Get Mystery Box with random crypto!

ለመሆኑ የአማዞን መስራች ማን ነዉ። እንዴትስ ተመሰረተ?? amazon (አማዞን) በጃኑዋ | ƝƲƦƲ ሳይቴክ

ለመሆኑ የአማዞን መስራች ማን ነዉ። እንዴትስ ተመሰረተ??

amazon (አማዞን)

በጃኑዋሪ 12 1964 ዓ.ም. ነዉ ሜክሲኮ በተባለች የአሜሪካ ክፍለ ግዛት ዉስጥ የተወለደዉ ጄፍ ቤዞስ ገና በወጣትነቱ ነበር ለኮምፒዉተር ፍቅር ያደረበት። ከዚህም የተነሳ የወላጆቹን የመኪና ማቆሚያ ጋራዥ በመዉሰድ የራሱ የኮምፒዉተር ቤተ-ሙከራ አደረገዉ። የ2ተኛ ደረጃ ትምህርቱን በከፍተኛ ዉጤት ከተመረቀ በኋላ በታዋቂዉ የፕሪንስተን ዩኒቨርስቲ የመጀመሪያ ድግሪዉን በኮምፒዉተር ሳይንስና ኤሬክትሪካል ኢንጅነሪንግ በ1986 ዓ.ም. በከፍተኛ ማዕረግ ተመርቋል። በርካታ የሥራ መቀጠር እድሎችን ያገኘዉ ጄፍ በዞስ በኒዉዮርክ ከተማ በከፍተኛ ደሞዝና ኃላፊነት ተቀጥሮ መሥራት ጀመረ። ምንም እንኳን ተቀጥሮ የሚሰራበት ስራ ከፍተኛ ደመወዝ የሚያስገኝለትና ስልጣንንም ያቀናጀዉ ቢሆንም፣ ሥራዉን ከአራት አመት በኋላ ለቆ በመዉጣት ዛሬ በኢንተርኔት ዘርፍ ታላቅ ስኬት የተቀናጀዉን አማዞንን ለማቋቋም ተነሳ። በወቅቱ ገና አዲስ የነበረዉን ኢ-ኮሜርስን ለማካሄድ ምርጥ ስራዉን የመልቀቅ እርምጃዉ እብድ ቢመስልም የፈጠራ ባለሙያዎች ባህርይ አንድን ነገር ለመሞከር መድፈርና ዉድቀትን አለመፍራት በጄፍ ቤዞስ ዉስጥም ጎልቶ ታይቷል። በ1994 ዓ.ም. ኒዉዮርክን ለቆ ኑሮዉን በሲያትል ከተማ በማድረግ የመጀመሪያዉን የመፅሀፍ መገበያያ ድረ-ገፅ ይፍ አደረገ። የመኖርያ ቤቱን የመኪና ጋራዥ የኮምፒዉተር ተቋሙ፣ መኝታ ቤቶቹንም ቢሮ በማድረግ ከጥቂት ሠራተኞች ጋር ስራዉን ጀመረ። 300 ያክል ዘመድ ወዳጆቹን ለሙከራ ወደ ስራዉ የመገበያያ ድረ-ገፅ በመጋበዝ አነስተኛ ክፍያን እየተቀበለ መፅሃፍትን በኢንተርኔት ላይ መሸጥ የተጀመረዉ ስራ በጁላይ 1995 ዓ.ም. "amazon.com" በሚል ስም ለተጠቃሚ ክፍት አደረገ። ቤዞስ አማዞን የሚለዉን ስም ያወጣዉ በሁለት ምክንያቶች ነበር። የመጀመሪያዉ የአማዞንን ጫካ በመወከል በርካታ መፅሃፍት የሚገኙበት ግዙፍ የኢንተርኔት መደብር መሆኑን ለማሳየት ሲሆን፣ ሁለተኛዉ ደግሞ በወቅቱ ድረ-ገጾች በፊደል ቅደም ተከተል ይደረደሩ ስለነበር በቀላሉ ለሰዎችበድረ-ገጾች ማሰሻ ላይ እንዲታይ ታስቦ ነበር። የአማዞን መለያ አርማ በሶስት የመሻሻል ሂደት ዉስጥ ያለፈ ሲሆን፣ በ2000 ዓ.ም. የተደረገዉ መሻሻል ዛሬ ድረስ የምናቀዉን መልክ ሰጥቶታል። በዚህ የመለያ አርማ ላይ ያለዉ ከፍ "A" ተነስቶ "Z" ጋር የሚደርስ ቀስት ሁሉንም ነገር በአማዞን ላይ ማግኘት እንደሚቻል ለማሳየት ነዉ።

ይቀጥላል.....