Get Mystery Box with random crypto!

amazon (የቀጠለ) ድረ-ገጹ ተወዳጅነትን ያተረፈዉ ወድያዉኑ ነበር። በ60 ቀናት ዉስጥ ያለ | ƝƲƦƲ ሳይቴክ

amazon (የቀጠለ)

ድረ-ገጹ ተወዳጅነትን ያተረፈዉ ወድያዉኑ ነበር። በ60 ቀናት ዉስጥ ያለምንም ማስታወቂያ በበርካታ የአሜሪካ ግዛቶች እና ከ45 በላይ አገራት ዉስጥ የሚነኙ ደንበኞች ዋጋዉ ከ$20 ሺህ በላይ የሚያወጣ የመፅሃፍ ግዢን ፈጸሙ። በ1997 ዓ.ም. አማዞን አክስዮኑን ለህዝብ መሸጥ ጀመረ። ጄፍ ቤዞስ በድረ-ገጹ ላይ የሚሸጠዉን እቃ ከመፅሃፍት ባለፈ መልኩ በማሳደግ ሲዲዎቹንና ፊልሞችን አካቶ መሸጥ ጀመረ። ቀጥሎም የህጻናት አሻንጉሊቶችን፣ ልብሶችንና የኤሌክትሮኒክ እቃዎችንና በርካታ ምርቶችን መሸጡን ቀጠለ። በወቅቱ ተከስቶ በነበረዉ የኢንተርኔት ኢኮኖሚ ቀዉስ "dot com crisis" ብዙ ኩባንያዎችን ከገበያ ዉጪ ቢያደርጋቸዉም አማዞን ግን ትርፍማነቱን ቀጥሎ በ1995 ዓ.ም. ከአካሄደዉ የ500 ሺህ ዶላር ሽያጭ በጥቂት ዓመት ዉስጥ ቁጥሩ እጅግ ጨምሮ ወደ ሚሊየኖች ገባ። አማዞን በ2007 ዓ.ም. የመፅሃፍት ነባራዊ እዉነታ የሚቀይር ፈጠራ አስተዋወቀ። ኪንድል የዲጂታል መፅሃፍ ማንበቢያ "e-reader" በመፍጠር የታተሙ መፅሃፍትን ከመግዛት በተጨማሪ አንባቢዎች ዲጂታል መፅሃፍትን በኪንድል ገዝቶ በማዉረድ እንዲጠቀሙ አስቻለ። በ2011 ዓ.ም. ኪንድል ፍየር የተባለዉን ታብሌትም ይፍ አድርጎ የገበያ ፉክክርን ተቀላቀለ። ኩባንያዉ በመላዉ ዓለም በርካታ ቢሮዎች፣ የመረጃ ተቋማት (datacenters) እና ከ150 ሺህ በላይ ሰራተኞች አሉት። በሰከንድ እስከ 500 የግዢ ትዕዛዞችን ማስተናገድ የሚችለዉ አማዞን በመላዉ አለም ከ244 ሚሊየን በላይ ቋሚ ደንበኞች እንዳሉት ይነገራል። በአሁኑ ሰዓት በአመት በአማካኝ ወደ $130 ቢሊየን በላይ ሽያጭ ያከናዉናል። ጄፍ ቤዞሶ ከ$110 ቢሊየን በላይ በማካበት በአጠቃላይ የሰዉ ልጅ ታሪክ ዉስጥ ትልቁ ባለጸጋ ሊሆን በቅቷል። ከ1990ዎቹ ጀምሮ በዓለም ላይ አንደኛ ባለጸጋ የሆነዉን ቢል ጌትስ ለመጀመሪያ ጊዜ በሃብት በመብለጥ የዓለማችን 1ኛ ባለጸጋ መሆን የቻለዉም በ2017 አጋማሽ ላይ ነበር። የባለጸግነቱ እርከን በየጊዜው ቢቀያየርም በፎርብስ ዘገባ መሠረት ጄፍ ቤዞስ በሰዉ ልጅ ታሪክ ዉስጥ ቁንጮ የዓለማችን ባለጸጋ ሊሆን በቅቷል።

በቀጣይ ሌሎች የጄፍ ቤዞስ የፈጠራ ስራዎችን እናያለን