Get Mystery Box with random crypto!

የተዘጉ ስልኮችን መክፈት ማለት ምን ማለት ነው? መፍትሄ 1 PART ONE ▬ | ƝƲƦƲ ሳይቴክ

የተዘጉ ስልኮችን መክፈት ማለት ምን ማለት ነው?
መፍትሄ 1

PART ONE
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

የተዘጉ ስልኮችን መክፈት ማለት ምን ማለት ነው?
Network ሰጪ ድርጅቶች በመላው አለም ላይ ይገኛሉ። በሀገራችንም ethio telecom ይገኛል። በሌሎች ሀገራት ደግሞ ከ አንድ በላይ network አቅራቢ ድርጅቶች ሊኖሩ ይችላሉ። ይህም የሆነበት ምክንያት በመንግስት ስር ሳይሆን በግል ተቋማት ስር ስለሆኑ ነው።ለዚህም ጎሮቤታችን Kenya ጥሩ ማሳያ ናት። ከአንድ በላይ የመኖሩ ጥቅም ህዝቡ የተሻለ አማራጭ ያገኛል ድርጅቶቹም የተሻለ ነገር ለማቅረብ ፉክክር ዉስጥ ይገባሉ። አንድ አንድ network ሰጪ ድርጅቶች ደግሞ አለም አቀፍ እውቅና አላቸው።
ለምሳሌ T-mobile, verizon, orange, vodafone.....
እነዚህ ድርጅቶች ከሚፎካክሩቸው መንገዶች አንዱ ደንበኞችን ለመሳብ ሲሉ የስልክ ቀፎዎችን በቅናሽ ዋጋ ያቀርባሉ። ይህን የሚያደርጉት ደንበኞቻቸው የአየር ሰአት በገዛቸዉ ቁጥር ተጠቃሚ ስለሚሆኑ ነው። ነገር ግን በዚህ መንገድ የተገዙ የስልክ ቀፎዎች ከተገዙበት የnetwork ሰጪ ተቋማት ውጪ ያሉ sim cardoችን አይቀበሉም ይህም ምክንያቱ በ security code ስለሚቆለፉ ነው። እንደዚህ አይነት ስልኮች ሀገር ስለቀየሩ ሳይሆን እንቢ የሚሉት ከተገዙበት የ network ሰጪ ድርጅት ዉጪ ባሉ network ሰጪ ድርጅቶች sim card ስለማይሰሩ ነው።

የተዘጉ ስልኮች የሚከተሉትን ምልክቶች ያሳያሉ።
Sim not valid, wrong sim,unknown sim, phone restricted, contact service provider.....

ከ network ሰጪ ድርጅቶች የተገዛ ስልክ ለመክፈት ሁለት መንገድ አለ።

1. Computer , flasher box, እና flasher file በመጠቀም መክፈት ይቻላል።
ይህ ዘዴ አሁን ላይ ethio telecome የሚዘጋቸውን ስልኮችንም ይመለከታል ነገር ግን በዚህ Method ለመክፈት Computer, flasher box እና flasher file ያስፈልገናል።
ስለ Computer ማብራራት አያስፈገኝም ነገር ግን በዚህ Method ትንሽ አሸጋሪ የሚሆነው Universal flasher box ማግኘት ነው ይሄ box የተለያዩ ጥቅሞች ሲኖሩት ከዚህም ውስጥ በስልኩ ሞዴል የራሱን flasher file ከ Google ላይ በማወረድ ከስልኮቻችን ጋር በማገናኘት የትኛውንም ስልክ ማስተካከል እንችላለን ከ hardware ውጪ ምንም አይነት ችግሮችን እንድናስተካክል ያስችለናል።
ይህ universal flasher Box orginale ስልኮችን IMEI create በማድረግ አሁን ላይ ላለው ethio telecome ለሚዘጋቸው ስልኮች ፍቱን መድሃኒት ሲሆን የ flasher box ዋጋ በ Ethiopia 4326birr አከባቢ ሲሆን የተወሰኑ ሞባይል ቤቶች በ addis abeba እየተጠቀሙበት ይገኛሉ።
ለምሳሌ ለመጠቆም ያህል መርካቶ ይርጋ ሃይሌ building ላይ በኛ በኩልም ይህን flasher box ማግኘት ይችላሉ።

2. ለ ድርጅቱ መጠነኛ ክፍያ በመፈጸም ማስከፈት ሲሆን:-
ለምሳሌ iphone በ icloud የተዘጉ ስልኮችን መጥቀስ ይቻላል እንደዚህ አይነት ስልኮች የ e-commerce እንዲሁም credit card ይጠይቃሉ። ይሄ አገልግሎት ደግሞ እኛ ሀገር ስለሌለ ያለው አማራጭ ውጭ ሀገር በምናቀው ሰው ማስከፈት ነው። ይህ ማለት ድህረ ገፁ ላይ ግብተን የስልኩን ሞዴል ስናስገባ ክፍያ ይጠይቀናል ክፍያውም የሚከናወነው በ ማስተር ካርድ ስለሆነ ክፍያውን ውጪ ሃገር ማስተር ካርድ ባለው ሰው ከባላንሱ ላይ እንዲፈፅምልን በማድረግ ክፍያው ከተፈጸመላቸው ድርጅቱ ኮዱን በሚያስገባው Email አድሬስ ስለሚልክልን ወድያውኑ መክፈት ይቻላል።
በ icloud የተዘጉ ስልኮች በማስተር ካርድ በ አሁን ጊዜ የሚያስከፈለው 104$ ዶላር ነው ለዚህም ነው በአዲስ አበባ በተለያዩ የ ሞባይል ቤቶች በተለይ መርካቶ ላይ ከ200$ ዶላር በላይ የሚጠይቁት ጥቅማቸውን በማሰብ ማለት ነው። እዚህ ላይ ማስተዋል ያለባችሁ ውጪ ሃገር ላይ የ ማስተር ካርድ ቪዛ ኮዱን አስገብቶ ክፍያውን ሊፈፅምላችሁ እና በ Email የሚላክለትን Code ሊልክላችሁ የሚችል ወዳጅ ከሌላችሁ ምንም አይነት አማራጭ የላችሁም ከ200$ ዶላር በላይ ከፍለን ከማስከፈት ውጪ ስልኩን መጠቀም አንችልም።
በ i Cloud ያልተዘጉ ስልኮችን እና እንዲሁም የተወሰኑ icloud locked የሆኑ iphone ስልኮችን DNS method በመጠቀም መክፈት የምንችልበትን ዘዴ ሰፋ ባለ Program ከዚህ በፊት አቅርበንላችኋል ወደኋላ በመመለስ Check ማድረግ ትችላላችሁ።

መፍትሄ 2

PART two
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

ይሄ መንገድ ስላካችንን በመጀመሪያ ሩት ማድረግ ይጠበቅብናል። ስለ ሩት ከዚህ በፊት Post ላይ ማብራሪያ ስለሰጠን ከዛ ላይ ገብተው ያንብቡ። ሩት የሆነ ቀፎ ካለን እንደሚከተለው በማድረግ imei መቀየር እንችላለን ።

ይህን ዘዴ ለመጠቀም ሁለት ፕሮግራሞች እንጠቀማለን የመጀመሪያው:-

1.Mobileuncle MTK IMEI Write Tool የሚለውን ሶፍትዌር ኮምፒውተራችን ላይ ዳውንሎድ እናደርጋለን ከዛ በዚፕ ያለውን ፕሮግራም ስንከፍት የሚያመጣልን ዊንዶው ላይ Y ብልን ፅፈን enter እንጫናለን ከዛ የሞባይላችንን imei እንፅፍና
create IMEI .BAK ብለን አዲስ የተፈጠረውን imei.bak ፋይል ወደ ሜሞሪ ካርድ እንልከዋለን።

ሜሞሪ ካርዱን ቀፎ ውስጥ ካስገባን በኋላ...

2.ይህን አፕሊኬሽን ቀፏችን ላይ እንጭናለን mobileuncle_MTK_toolv2.9.9.apk

3.ከዛ የጫነውን አፕሊኬሽን ስንከፍት ሩት ኣክሰስ ጥያቄ ሲጠይቅ grant ብለን ፍቃድ እንሰጠዋለን።

ከዛ IMEI backup and restore የሚለውን ከፍተን ,restore IMEI.bak. ስንል ቅድም ሜሞሪ ላይ ያስቀመጥነውን ፋይል ወደ ቀፏችን ይፅፍልናል።

ሲጨርስ ቀፏችንን Restart አድርገን መደወያው ላይ *#06# አስገብተን በትክክል መፃፉን እናረጋግጣለን።
ነገር ግን ሚሞሪ የማይወስዱ ስልኮች እና የተወሰኑ ሞባይሎች ለምሳሌ iphone...etc በmobile Uncle tools ImEI backup restore የሚለው not supported ካላችሁ ከላይ ለመግለፅ እንደሞከርንው በ method one የሚከፈቱ ስለሆኑ የግድ Flasher box መግዛት ይጠበቅባችኋል።


የዩቲዩብ ቻናላችንን Subscribe በማድረግ የኤሌክትሮኒክስ ጥገናዎችን ይማሩ



https://www.youtube.com/channel/UCr1PSR41Dom6j2qYe80LxjQ?

▬▬▬ Share ▬▬▬▬