤና ሳይንስ
oኢንጂነሪንግ
oኮምፒውተር ሳይንስ
oሂስትሪ
oፊሎዞፊ

ሊንክ http://www.openculture.com/freeonlinecourses

3ኛ፦ Udemy

ሊንክ https://www.udemy.com/
4ኛ፦ Lifehack Fast TrackClass

ሊንክ https://www.lifehack.org/free-classes

5ኛ፦ AcademicEarth

ሊንክ https://academicearth.org/

6ኛ፦ EdX
ሊንክ https://www.edx.org/

7ኛ፦Alison
o ይህ ዌብሳይት ከሌሎች ዌብሳይቶች የሚለየው ሁሉም ትምህርቶች በነፃ ነው የሚሰጠው፡፡ ለአንድ አንድ ስልጠናዎች ሰርተፊኬትም ይሰጣል፡፡

ሊንክ http://alison.com/

8ኛ፦ITunesU FreeCourses
ሊንክ https://itunes.apple.com/ca/app/itunes-u/id490217893?mt=8&at=1000lwqv
9ኛ፦ StanfordOnline

ሊንክ http://online.stanford.edu/courses

10ኛ፦ HarvardExtension
ሊንክ https://www.extension.harvard.edu/
3.7K viewsƝƲƦƲ ሳይቴክ, edited  07:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2020-12-31 10:10:06 amazon (የቀጠለ)

ድረ-ገጹ ተወዳጅነትን ያተረፈዉ ወድያዉኑ ነበር። በ60 ቀናት ዉስጥ ያለምንም ማስታወቂያ በበርካታ የአሜሪካ ግዛቶች እና ከ45 በላይ አገራት ዉስጥ የሚነኙ ደንበኞች ዋጋዉ ከ$20 ሺህ በላይ የሚያወጣ የመፅሃፍ ግዢን ፈጸሙ። በ1997 ዓ.ም. አማዞን አክስዮኑን ለህዝብ መሸጥ ጀመረ። ጄፍ ቤዞስ በድረ-ገጹ ላይ የሚሸጠዉን እቃ ከመፅሃፍት ባለፈ መልኩ በማሳደግ ሲዲዎቹንና ፊልሞችን አካቶ መሸጥ ጀመረ። ቀጥሎም የህጻናት አሻንጉሊቶችን፣ ልብሶችንና የኤሌክትሮኒክ እቃዎችንና በርካታ ምርቶችን መሸጡን ቀጠለ። በወቅቱ ተከስቶ በነበረዉ የኢንተርኔት ኢኮኖሚ ቀዉስ "dot com crisis" ብዙ ኩባንያዎችን ከገበያ ዉጪ ቢያደርጋቸዉም አማዞን ግን ትርፍማነቱን ቀጥሎ በ1995 ዓ.ም. ከአካሄደዉ የ500 ሺህ ዶላር ሽያጭ በጥቂት ዓመት ዉስጥ ቁጥሩ እጅግ ጨምሮ ወደ ሚሊየኖች ገባ። አማዞን በ2007 ዓ.ም. የመፅሃፍት ነባራዊ እዉነታ የሚቀይር ፈጠራ አስተዋወቀ። ኪንድል የዲጂታል መፅሃፍ ማንበቢያ "e-reader" በመፍጠር የታተሙ መፅሃፍትን ከመግዛት በተጨማሪ አንባቢዎች ዲጂታል መፅሃፍትን በኪንድል ገዝቶ በማዉረድ እንዲጠቀሙ አስቻለ። በ2011 ዓ.ም. ኪንድል ፍየር የተባለዉን ታብሌትም ይፍ አድርጎ የገበያ ፉክክርን ተቀላቀለ። ኩባንያዉ በመላዉ ዓለም በርካታ ቢሮዎች፣ የመረጃ ተቋማት (datacenters) እና ከ150 ሺህ በላይ ሰራተኞች አሉት። በሰከንድ እስከ 500 የግዢ ትዕዛዞችን ማስተናገድ የሚችለዉ አማዞን በመላዉ አለም ከ244 ሚሊየን በላይ ቋሚ ደንበኞች እንዳሉት ይነገራል። በአሁኑ ሰዓት በአመት በአማካኝ ወደ $130 ቢሊየን በላይ ሽያጭ ያከናዉናል። ጄፍ ቤዞሶ ከ$110 ቢሊየን በላይ በማካበት በአጠቃላይ የሰዉ ልጅ ታሪክ ዉስጥ ትልቁ ባለጸጋ ሊሆን በቅቷል። ከ1990ዎቹ ጀምሮ በዓለም ላይ አንደኛ ባለጸጋ የሆነዉን ቢል ጌትስ ለመጀመሪያ ጊዜ በሃብት በመብለጥ የዓለማችን 1ኛ ባለጸጋ መሆን የቻለዉም በ2017 አጋማሽ ላይ ነበር። የባለጸግነቱ እርከን በየጊዜው ቢቀያየርም በፎርብስ ዘገባ መሠረት ጄፍ ቤዞስ በሰዉ ልጅ ታሪክ ዉስጥ ቁንጮ የዓለማችን ባለጸጋ ሊሆን በቅቷል።

በቀጣይ ሌሎች የጄፍ ቤዞስ የፈጠራ ስራዎችን እናያለን
3.1K viewsƝƲƦƲ ሳይቴክ, 07:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2020-12-30 10:03:32 ለመሆኑ የአማዞን መስራች ማን ነዉ። እንዴትስ ተመሰረተ??

amazon (አማዞን)

በጃኑዋሪ 12 1964 ዓ.ም. ነዉ ሜክሲኮ በተባለች የአሜሪካ ክፍለ ግዛት ዉስጥ የተወለደዉ ጄፍ ቤዞስ ገና በወጣትነቱ ነበር ለኮምፒዉተር ፍቅር ያደረበት። ከዚህም የተነሳ የወላጆቹን የመኪና ማቆሚያ ጋራዥ በመዉሰድ የራሱ የኮምፒዉተር ቤተ-ሙከራ አደረገዉ። የ2ተኛ ደረጃ ትምህርቱን በከፍተኛ ዉጤት ከተመረቀ በኋላ በታዋቂዉ የፕሪንስተን ዩኒቨርስቲ የመጀመሪያ ድግሪዉን በኮምፒዉተር ሳይንስና ኤሬክትሪካል ኢንጅነሪንግ በ1986 ዓ.ም. በከፍተኛ ማዕረግ ተመርቋል። በርካታ የሥራ መቀጠር እድሎችን ያገኘዉ ጄፍ በዞስ በኒዉዮርክ ከተማ በከፍተኛ ደሞዝና ኃላፊነት ተቀጥሮ መሥራት ጀመረ። ምንም እንኳን ተቀጥሮ የሚሰራበት ስራ ከፍተኛ ደመወዝ የሚያስገኝለትና ስልጣንንም ያቀናጀዉ ቢሆንም፣ ሥራዉን ከአራት አመት በኋላ ለቆ በመዉጣት ዛሬ በኢንተርኔት ዘርፍ ታላቅ ስኬት የተቀናጀዉን አማዞንን ለማቋቋም ተነሳ። በወቅቱ ገና አዲስ የነበረዉን ኢ-ኮሜርስን ለማካሄድ ምርጥ ስራዉን የመልቀቅ እርምጃዉ እብድ ቢመስልም የፈጠራ ባለሙያዎች ባህርይ አንድን ነገር ለመሞከር መድፈርና ዉድቀትን አለመፍራት በጄፍ ቤዞስ ዉስጥም ጎልቶ ታይቷል። በ1994 ዓ.ም. ኒዉዮርክን ለቆ ኑሮዉን በሲያትል ከተማ በማድረግ የመጀመሪያዉን የመፅሀፍ መገበያያ ድረ-ገፅ ይፍ አደረገ። የመኖርያ ቤቱን የመኪና ጋራዥ የኮምፒዉተር ተቋሙ፣ መኝታ ቤቶቹንም ቢሮ በማድረግ ከጥቂት ሠራተኞች ጋር ስራዉን ጀመረ። 300 ያክል ዘመድ ወዳጆቹን ለሙከራ ወደ ስራዉ የመገበያያ ድረ-ገፅ በመጋበዝ አነስተኛ ክፍያን እየተቀበለ መፅሃፍትን በኢንተርኔት ላይ መሸጥ የተጀመረዉ ስራ በጁላይ 1995 ዓ.ም. "amazon.com" በሚል ስም ለተጠቃሚ ክፍት አደረገ። ቤዞስ አማዞን የሚለዉን ስም ያወጣዉ በሁለት ምክንያቶች ነበር። የመጀመሪያዉ የአማዞንን ጫካ በመወከል በርካታ መፅሃፍት የሚገኙበት ግዙፍ የኢንተርኔት መደብር መሆኑን ለማሳየት ሲሆን፣ ሁለተኛዉ ደግሞ በወቅቱ ድረ-ገጾች በፊደል ቅደም ተከተል ይደረደሩ ስለነበር በቀላሉ ለሰዎችበድረ-ገጾች ማሰሻ ላይ እንዲታይ ታስቦ ነበር። የአማዞን መለያ አርማ በሶስት የመሻሻል ሂደት ዉስጥ ያለፈ ሲሆን፣ በ2000 ዓ.ም. የተደረገዉ መሻሻል ዛሬ ድረስ የምናቀዉን መልክ ሰጥቶታል። በዚህ የመለያ አርማ ላይ ያለዉ ከፍ "A" ተነስቶ "Z" ጋር የሚደርስ ቀስት ሁሉንም ነገር በአማዞን ላይ ማግኘት እንደሚቻል ለማሳየት ነዉ።

ይቀጥላል.....
3.2K viewsƝƲƦƲ ሳይቴክ, 07:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2020-12-29 09:19:18 ‍ ብዙ ጊዜ በinbox ለምትጠይቁ ጥያቄዎች (FAQ)


በምንድነው ሚከፍለው YouTube?

YouTube ሚከፍለው የሰራቹሁትን በየወሩ በባንክ አካውንታቹ ቀጥታ ወይም በWestern Union ነው (Western Union በ2021 ሚቋረጥ ቢሆንም)፡፡

በስንት ተመልካች ስንት ይከፈላል?

ከቻናል ቻናል ይለያያል፤ የተመልካቾች ቦታ፣ የቪድዮ ርዝመት እና ሌሎች፡ነገሮችም ይወስኑታል ስለዚህ በዚህ ያህል ቪው ይሄን ያህል ማለት አይቻልም፡፡

ሰብስክራይበር ምን ያደርጋል?

በርካታ ሰብስክራይበር አላቹ ማለት አዲስ ቪድዮ ስትለቁ ለማየት ሚፍልጉ በርካታ ሰዎች አሉ ማለት ነው፤ ስለዚህ አዲስ ቪድዮ ስትለቁ ለሰብስከራይበር ይደርሳል ያ ማለት ደሞ ቪው ይጨምራል ያ ማለት ደሞ ብር ይጨምራል፡፡


የኔ ያልሆነ ቪድዮ መልቀቅ አልቻልም?

Copyright የናንተ ያልሆነ ቪድዮ መልቀቅ ቻናላቹን ሊያስዘጋባቹ ይችላል፤ ድሮ ብዙ
ቻናሎች የራሳቸው ባልሆነ ቪድዮ ብዙ ብር ሰርተዋል አሁን ግን ቻናላቹ ብር ለመስራት ከመለቀቁ በፊት ምን ዓይነት ቪድዮ እንደምትለቁ ይታያል ስለዚህ የሰው ቪድዮ በመልቀቅ ብር መስራት እንደማይቻል ሆንዋል!!

YouTube channel እንዴት #Subscribe እናደርጋለን?

ስልካችሁ ላይ #Google account (Gmail) ካለ በቀላሉ ከታች ያለውን ሊንክ ውስጥ ገብተው "Subscribe" የሚለውን #መንካት ብቻ / Facebook ላይ ፎቶ like ማድረግ ያህል ቀላል ነው።

ስልካችሁ ላይ Google account (Gmail) የሌለ ደግሞ የGmail Username and password በማስገባት "Subscribe" ማድረግ ትችላላችሁ /ወደፊትም ድንገት ስልካችሁ ቢበላሽ ይጠቅማችኋል።

ጥቅሙ የናንተው ነውና ለSubscribe እንዳትሰስቱ
3.3K viewsƝƲƦƲ ሳይቴክ, 06:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ