Get Mystery Box with random crypto!

ƝƲƦƲ ሳይቴክ

የቴሌግራም ቻናል አርማ nurudish — ƝƲƦƲ ሳይቴክ Ɲ
የቴሌግራም ቻናል አርማ nurudish — ƝƲƦƲ ሳይቴክ
የሰርጥ አድራሻ: @nurudish
ምድቦች: እውነታው
ቋንቋ: አማርኛ
ሀገር: ኢትዮጵያ
ተመዝጋቢዎች: 8.06K
የሰርጥ መግለጫ

ይህ ቻናል ፈጠራዎችን ፣ መረጃዎችን በአማርኛ& English፣የቴክኖሎጂ እውነታዎችን ፣ የወደፊቱን ቴክኖሎጂ እና የአይቲ ምክሮችን በማካተት የቴክኖሎጂ ዓለምን ያቀርባል፡፡
በተጨማሪም፦ ዌብሳይት በተመጣጣኝዋጋ እንሰራለን
🔷 ማህበራዊ ሚዲያን ለእውቀት ብቻ እንጠቀምበት !
🔺 ጥያቄ እና አስተያየት ካለ በዚህ ስልክ ያሳውቁን! 251945686310

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2021-01-17 13:08:23 የዋትሳፕ አስደንጋጩ ህግ እና አዲሱ ገራሚ አፕ | How to use Signal App


2.9K viewsƝƲƦƲ ሳይቴክ, edited  10:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-01-15 10:09:20 ሞባይል ዳታ በሚከፈትበት ጊዜ ካርድ ወይም የተሞላውን የዳታ ጥቅል በቶሎ የሚጨርስበት ምክንያትቶችና መፍትሔዎች:

ምክንያቶች :-
1.የሞባይል ዳታ ተከፍቶ ሲረሳና ሳይዘጋ ሲቀር
2.ኢንተርኔት ክፍት ሆኖ ከተለያዩ ደህረ ገፆች ላይ ቀጥታ ቪዲዮች ሲታዩ
3.System settings እና Applications በራሳቸው ጊዜ አፕዴት ሲያደርጉ
4.በሞባይሉ ላይ የሚገኙ አፕሊኬሽኖች ተጠቃሚው በማያቸው መንገድ ከበስተጀርባ ሲሰሩ
5.በሞባይል ስልኩ ውስጥ ቫይረስ ሲኖር
---------------------------
መፍትሔዎች :-
ሞባይል ዳታ ተከፍቶ ሲረሳና ሲቆይ እንደ ሶሻል ሚዲያና ኦንላይን የሚሰሩ አፕሊኬሽኖች ከተጠቃሚው እይታ ውጪ ስራቸውን ያከናውናሉ። በዚህ ጊዜ በሞባይሉ ላይ የተሞላው ክሬዲት ሰዓት ይቀንሳል ወይም ያልቃል ስለዚህም ኢንተርኔት ተጠቅመው ከጨረሱ በኋላ የሞባይሉን ዳታ ያጥፉ።

በሞባይል ዳታ ኢንተርኔት ከፍቶ ከተለያዪ ድህ ገፆች ላይ በቀጥታ ቪዲዮ መመልከት የተሞላውን ካርድ መጠን በጊዜ ከሚያሳጥሩት ነገሮች ወስጥ አንደኛው ሲሆን ለዚህም ዋነኛው
ምክንያት በኢንተርኔት ቪዲዮ ቀጥታ መመልከት የሚቆጥረው የዳታ መጠን ከፍተኛ ስለሆነ ነው ስለዚህ ቪዲዮ ማየቱ ግዴታ ከሆነ በ Vidmate እና በሌሉች ቪዲዮ ዳውሎደር አፕሊኬሽኖች የቪዲዮ ይዘት በመቀነስ ጭኖ መመልከቱ ወጪን
ይቆጥባል።

System settings እና Application በራሳቸው ጊዜ አፕዴት ሲያደርጉ የተሞላውን ዳታ(ካርድ) ይወስዳሉ ታዲያ ይህን ለማስቀረት Free wifi ከተገኘ አፕዴት ማድረግ ይህ ማድረግ የማይቻል ከሆነ system settings አፕዴት እንዳያደርግ ማስቆም:
Settings ----About----Software Update---
Automatic update የሚለውን ማጥፋት
Applications አፕዴት እንዳያደርጉ ከተፈለገ ደግሞ
-Google Play መክፈት.
- hamburger የሚመስለውን በለ ሶስት ሆሪዞንታል ምልክት ያለበትንም አናት ላይ በስተግራ በኩል Settings በመንካት
Auto-update apps.- disable automatic app updates, የሚለውን በመክፈት እና በመምረጥ መዝጋት
ይቻላል

በሞባይሉ ላይ የሚገኙ አፕሊኬሽኖች ተጠቀሚው በማያቸው መንገድ ከበስተጀርባ ሲሰሩ ከእይታ ውጪ በመሆን የክሬዲት መጠን ይቀንሳሉ ታዲያ ይህን ለመከላከል:
Settings----
data usage ---Restricted Background data
የሚለውን መክፈት... ከዚህ ይበልጥ ደግሞ Mobile data
saver አፕሊኬሽኖች በመጫን መጠቀም

በሞባይል ሰልክ ውስጥ ቫይረስ ሲኖር የተሞላውን ሞባይል
ዳታ ከመቅስፈት እድሜው እንዲያጥር ያደርጋል ብሎም ቫይረሱ በራሱ ጊዜ የሞባይሉን ኦፕሬቲንግ ሲስተም በማዘዝ ያለማንም ትዕዛዝ ዳታ ይከፍታል ዳውንሎድ ያደርጋል አላስፈላጊ ነገሮችና ማስታወቂያዋች ይለቃል ከዚህም የተነሳ በፍጥነት የሞባይል ካርድ( ዳታ ጥቅል) ይጨርሳል ይህ ነገር በሞባይሉ ላይ ቢከሰት አንቲ ቫይረስ በመጫ ሰካን ማድረግ ይህ መፍትሔ የማይሆን ከሆነ ለባለሙያ ማሳየቱ ተገቢ ነው::

መረጃዎች ቶሎ ቶሎ እንዲደርሳችሁ ቻናላችንን #Mute ያደረጋችሁት #UNMUTE በማድረግ ተባበሩን "

የዩቲዩብ ቻናላችንን Subscribe በማድረግ የቴክኖሎጂ እውቀትዎን ያሳድጉ!



https://www.youtube.com/channel/UCr1PSR41Dom6j2qYe80LxjQ?

▬▬▬ Share ▬▬▬▬
3.5K viewsƝƲƦƲ ሳይቴክ, 07:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-01-14 10:14:11 ሠላም ዉድ የኑሩ ሳይቴክ ተከታታዮች ዛሬ የአብዛኛው ሠው ጥያቄ ስለሆነው #BISSKEY /የተቆለፉ ቻናሎችን የምንከፍትበት መንገዶችን ልንገራችሁ
SUPER MAX 9300 ባለ 2ፍላሽ መሠኪያ

የምንፈልገውን ቻናል ከፍተን በመቀጠል MENUእንነካለን ከዛን 8ቁጥርን አራት ጊዜ ስንጫን የመሙያ ሳጥን ይመጣልናል ከዛን ለምሳሌ የ #TV_VARZISH የምንሞላ ከሆነ ABAFCD እንሞላለን ማለት ነው፡፡
SM 2425 HD,SM2350 Power Tech and SM 2560 Brilliant ,FT 9700 Diamond እና SM 9700 Gold Plus

የምንፈልገውን ቻናል እንክፈት በመቀጠል OK ስንነካ የቻናል ዝርዝሮች ይመጣልናል ከዛን ሪሞቱ ላይ ሰማያዊ በተን ስንነካ የbiss menuይመጣልናል okየሚለውን በመንካት ኮዱን ካስገባን በዋላ ሠማያዊ በተንን 2ጊዜ ስንነካ save ያደርግናል ማለት ነው፡፡
SM 9700 GOLD + CA HD
የፈለገንን ቻናል ከፍተን ሪሞቱ ላይ 9339 በመንካት ከሚመጡልን አማራጮች SSSP(twin) የሚለውን እንምረጥ ከዛን ቀይ በተንን በመንካት የቻናሉን ኮድ እናስገባና saveእናደርጋለን ከዛን ቻናሉ ራሱ ይከፍታል፡፡
SM 2550 HD CA MINI
በመጀመርያ ቻናሉን እንከፍታለን በመቀጠል ይህንን እንከተል MENU>CONDITIONAL>ACCESS>CA SETTING> KEY EDIT> BISS> PRESS OK ከዛን የበፊቱን ቁጥር አጥፍተን ADD(አረንጓዴ )በተንን እንንካ በመቀጠል ቁጥሩን ካስገባን በዋላ save እናደርጋለን፡፡

SM 9200 CA HD,SM2425 power plus,SM 9700 + HD

ቻናሉን እንከፍታለን በመቀጠል slow በተንን እና አንድ ቁጥርን 4ጊዜ በመንካት patch menu active እናድርግ፡፡በመቀጠል page - የሚለውን ስንነካ አዲስ window ይመጣልናል ከዛን ቁጥሩን ከሞላን በዋላ save አድርገን ሩሲቨሩን አጥፍተን ስናበራው ቻናሉን ይበረግድልናል፡፡
Eurostar EB 9600,9200,9300
እነኚህ ሪሲቨሮች ላይ BISS ለማስገባት MENU እንነካለን ከዛን ሠባትን 4ጊዜ (7777) እንነካለን ከዛ biss የሚል ይመጣልናል ok ብለን እናስገባና save እናደርጋለን
IBOX 3030 HD
ይህ ሪሲቨር ሁለት አይነት አገባብ አለው
የመጀመርያው መንገድ
በlatest software ሪሲቨሩን upgrade እናደርጋለን በመቀጠል ሪሞቱ ላይ የኢንተርኔት ምልክት ስንነካ patch menu open ሲለን yes እንለዋለን ከዛን ከዚህ እንወጣና AB- የሚለውን ስንነካ የBISS KEY box መሙያ ይመጣልናል ከዛን ቀይ በተን ስንነካ መሙላት እንችላለን ማለት ነው ፡፡ከዛን ቻናሉ ይከፈለ፡ታል ማለት ነው፡፡ በዚህ ካልሆነ
#ሁለተኛው_መንገድ

ሪሞቱ ላይ የኢንተርኔት ምልክት ስንነካ patch menu open ሲለን yes እንለዋለን በመቀጠል manualy key የሚለውን አማራጭ እንነካለን፡፡በመቀጠል ከላይ በኩል ከተደረደሩት ኪዎች ትተን የጎን አቅጣጫ በመንካት bisskey የሚል እስኪያመጣልን ድረስ እንሔዳለን ከዛን Add የሚለውን ቀይ በተን እንነካለን ከዛ 3መደብ ላይ ቢጫ በመጫን መሙላት ከዛን save እናደርጋለን ከዛን በመመለስ ፍሪኩዌንሲ symbol rate አስገብተን ማየት እንችላለን፡፡
CORNOT HD RECIVERS
ቻናሉን እንከፍታለን በመቀጠል ሪሞታችን ላይ ሠማያዊ በተን እንነካና KEY እናስገባለን ማለት ነው ፡፡
LIFE STAR 6060 & 8080
መጀመርያ የሪሲቨሮቹን ሶፍትዌር ከጫንን በኋላ የምንፈልገው ቻናል ላይ በማድረግ በቅድሚያ ሪሞቱ ላይ “F1+000” በመንካት patch menu active እናደርጋለን ከዛ ሪሞቱ ላይ “F1+333” በመንካት Bisskey ማስገባት እንችላለን፡፡
HD WORLD RECIVERS
የተቆለፈዉ ቻናል $ ላይ ማድረግ
ቀጥሎ ሪሞቱ ላይ { 0000 } አራት መንካት ኮዱን ምንሞላበትን ያመጣልናል Biss Key ዉን መሙላት ነው ።
LIFE STAR 4040
መጀመሪያ ምንከፍተዉ ቻናል $ ላይ ማድረግ ቀጥሎ ሪሞቱ ላይ { 0000 } አራት ግዜ መንካት ኮዱን ምንሞላበትን ያመጣልናል Biss key ዉን መሙላት ነው።
SM F18 HD RECIVER
በመጀመርያ የሪሲቨሩን ሶፍትዌር መጫን በመቀጠል PAGE - በመንካት BISSKEY ማስገባት እንችላለን ፡፡
GSKY V6 RECIVERS
በመጀመርያ የPOWER VU SOFTWATE መጫኑን ማረጋገጥ በመቀጠል MENU ገብተን CONDITIONAL ACCESS የሚለውን እነጫናለን ከዛን KEY የሚለውን BISSKEY እናገኛለን፡፡በመቀጠል ADD እንነካለን PROVIDER ID የሚለውን 65D እናደርግና ENTER ከመጡት አማራጮች ላይ የምንከፍተውኝ የቻናል ኪይ በማስገባት SAVE ብለን ENTER እንለዋለን ከዛ ቻናሉ ይከፍታል፡፡
LEG N24 - LEG A25 LEG H14 NURSAT 23500+
የምንከፍተው ቻናል ላይ FULL SCREEN ስናደርግ $CRAMBLE ሲለን ቀጥታ MENU ላይ BISS የሚለውን ሠማያዊ በተን ስንነካ ያመጣልናል ፡፡ከዛን ቀዩን ተጭነን ካስገባን በዋላ SAVE አድርገን እነወጣለን ከዛን ቻናሉ ይከፍታል ማለት ነው ::
LEG N24 +
ሪሞታችን ላይ BISS የሚለውን በመጫን ማስገባት እንችላለን፡፡
LIFESTAR 1000 -LS 2000- LS V6 -LS V7
ሪሞት ኮንትሮሉ የኮከብ ሎጎ ያለበት ባለ 1 FLASH ( USB ) ከሆነ አረንጓዴ በተንን ሲጫኑ BISSKEY ይመጣል ከዛን በማስገባት መክፈት ይቻላል፡፡
ለባለ ሁለት FLASH መሠክያ ላላቸው ደግሞ GO TO ተጭነው BISSKEY ማስገባት ይችላሉ፡፡
LTIGER HIGH CLASS V2
ሪሞታችን ላይ F1 በመጫን ከዛን 333 በመጫን ማስገባት እነችላለን
STAR GOLD MINI
MENU በመንካት ከዛን 999 ስንነካ BISSKEY መሙያ ያመጣልናል፡፡ኪውን በማስገባት ቻናሉን መክፈት እንችላለን፡፡
ALL FREE SAT RECIVERS
BISS KEY መሙላት የፈለግነውን ቻናል ከከፈትን በዋላ በቅድምያ MENU ላይ እንገባለን ከዛ CONDITIONAL ACCESS የሚል አማራጭ በመፈለግ ስናገኝ 6666 አራት ጊዜ በመጫን ስንነካ KEY EDIT የሚለውንጋር በመሄድ ADD ካልነን በዋላ የቻናሉን KEY ሞልተን EXIT በማድረግ እንጨርሳለን ማለት ነው፡፡
LIFESTAR DUAL FLAS
LS 2350-LS 2425- LS 2020,3030,4040,LS 18HD ,LS 9300-LS 9200( ባለ ሁለት ፍላሽ የሚሠኩ )
GOTO የሚለውን በመንካት BISSKEY ማስገባት እንችላለን፡፡
LIFESTAR 8585,9090,6060,8080
በመጀመርያ ሪሞታችን ላይ F1 እና 000 እንጫናለን አዛን ACTIVE ሲሆንልን ከዛን በድጋሜ F1 + 333 ስንነካ BISSKEY ማስገብያ እናገኛለን ፡፡
TIGER E12 HD ULTRA RF
ይህ ሪሲቨር ላይ BISS ለመሙላት F1 በመጫን ከዛን ኮዱን በመሙላት መጠቀም እንችላለን፡፡
=========================

የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ https://t.me/nurudish
2.9K viewsƝƲƦƲ ሳይቴክ, edited  07:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-01-14 10:14:11 ሠላም ዉድ የኑሩ ሳይቴክ ተከታታዮች ዛሬ የአብዛኛው ሠው ጥያቄ ስለሆነው #BISSKEY /የተቆለፉ ቻናሎችን የምንከፍትበት መንገዶችን ልንገራችሁ
SUPER MAX 9300 ባለ 2ፍላሽ መሠኪያ

የምንፈልገውን ቻናል ከፍተን በመቀጠል MENUእንነካለን ከዛን 8ቁጥርን አራት ጊዜ ስንጫን የመሙያ ሳጥን ይመጣልናል ከዛን ለምሳሌ የ #TV_VARZISH የምንሞላ ከሆነ ABAFCD እንሞላለን ማለት ነው፡፡
SM 2425 HD,SM2350 Power Tech and SM 2560 Brilliant ,FT 9700 Diamond እና SM 9700 Gold Plus

የምንፈልገውን ቻናል እንክፈት በመቀጠል OK ስንነካ የቻናል ዝርዝሮች ይመጣልናል ከዛን ሪሞቱ ላይ ሰማያዊ በተን ስንነካ የbiss menuይመጣልናል okየሚለውን በመንካት ኮዱን ካስገባን በዋላ ሠማያዊ በተንን 2ጊዜ ስንነካ save ያደርግናል ማለት ነው፡፡
SM 9700 GOLD + CA HD
የፈለገንን ቻናል ከፍተን ሪሞቱ ላይ 9339 በመንካት ከሚመጡልን አማራጮች SSSP(twin) የሚለውን እንምረጥ ከዛን ቀይ በተንን በመንካት የቻናሉን ኮድ እናስገባና saveእናደርጋለን ከዛን ቻናሉ ራሱ ይከፍታል፡፡
SM 2550 HD CA MINI
በመጀመርያ ቻናሉን እንከፍታለን በመቀጠል ይህንን እንከተል MENU>CONDITIONAL>ACCESS>CA SETTING> KEY EDIT> BISS> PRESS OK ከዛን የበፊቱን ቁጥር አጥፍተን ADD(አረንጓዴ )በተንን እንንካ በመቀጠል ቁጥሩን ካስገባን በዋላ save እናደርጋለን፡፡

SM 9200 CA HD,SM2425 power plus,SM 9700 + HD

ቻናሉን እንከፍታለን በመቀጠል slow በተንን እና አንድ ቁጥርን 4ጊዜ በመንካት patch menu active እናድርግ፡፡በመቀጠል page - የሚለውን ስንነካ አዲስ window ይመጣልናል ከዛን ቁጥሩን ከሞላን በዋላ save አድርገን ሩሲቨሩን አጥፍተን ስናበራው ቻናሉን ይበረግድልናል፡፡
Eurostar EB 9600,9200,9300
እነኚህ ሪሲቨሮች ላይ BISS ለማስገባት MENU እንነካለን ከዛን ሠባትን 4ጊዜ (7777) እንነካለን ከዛ biss የሚል ይመጣልናል ok ብለን እናስገባና save እናደርጋለን
IBOX 3030 HD
ይህ ሪሲቨር ሁለት አይነት አገባብ አለው
የመጀመርያው መንገድ
በlatest software ሪሲቨሩን upgrade እናደርጋለን በመቀጠል ሪሞቱ ላይ የኢንተርኔት ምልክት ስንነካ patch menu open ሲለን yes እንለዋለን ከዛን ከዚህ እንወጣና AB- የሚለውን ስንነካ የBISS KEY box መሙያ ይመጣልናል ከዛን ቀይ በተን ስንነካ መሙላት እንችላለን ማለት ነው ፡፡ከዛን ቻናሉ ይከፈለ፡ታል ማለት ነው፡፡ በዚህ ካልሆነ
#ሁለተኛው_መንገድ

ሪሞቱ ላይ የኢንተርኔት ምልክት ስንነካ patch menu open ሲለን yes እንለዋለን በመቀጠል manualy key የሚለውን አማራጭ እንነካለን፡፡በመቀጠል ከላይ በኩል ከተደረደሩት ኪዎች ትተን የጎን አቅጣጫ በመንካት bisskey የሚል እስኪያመጣልን ድረስ እንሔዳለን ከዛን Add የሚለውን ቀይ በተን እንነካለን ከዛ 3መደብ ላይ ቢጫ በመጫን መሙላት ከዛን save እናደርጋለን ከዛን በመመለስ ፍሪኩዌንሲ symbol rate አስገብተን ማየት እንችላለን፡፡
CORNOT HD RECIVERS
ቻናሉን እንከፍታለን በመቀጠል ሪሞታችን ላይ ሠማያዊ በተን እንነካና KEY እናስገባለን ማለት ነው ፡፡
LIFE STAR 6060 & 8080
መጀመርያ የሪሲቨሮቹን ሶፍትዌር ከጫንን በኋላ የምንፈልገው ቻናል ላይ በማድረግ በቅድሚያ ሪሞቱ ላይ “F1+000” በመንካት patch menu active እናደርጋለን ከዛ ሪሞቱ ላይ “F1+333” በመንካት Bisskey ማስገባት እንችላለን፡፡
HD WORLD RECIVERS
የተቆለፈዉ ቻናል $ ላይ ማድረግ
ቀጥሎ ሪሞቱ ላይ { 0000 } አራት መንካት ኮዱን ምንሞላበትን ያመጣልናል Biss Key ዉን መሙላት ነው ።
LIFE STAR 4040
መጀመሪያ ምንከፍተዉ ቻናል $ ላይ ማድረግ ቀጥሎ ሪሞቱ ላይ { 0000 } አራት ግዜ መንካት ኮዱን ምንሞላበትን ያመጣልናል Biss key ዉን መሙላት ነው።
SM F18 HD RECIVER
በመጀመርያ የሪሲቨሩን ሶፍትዌር መጫን በመቀጠል PAGE - በመንካት BISSKEY ማስገባት እንችላለን ፡፡
GSKY V6 RECIVERS
በመጀመርያ የPOWER VU SOFTWATE መጫኑን ማረጋገጥ በመቀጠል MENU ገብተን CONDITIONAL ACCESS የሚለውን እነጫናለን ከዛን KEY የሚለውን BISSKEY እናገኛለን፡፡በመቀጠል ADD እንነካለን PROVIDER ID የሚለውን 65D እናደርግና ENTER ከመጡት አማራጮች ላይ የምንከፍተውኝ የቻናል ኪይ በማስገባት SAVE ብለን ENTER እንለዋለን ከዛ ቻናሉ ይከፍታል፡፡
LEG N24 - LEG A25 LEG H14 NURSAT 23500+
የምንከፍተው ቻናል ላይ FULL SCREEN ስናደርግ $CRAMBLE ሲለን ቀጥታ MENU ላይ BISS የሚለውን ሠማያዊ በተን ስንነካ ያመጣልናል ፡፡ከዛን ቀዩን ተጭነን ካስገባን በዋላ SAVE አድርገን እነወጣለን ከዛን ቻናሉ ይከፍታል ማለት ነው ::
LEG N24 +
ሪሞታችን ላይ BISS የሚለውን በመጫን ማስገባት እንችላለን፡፡
LIFESTAR 1000 -LS 2000- LS V6 -LS V7
ሪሞት ኮንትሮሉ የኮከብ ሎጎ ያለበት ባለ 1 FLASH ( USB ) ከሆነ አረንጓዴ በተንን ሲጫኑ BISSKEY ይመጣል ከዛን በማስገባት መክፈት ይቻላል፡፡
ለባለ ሁለት FLASH መሠክያ ላላቸው ደግሞ GO TO ተጭነው BISSKEY ማስገባት ይችላሉ፡፡
LTIGER HIGH CLASS V2
ሪሞታችን ላይ F1 በመጫን ከዛን 333 በመጫን ማስገባት እነችላለን
STAR GOLD MINI
MENU በመንካት ከዛን 999 ስንነካ BISSKEY መሙያ ያመጣልናል፡፡ኪውን በማስገባት ቻናሉን መክፈት እንችላለን፡፡
ALL FREE SAT RECIVERS
BISS KEY መሙላት የፈለግነውን ቻናል ከከፈትን በዋላ በቅድምያ MENU ላይ እንገባለን ከዛ CONDITIONAL ACCESS የሚል አማራጭ በመፈለግ ስናገኝ 6666 አራት ጊዜ በመጫን ስንነካ KEY EDIT የሚለውንጋር በመሄድ ADD ካልነን በዋላ የቻናሉን KEY ሞልተን EXIT በማድረግ እንጨርሳለን ማለት ነው፡፡
LIFESTAR DUAL FLAS
LS 2350-LS 2425- LS 2020,3030,4040,LS 18HD ,LS 9300-LS 9200( ባለ ሁለት ፍላሽ የሚሠኩ )
GOTO የሚለውን በመንካት BISSKEY ማስገባት እንችላለን፡፡
LIFESTAR 8585,9090,6060,8080
በመጀመርያ ሪሞታችን ላይ F1 እና 000 እንጫናለን አዛን ACTIVE ሲሆንልን ከዛን በድጋሜ F1 + 333 ስንነካ BISSKEY ማስገብያ እናገኛለን ፡፡
TIGER E12 HD ULTRA RF
ይህ ሪሲቨር ላይ BISS ለመሙላት F1 በመጫን ከዛን ኮዱን በመሙላት መጠቀም እንችላለን፡፡
=========================
አዲሱን ቻናላችንን ኑሩ ቤተሰብን ይቀላቀሉ @nurubeteseb
2.4K viewsƝƲƦƲ ሳይቴክ, 07:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-01-13 09:54:54
ብዙ ጊዜ የምንመለከተው #ቻናል ሲቆራረጥብን የኬብላችን ኮኔክተር የላላ ስለሚመስለን አየነቀልንና እየሰካን ቻናል ለማምጣት ጥረት እናደርጋለን ።
በርግጥም የኮኔክተር መላላት የቻናል መቆራረጥ ችግር ሊያመጣ ይችላል ነገር ግን በዚህ ወቅት ቀጫጭን ስቲንገሮችና አሉሚኒየሙ ከመዳቡ የመሀለኛው ወፍራም ሽቦ ጋር ግንኙነት እንዳይፈጥር ጥንቃቄ ማድረግ አለብን ።
በስህተት ከተገናኙ ሪሲቨራችን ላይ ችግር ይፈጠራል ቻናሎቹም አይሰሩም።
ስለዚህ ሁሌም ኮኔክተር በምንሰካበት ወቅት ሁሉም ቀጫጭን ስቲንገሮችና አሉሚኒየም ፎይሉ ወደኋላ መሆናቸውን ማረጋገጥ ይጠበቅብናል። (በይበልጥ ለመረዳት ምስሉን ይመልከቱ)
እጅግ በጣም ቀላል ስህተት ነገር ግን ትልቅ ችግር!


ቴሌግራማችን http://t.me/nurudish/
2.5K viewsƝƲƦƲ ሳይቴክ, 06:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-01-12 08:55:03 ስልኮዎ በቫይረስ መጠቃቱን እንዴት ማወቅ ይችላሉ ?
How to tell if your android phone is infected by virus or malware?
በተለይ ቁጥር 6. ጠቃሚ ምልክት ነው!
ለዛሬ ይዘንላቹህ የመጣነው ስልኮዎ በቫይረስ መጠቃቱን እንዴት ማወቅ ይችላሉ ስልኮዎንስ ከቫይረስ እንዴት ነጻ ማድረግ እንደሚችሉ የሚያሳይ ትምህርት ነው መልካም ቆይታ
-ስለ ሞባይል እና ኮምፒውተር መረጃ -
ስልኮዎ በቫይረስ መጠቃቱን እንዴት ማወቅ ይችላሉ ?
1፡በስልኮዎ ውሰጥ ያሉ ፐሮግራሞቸ አልከፍት ይላሉ
2፡በሚሞሪ ካርድዎ እና በስልክዎ ውስጥ ያሉ የራስዎ ፋይሎች ራሳቸውን ይቀይራሉ በተለይ ደግሞ በቫይረስ የተጠቃው ስልክዎ ከሆነ ፋይሎችን አልያ ሶፍትዌሮችን ለመክፈት ሲሞክሩ application not supported or file dasn’t exist የሚል ሜሴጅ ሊመጣ ይችላል
3፡የስልክዎ የባትሪ ጉልበት በጣም እየደከመ ይመጣል ይሀ ምልክት ግነ በኖርማልስልኮች ላይም ሊስተዋል ይችላል ያ የሚሆነው ደግሞ የሚጠቀሙት ባትሪ ኦርጅናል ባለመሆኑና በሌሎችም ችግሮች ሊሆን ይችላል ለምሳሌ የስልክዎ ባትሪ ኮኔክተር ችግር ካለበት ባትሪዎን ቶሎ ቶሎ ይጨርስቦታል
4:ምናልባት ስልክ ደውለው እያናገሩ እያለ አልያ ደግሞ ገና እየደወሉ እያለ ስልክዎ ይቋረጣል :(ይህም ሌላ ምክነያትሊኖረው ይችላል ለምሳሌ የስልክዎ ስክሪን ችግር ካለበትና ስልክዎ ባጋጣሚ የሚጠፋ ከሆነ፣የባትሪዎ ችግርም ሊሆን ይችላል
5: በስልክዎ ላይ በጫኑት አፕልኬሽን እየተጠቀሙ እያሉ ፕሮግራሙ በራሱ ጊዜ ሊዘጋቦ ይችላል
6: እንደ አጠቃላይ ልናየው የምንችለው ደግሞ የስልክዎ ነገራቶችን በፍጥነት የመከወን ብቃት እጅጉን ይቀንሳል ተሰላችተ እስከመወርወር ድረስ ሊያናድድዎም ይችላል
ስለምለክቶቹ ይህን ያክል ካልን እንዴት መከላከል እንዳለብንና እንዴትስ ሁነቱ ከተከሰተ በኋላ ማስወገድ እንደምንችል አንዳንድ ነገራቶችን እንጥቀስ
*ስለ ሞባይል እና ኮምፒውተር መረጃ *
1፡ ኢንተርኔት እየተጠቀሙ እያለ ከሆነ ክስተቱ የተፈጠረው ስልክዎን ወዲያውኑ አጥፍተው ያብሩት/ ያስነሱት ይህን ማድረግዎ ኦንላይን የተለቀቁ ቫይረሶች በስልክዎ ላይ ለውጥ ማምጣት እንዳይችሉ ይረዳወ ዘንድ ነው
2:የተጠራጠሩትን ፕሮግራም ከሞባይልዎ ሾርትከት ላይ ለማጥፋት ይሞክሩ ይህ አልሆን ካለ
3:ከስልክዎ ውሰጥ setting የሚለውን በተን ተጭነው app የሚለውን ጠቅ ሲያደርጉ ብዙ ፕሮግራሞች ይታያሉ ከነኛ መካከልእርስዎ የተጠራጠሩትን ያጥፉት select and then press uninstall
4: ከ setting ሳይወጡ ወደሆላ በመመለስ security የሚለውን ይምረጡ ከዚክ ጋ device adminstartore የሚለውን ይጫኑትና በ ቼክ ቦክስ cheekbox ቲክ የተደረጉትን በሙሉ አጥፍተው ስልክዎን ሪስታርት ያድርጉት ምናልባት ስልክዎ ቫይረስ ከሌለው ይህኛው አማራጭ በ ቼክ ቦክስ cheekbox ቲክ የተደረጉነ ፕሮግራሞችን ላያመጣይችላል
5.ስልኮን አጥፍተው የድምፅ መቀነሻው ይጫኑና እሲከበራ አይልቀቁ በዚህን ጊዜ ስልኮ ሴፍ ሞድ የሚል ፅሁፍ ያመጣልናል: ይህ የሚጠቅመን አልጠፋም ያሉ የቫይረስ አፕሊኬሽኖችን ከሴቲንግ መተግበሪያ ውስጥ በቀላሉ ለማጥፋት ነው::
ስልካችን በቫይረስ ከተጣቃ ምን ማደረግ አለብን?
1፡ ኢንተርኔት እየተጠቀሙ እያለ ከሆነ ክስተቱ የተፈጠረው ስልክዎን ወዲያውኑ አጥፍተው ያብሩት/ ያስነሱት ይህን ማድረግዎ ኦንላይን የተለቀቁ ቫይረሶች በስልክዎ ላይ ለውጥ ማምጣት እንዳይችሉ ይረዳወ ዘንድ ነው
2:የተጠራጠሩትን ፕሮግራም ከሞባይልዎ ሾርትከት ላይ ለማጥፋት ይሞክሩ ይህ አልሆን ካለ
3:ከስልክዎ ውሰጥ setting የሚለውን በተን ተጭነው app የሚለውን ስትጫኑ ሲያደርጉ ብዙ ፕሮግራሞች ይታያሉ ከነኛ መካከልእርስዎ የተጠራጠሩትን ያጥፉት select and then press uninstall
4: ከ setting ሳይወጡ ወደሆላ በመመለስ security የሚለውን ይምረጡ ከዚክ ጋ
device adminstartore የሚለውን ይጫኑትና በ ቼክ ቦክስ cheekbox ቲክ የተደረጉትን በሙሉ አጥፍተው ስልክዎን ሪስታርት ያድርጉት ምናልባት ስልክዎ ቫይረስ ከሌለው ይህኛው አማራጭ በ ቼክ ቦክስ cheekbox ቲክ የተደረጉነ ፕሮግራሞችን ላያመጣይችላል
5.ስልኮን አጥፍተው የድምፅ መቀነሻው ይጫኑና እሲከበራ አይልቀቁ በዚህን ጊዜ ስልኮ ሴፍ ሞድ የሚል ፅሁፍ ያመጣልናል: ይህ የሚጠቅመን አልጠፋም ያሉ የቫይረስ አፕሊኬሽኖችን ከሴቲንግ መተግበሪያ ውስጥ በቀላሉ ለማጥፋት ነው::
6.የተለያዩ anti-virus application መጠቀም።
2.7K viewsƝƲƦƲ ሳይቴክ, 05:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-01-11 11:39:22 ስልክዎ እንደተጠለፈ የሚያሳዩ ሰባት ምልክቶች
▃▃▃▃▃▃▃▃▃▃▃▃▃

1. የስልክዎ ፍጥነት ከቀነሰ

ተንቀሳቃሽ ስልክዎ ከሌላው ጊዜ በተለየ ትዕዛዞችን ለማከናወን ረዘም ያለ ጊዜ የሚፈጅ ከሆነ፤ ባዕድ ሶፍትዌሮች (ማልዌር) እያስቸገሩት ነው ማለት ነው።

እነዚህ ማልዌር የተባሉት ቫይረሶች ዋነኛ ሥራቸው የስልክዎን አጠቃላይ እንቅስቃሴ ማዘግየት ሊሆን ስለሚችል፤ በአፋጣኝ ማስወገድ ተገቢ ነው።

2. ስልክዎ በጣም የሚግል ከሆነ

ስልክዎት ከተለመደው ከፍ ባለ ሁኔታ የሚግል ከሆነ፤ ችግር አለ ማለት ነው። በፍጥነት እርምጃ ይውሰዱ አልያም ባለሙያ ያማክሩ።

3. የስልክዎ የባትሪ ኃይል ቶሎ የሚያልቅ ከሆነ

ስልክዎ ከፍተኛ ሙቀት አለው ማለት ደግሞ የባትሪው ኃይል ቶሎ ቶሎ ያልቃል ማለት ነው።

ምናልባት ስልክዎ አዳዲስ መተግበሪያዎችንና ሶፍትዌሮችን ለማደስ በሚሞክርበት ወቅት የባትሪውን ኃይል ሊጨርስ ይችላል። ነገር ግን ምክንያቱ ይህ ካልሆነ ስልክዎ ተጠልፎ ሊሆን እንደሚችል ማሰብ አለብዎ።

4. ወደ ማያውቁት ሰው መልዕክት ከተላከ ወይም ከማያውቁት ሰው መልዕክት ከደረስዎ

ብዙ ጊዜ እርስዎ የማያውቋቸው መልእክቶች የሚላኩት በዋትሳፕና በመሳሰሉ መተግበሪያዎች በኩል ሲሆን፤ የሚላከው ደግሞ ወደ ጓደኛዎት አልያም ወደ የማያውቁት ሰው ሊሆን ይችላል።

ወደ እርስዎ የሚላኩ መልዕክቶች ደግሞ ብዙ ጊዜ ይህንን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ የሚሉ ማሳሰቢያዎች ይበዟቸዋል።

5. ከበይነ መረብ የሚመጡ ድንገተኛ መልዕክቶች

ስልክዎን በመጠቀም በይነ መረብን (ኢንትርኔት) በሚያስሱበት ወቅት ወደ ሌላ ድረ-ገጽ የሚያሸጋግሩ መልዕክቶች በተደጋጋሚ የሚመጡ ከሆነ የስልክዎ መጠለፍ ነገር እውን ሊሆን ይችላል።

መልዕክቱን ሲጫኑ በአንድ ጊዜ ወደ ሁለትና ሦስት የድህ-ረገጾች አድራሻዎች የሚመራዎ ከሆነ በፍጥነት ይውጡ።

6. አጠራጣሪ መተግበሪያዎችና ገንዘብ ነክ ጥያቄዎች

አንዳንድ ጊዜ እርስዎ ያልገዙት ወይም ከበይነ መረብ ያላወረዱት መተግበሪያ ስልክዎት ላይ ሊመለከቱ ይችላሉ። ምናልባትም የሞባይል ዳታ እና የጽሁፍ መልዕክት ላይ የዋጋ ጭማሪም ሊያስተውሉ ይችላሉ።

የክሬዲት ካርድና የሞባይል ገንዘብ ማንቀሳቀሻ መንገዶችን የሚጠቀሙ ከሆነ ይህ ሁኔታ ለጠላፊዎች ምቹ አጋጣሚ ሊፈጥርላቸው ይችላልና ይጠንቀቁ።

ስለዚህ የይለፍ ቃሎችንና የግል መረጃዎችን ስልክዎት ላይ ባያስቀምጡ ይመረጣል፤ አልያም በጠላፊዎች እንዳይገኝ ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል።

7. ያልተለመዱ ድምጾች

የድምጽ ጥሪ በሚያደርጉበት ወቅት ያልተለመዱና ከዚህ በፊት ያልነበሩ ድምጾች የሚሰማዎት ከሆን ምናልባት ስልክዎ የጠላፊዎች ሰላባ ሆኖ ሊሆን ይችላል። ይባስ ብሎም የስልክ ጥሪዎችዎ እየተቀዱም ሊሆን ይችላል።

━━━━━━━━━━━━━━
━━━━━━━━━━━━━━━


መፍትሄዎች
━━━━━━
የስልክ ማጽጃዎችን ከታማኝ ምንጭ ማግኘት

እርስዎ የማያውቋቸውን . መተግበሪያዎች ከስልክዎ ማጥፋት

ብዙ ሰው የሚጠቀማቸው ነጻ የኢንተርኔት አገልግሎቶችን አለመጠቀም

ስልክዎን በቀላሉ ሊታወቅ በማይችል የይለፍ ቃል መዝጋት

ከማይታወቁ ምንጮች መተግበሪያዎችን አለመጫን

ስልክዎና በስልክዎ ላይ ያሉ መተግበሪያዎችን ቶሎ ቶሎ ማሳደስ (update)

የስልክ ክፍያዎንና የዳታ አጠቃቀምዎን ይቆጣጠሩ

❖ ውድ የ ኑሩ ሳይቴክ ቤተሰቦች ድጋፋችሁን ቻናላችንን ሼር በማድረግ እንድትተባበሩን በትህትና እንጠይቃለን።
Please Give me credit when you make copy paste!
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
❍«ሺ» ሆነን እንደ«1» አንድ ሆነን እንደ «ሺ»❍ እንመራለን #ለተሻለ_ለዉጥ_እንሰራለን !!!
የቴሌግራም ቻናላችን
╔═══════════╗
@nurudish
@nurudish
@nurudish
╚═══════════╝
━━━━━━⊱✿⊰━━━━━━

🇳 🇺🇷 🇺 Sci-Tech
2.8K viewsƝƲƦƲ ሳይቴክ, 08:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-01-10 17:37:07 ብዙ ጊዜ ሞባይል ስንገዛ የምንገዛውን ሞባይል ጥራት ለመለየት ስለምንቸገር በቅርብ ያገኘነውን ሰው በመጠየቅ በምስክርነት እንወስናለን ፡፡
የስሞች መብዛትም አንዱ ችግር ነው፡፡ሳምሰንግ ፣ኖኪያ፣ ኤልጂ፣አፕል፣ወዘተ ወዘተ እየተባለ ይሄ ያ ይበልጣል ሙግትም አለ፡፡
እስቲ ለዛሬ ከሞባይል ቀፎ መሰረታዊ ማወዳደሪያ መስፈርቶች ውስጥ ጥቂቶቹን እንይ፡፡
የመጀመሪያው የሞባይል ቀፎ ማወዳደሪያ ኦፕሬቲንግ ሲስተሙ ነው። ለምሳሌ ሳምሰንግ አንድሮይድን ና ቴክኖ አንድሮይድን ይጠቀማሉ እንበል፡፡ ኦፕሬቲንግ ሲስተማቸው አንድሮይድ መሆኑ በሞባይል ቀፎዎች መሀል ያለውን ያገልግሎት ጥራት፣ ከዘመነው (አፕዴት ቴክ ) ጋር ያለውን መግባባትና ችሎታ፣ለቫይረስ ያለመጋለጥ ብቃትን ጨምሮ ከከባድ ድረ ገጽና አፕሊኬሽን ጋር ተጣጥሞ የመስራት አቅሙን ማሳየቱ ጥቂቶቹ መገለጫዎቹ ናቸው፡፡ ባጠቃላይ የሞባይል ቀፎን ባሕርይ ወሳኝ ምዕራፍ ኦፕሬቲንግ ሲስተሙ ነው፡፡ ከሞባይል ቀፎ አንፃር አንድሮይድ ባሁኑ ወቅት ከዊንዶው እና ማክ የተሻለ የኪስን አቅም ባማከለ መልኩ ተቀባይነት እያገኘ ነው፡፡
ሁለተኛው ማነፃፀሪያ ደግሞ ዋይ ፋይ፣ ብሉቱዝ፣ ዩኤስቢ፣ ጂፒኤስ፣፣ 2G፣ 3G፣ 4G የመሳሰሉትን መያዙና በተጨማሪም ሁለትና ከዚያ በላይ ሲም መቀበሉ ሲሆን ከዚህም በላይ ኖርማል ሲም ጂ ኤስ ኤም እና ruim (cdma sim ) ባንድ ላይ መያዙ ነው፡፡ የፋይል አደረጃጀት ስርአታቸው ለአጠቃቀም ቀላል መሆንና እንደፈለግነው መቀየር መቻሉና ምቹ መሆናቸው ደግሞ ሌላው መለኪያ ነው ፡፡
ለምሳሌ ተች ስክሪን፣ ስክሪን ጋድጌትስን መቀይር መቻሉና በፋይል ማናጀር በምንፈልገው መንገድ መቆጣጠር በሚያስችል መንገድ ‘እንደዚህ ሁንልኝ’ ስንለው የሚሆንልን ስማርት ፎን ደስ አይልም ?
ሶሰተኛው ማነፃፀሪያ የራሱ የሞባይሉ ሜሞሪ ( ፎን ወይም ኢንተርናል ሜሞሪ) ምንለው ነው፡፡ ይህ ሜሞሪ አቅሙ በጨመረ ቁጥር ዋጋውም አብሮ መጨመሩ እሙን ሲሆን ለቀፎዎች የዋጋ ልዩነት መሰረትም አንዱ ምክንያት ነው፡፡ ቀፎዎች የምንከትላቸውን የውጭ ሜሞሪዎችና አብሮአቸው የተሰራውን ሜሞሪ ባንድ አይነት ስለማይጠቀሙ በፍጥነት፣ በጥራትና በአቅማቸው ላይ የሚያመጣው ልዩነት ትልቅ ነው፡፡ ቀፎዎች (TIF card)ቲፍ ካርድና ኤስዲ(SD card) ካርድን(ሞባይላችን ላይ ምንከታቸው ሜሞሪዎች ማለቴ ነው) ሲጠቀሙ ፍጥነታቸው ዝቅተኛ ከመሆኑም በላይ የሚጭኑት አፕሊኬሽን ውስንና ቀጥታ ፍሰት (Real Time access) ነው፡፡ ስለዚህ ቀፎ ስንገዛ የራሱን ሜሞሪ አቅም ማስተዋል ግድ ይላል፡፡
አራተኛው የሞባይል ቀፎ ማወዳደሪያ ‘ፎን ክሎክ’ የሞባይል ቀፎውን ሲስተም ሃርድዌር ፍጥነት ሚወስን ነው። ለምሳሌ ድረ ገፅ ላይ አንድ ሞባይል ያለምንም መቆራረጥ ከዩቱብ ወይንም ከኛው ድሬትዩባችን ላይ ቪዲዮ ቢያጫውት የክሎክ ፍጥነቱንና የቢዩልት ኢን ሜሞሪን(phone memory) ጥራት ያሳያል፡፡ በተጨማሪ ቪዲዮ ኮሊንግ ያለችግርና (ፍሪዝ) በእስካይፒ መጠቀም ከቻልን በርግጥም የቀፎዎችን ግሩም ጥራት ያሳየናል፡፡ እዚህ ጋር ከግንዛቤ ውስጥ እንዲገባልኝ ምፈልገው አሁን ያለው የአገራችን የኔትዎርክ ችግር በቀፎው እንዳይሳበብ የኔትዎርኩን ሁኔታም ማየት መልካም መሆኑን ነው፡፡
አምስተኛ የባትሪ ጥራትና ቆይታ ነው ፡፡ አንዳንድ ሞባይሎች ባትሪ ሙጥጥ አያረጉ ‘‘እረ የቻርጀር ያለህ!’’ እያሰኙ ስንቱን አስጨንቀዋል፡፡ በርግጥ የሞባይል አቅምና ያገልግሎት ጥራት በጨመረ ቁጥር ባትሪ አጠቃቀምም አብሮ ቢጨምርም ብዙ ሞባይል አምራቾች የሞባይል ባትሪ ጥራትን በማሻሻል እነዚህ ቀፎዎች ለ18 ሰኣት አንዲያገለግሉ አርገው ሰርተውልናል፡፡
ሌላው ባትሪን በተመለከተ ማየት ያለብን የተሻለ ሞባይል ለመግዛት የባትሪ ማኔጅመንት ፕሮቶኮል አውቶማቲክና ማኑዋል አማራጭ እንዳለው ማጣራት ነው፡፡ የባትሪ ቀበኛ ከሆኑት ስክሪን ብራይትነስና ቫይብሬት ቴክኖሎጂን ጨምሮ ከጀርባ ሳናያቸው የሚስሩ አፕሊኬሽኖች መኖር፣ ቫይረስና አንቲ ቫይረስ ማኔጅ ማድረግና የመሳሰሉትን መቆጣጠሪያ ሶፍት ዌር መጫን የባትሪን ቀይታ ለማራዘም የምጠቁመው ተጨማሪ መፍተሄ ነው። በመጨረሻም የተሻለ ሞባይል ለመያዝ ከላይ ከጠቀስኳቸው በተጨማሪ ኢሜይል፣የጽሑፍ መልዕክት፣ካሜራ ጥራት፣ ምቾት፣ሰክሪን ስፋትና የተመረተበትን ቀን ማረጋገጡ ጠቃሚ ነው፡፡
2.7K viewsƝƲƦƲ ሳይቴክ, 14:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-01-08 10:38:41 ድንገት እንኳን በዛገ ቆርቆሮ ወይም ሚስማር የመቆረጥ ወይም የመወጋት አደጋ ቢገጥመን የመንጋጋ ቆልፍ በሽታ ተጠቂ እንዳንሆን በፍጥነት በአልኮል በተነከረ ንፁህ ጥጥ የተቆረጠውን የሰውነታችን ክፍል በማከም በቁስል ፕላስተር አሽገን በአቅራቢያችን ወደሚገኝ የህክምና ተቋም መሄድ ይኖርብናል፡፡
-በክረምት ወራት በዝናብ ምክኒያት በሚኖር ርጥበት መሰላሎችና ጣራ ላይ አዳልጦን የመውደቅ አደጋ እንዳይደርስብን ርጥበቱ ሙሉ በሙሉ ተወግዶ እንኪደርቅ ድረስ መጠበቅ ይኖርብናል፡፡ በበጋና እጅግ ፀሀያማ በሆነ ወቅት በፀሀይ ብርሃን ምክኒያት የቆርቆሮ ጣራዎች በተለይም ከ ረፋዱ 5፡30 ሰአት ጀምሮ እስከ ቀትሩ 9፡30 እጅግ ከፍተኛ ሙቀትና ግለት ስለሚፈጥሩ ስራችንን በአግባቡና በተዝናኖት እንዳናከናውን ከፍተኛ የሆነ መሰናከል ሊሆኑብን እንደሚችል ግልፅ ነው በመሆኑም በተቻለ መጠን ከተጠቀሱት ሰአታት ውጭ ባሉት ጊዜያት ስራችንን በአግባቡና በተረጋጋ መንፈስ ማድረግ ይሮርብናል፡፡ በከፍተኛ ሙቀት ላይ ጣራ ላይ ወጥቶ ለረጅም ጊዜ መቆየት የአይን ብዥታን፣ያልታሰበ በአፍንጫ ውስጥ ደም መውረድ (ነስር) ፣ ራስ ማዞርና የእይታ በከፊል መጋረድ፣ ከባድ ራስ ምታትና ማናጃይትስ ወይም ማጅራት ገትር እንደሚያስከትል ጥናቶች ይጠቁማሉ፡፡ ወደ አለባበሳችን ደግሞ ስንመጣ እግራችንን እንደፈለግን የሚያንቀሳቅሱንን ሱሪዎችንና (እንደ ቱታ ያሉ) በቀለማቸው ሙቀትን የማይስቡ (ከጥቁር ከነጭ ውጭ የሆኑ) ነፀብራቅን የማይፈጥሩ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡ ጫማዎቻችን የታችኛው ሶላቸው በደንብ መሬት መቆንጠጥ የሚችልና ሙቀት አዝልቀው የማያስገቡ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡ ኮፍያዎችን የፀሀይ ሙቀት ሃያል በሚሆኑባቸው ጊዜያቶች ማድረግ ጥቅሙ የጎላ ሲሆን ነገር ግን ኮፍያዎችን ለረጅም ጊዜ ማድረግ ራሰ በራነትን ሊያስከትል ስለሚችል አደራረጋችን ላይ ገደብ ልናበጅለት ይገባል፡፡
ማንኛውም የዲሽ ባለሞያ ሊኖረው የሚገቡ ስነ-ምግባራት:-
-ሁሉንም የህብረሰብ ክፍል ፍፁም ትህትና በተሞላበትና በቀና መንገድና በእኩል አይነት መንገድ ማስተናገድ
-በስልክም ሆነ በአካል ከማንኛውም የህብረሰብ ክፍል የሚመጡ ቅሬታዎችን በቅን አእምሮ ተቀብሎ በአግባቡ ትህትና በተሞላበት መልኩ ማስተናገድ
-ለሰራበት ስራ ተገቢውን የሆነ ክፍያ መጠየቅና በተቻለ መጠን በኢኮኖሚያቸው ዝቅተኛ ደረጃ ላይ ለሚገኙ የማህበረሰብ ክፍሎች አስተያየት በማድረግ መጠነኛ ክፍያ ማስከፈል
-አገልግሎት በሚሰጥበት ሰዓት የመጨረሻ አቅሙን ተጠቅሞ ጥራት ያለው የማያዳግም ስራ በመስራት ደንበኞቹን ለማርካት የላሰለሰ ጥረት ማድረግ፡፡ -ከአቅም በላይ ለሚሆኑ ችግሮች ቀደም ያለ ጥልቅ እውቀትና ግንዛቤ ላላቸው የስራ አጋሮች ግልፅ የሆነ ጥያቄ ማድረግ፡፡
-አገልግሎት እንዲሰጥ ጥሪ በሚደረግለት ሰዓት ቦታው ለመድረስ የሚወስድበትን ጊዜ ገምቶ ማሳወቅና በሰዓቱ መገኘት፡፡ በስራ መደራረብ ወይም በተለያያ ግላዊ ምክኒያቶች ደንበኞችን ማስተናገድ የማይችልበት ሁኔታ ሲከሰት ለሌሎች በቅርብ ለሚገኙ የስራ አጋሮቹ ማስተላለፍ ወይም እንደማይመቸው መግለፅ፡፡
-በገበያው ላይ የሚገኙትን ትክክለኛ የዲሽ እቃ ዋጋዎች ለህብረተሰቡ ግልፅ በማድረግ ግልፀኝነትን ማስፈን
-በራስ ላይ አደጋ ሊጥሉ የሚችሉ ወይም ተመሳሳይ ይዘት ያለቸውን ስራዎችን ለራስ ክብርና ለሀገሪቱ ህልውና ሲባል ባለመስራት የዜግነት ግዴታን መወጣት
-ባለው እውቀት ያለመመካትና ከሌሎች ዲሽ ቴክኒሻኖች ጋር ያለ ምንም ክፍያ የሚያውቁትን በግልፅ ማካፈልና በተለያዩ የመወያያ መድረኮች የሚገበዩትን እውቀት ለአጋር ባለሞያዎች በስፋት ማዳረስ፡፡
እና ሌሌች መልካም ስነምግባርን የሚያመላክቱ ስራዎችንና ባህሪያትን ማዳበር
ውድ አንባቢያን ከፅሁፉ መጠነኛ ትምህርት እንዳገኛችሁበትና እንደወደዳችሁት ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ በቀጣይ ከዚህ ፅሁፍ ጋር በተያያዘ ተከታታይ ፅሁፎችን በጥሩ ትንታኔ አጅበን ይዘን እንድንመጣ ያግዘን ዘንድ የፌስቡክ ገፃችንን ላይክ በማድረግ ኮሜንት በመፃፍና ኮፒ ፔስት ከማድረግ ታቅበው ይህንን ፅሁፍ ሼር በማድረግ ጥቂት አእምሮአዊ እርካታ እንድናገኝ እንዲረዱን በትህትና እንጠይቃለን፡፡ በቀጣይ አስተማሪ ፅሁፋችን እንስክንገናኝ ድረስ ሰላሙን ሁሉ ያብዛላችሁ
Like! Like! Like! Like! Like! Like! Like! Comment and Share!
ለበለጠ መረጃ ፣ለአዳዲስ ፍሪኩዌንሲዎች፣ ለትኩስ ቴክኖሎጂ ነክ መረጃዎች እና ለሞያ አዘል ፅሁፎች የቴሌግራም ቻናላችንን አሁኑኑ ይቀላቀሉ በርግጠኝነት ብዙ ነገር ይማሩበታል።

የቴሌግራም ቻናላችን https://t.me/nurudish
3.4K viewsƝƲƦƲ ሳይቴክ, edited  07:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-01-08 10:38:41 ዲሽ አተካከል ለፍፁም ጀማሪዎችና ለተካኑ የዲሽ ቴክኒሺያኖች

ዲሽ ለመጀመሪያ ጊዜ ለመትከልና ለመግጠም የተሰማሩ የዲሽ ባለቤት ግለሰቦች ፡ ጀማሪ ወይም ልምድ ያላቸው ቴክኒሺያኖች መያዝ የሚገባቸው የሳተላይት ዲሽ መግጠሚያ መሳሪያዎችና አጠቃቀማቸው፡-
– ማንኛውም የሳተላይት ዲሽ ቴክኒሺያን በቅድሚያ የሚገጥመውን የሳተላይት ዲሽ አይነትና አቅጣጫ በአትኩሮትና በበቂ ሁኔታ ከምንም በላይ መገንዘብ ይኖርበታል፡፡
– በአብዛኛው በሃገራችን የሚገጠሙና ስርጭታቸው በሰፊ ከሚገኙ የሳተላይት ዲሽ ቻናሎች ለመጥቀስ ያህል በየቤታችን የሚገኘውና እጅግ ብዙ ተጠቃሚዎች ያሉት የናይልሳትና ከ 5 እና 6 አመታት በፊት ሁሉም የሀገራችን ብሎም ተወዳጅ የውጭ ቻናሎች ይገኙበት የነበረው አሁን በአረቡ አለም ዘንድ ብቻ በስፋት በጥቅም ላይ የሚውለው የአረብሳት ቻናል እና ነፃ የኳስ ቻናሎች ማለትም ቨርዛሽ ቲቪ፣ ቶሎዶ ቲቪ እና ሌሎችን የእንግሊዝና ስፔን ላሊጋ ብሎም፣ የቻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታዎችን የሚያስተላልፉ ቻናሎች የሚገኙባቸው የያህሳት ቻናል ዲኤስቲቪ እና የ ፓወር ቪዩ ቻናሎች የሚገኙ ሲኖን እንደ አንድ የሳተላይት ዲሽ ጀማሪም ሆነ የተካነ ቴክኒሺያን ማወቅ ከሚገቡን ነገሮች መካከል የእያንዳንዱን ቻናል አቅጣጫና አቀማመጥ ነው፡፡ እነዚህን ቻናሎች በአግባቡ ለመትከል እንዲረዳን የአቅጣጫ ጠቋሚ ማለትም ኮምፓስ መጠቀም በብዛት የሳተላይት ዲሾችን ለመግጠም ጥቅሙ እጅግ ከፍ ባለ ደረጃ የሚረዳን ሲሆን አጠቃቀሙን በቀጣይ ፅሁፋችን ከፍተኛ አትኩሮት ወደምንሰጥበት መሰረታዊ ፅንሠ ሃሳቦች ጋር ይዘን በሰፊው እንመለስባቸዋለን፡፡
– ማንኛውም የሳተላይት ዲሽ ለመትከል የተዘጋጀ ጀማሪም ሆና የተካነ ባለሙያ መያዝ ያለባቸው እጅግ መሰረታዊና የምንጊዜም አጋዠ መሳሪያዎች መካከል የሚከተሉትን መዘርዘር ይቻላል፡፡
በተለምዶ አስር ቁጥር ብለን የመንጠራው የብሎን መፍቻ ለባለ 60 ሴንቲሜትር ሳህንና (ለ 90 ሲንቲሜትርና ከዛ ክፍ ለሚሉ የዲሽ ሳህኖች፣ 10 ቁጥርን ጨምሮ እንደአስፈላጊነቱ 10፣11፣12፣ እና ከዚያ በላይ ያሉት መፍቻዎች በተናጠል ወይም (በህብረት) ማለትም በአንድ የብረት ዘንግ ሶስቱንም በስሩ የያዘ መፍቻ ወይም ከአነስተኝ እስከ ከፍተኛ የብሎን አናት ቁጥሮችን በማጥበቅና በማላላት የምንጠቀምበት በተለምዶ ካበ እንግሊዝ (Wrench) ብለን የምንጠራውን ባለ አንድ ወጥ በጣት በማሽከርከር እንደ ብሎኑ አናት መጠን የሚጠብና የሚሰፋ መፍቻ በቅርብ ከሚገኝ የህንጻ መሳሪያ መደብር መግዛትና ሁሌም ዲሽ ለመትከልም ሆነ ለማስተካለል በምንቀሳቀስበት ጊዜና ቦታ መያዝ፡፡
የሚቻልና አቅማችን ከፈቀደ (በተለይ ዲሽ መትከልን እንደ ዘላቂ ሙያ ለያዡ) ሙሉ በሙሉ ዲጂታል የሆነ የሳተላይት ማሰሻ ወይም Finder በመግዛት ለአስፈላጊው ስራ መዘጋጀት፡፡ አቅም የማይፈቅድ ከሆነም ቆየት ያለውን ነገር ግን ላዩ ላይ ዲጅታል ፋይንደር የሚል ፅሁፍ ያለውንና ከ 0 እስከ 10.5 ዲ.ቢ የሚለካውን ባለ ሜትሩን የሳተላይት ዲሽ ማሰሻ ከ 400 ብር ባልበለጠ ገንዘብ በአካባቢያችን በሚገኙ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች መሸጫ መደብሮች መግዛትና መያዝ፡፡ ለስራችን ቅልጥፍና የሚረዳን የመጀመሪያው አይነት ዲጅታል ፋይንደር ሲሆን የራሱ የሆነ የባትሪ ሀይል ስላለው መብራት እንኳን ቢጠፋ ጣራ ላይ ባለንበት ስራችንን ለመጨረስ ያስችለናል በተጨማሪም የፋይንደሩ ሰሌዳ ላይ ልክ ሪሲቨሩ ላይ እንደምናየው ሲግናልና ኳሊቲ ማንበቢያ ስላለውና የምንፈልጋቸውን የቻናል ፍሪኩዌንሲዎች ሞልቶ ስለሚይዝልን ስራችንን እጅግ ፈጣን ያደርግልናል፡፡ እጅግ በጣም የሚያስፈልገን ከሆነ ደግሞ በአንገት የሚንጠለጠል የምናስሰውን ቻናል በፋይንደሩ ሰሌዳ ላይ ልክ እንደ ቴሌቪዥን ምስሉን በጥራት የሚያሳይ ድምፁንም በጥራት የሚያሰማ ሲግናልና ኳሊቲ ማንበቢያ ያለው እጅግ ዘመናዊ የሆነ ፋይንደር ገዝተን ስራችንን በጣም በዘመናዊ መልኩ ማካሄድ እንችላለን፡፡
-ከ ፋደራችን አይነትና አቅም ጋር የሚሄድ ተወርዋሪ ገመድ ከዲሹ ጋር ከሚመጣው RG-6 Coaxial Cable (የዲሽ ገመድ) ወይም ከቴሌቪዥን የውጭ አንቴና ጋር ከሚመጡ በውስጣቸው ቀጭን የኮፐር ወይም መዳብ ዘንግ ከያዙ ገመዶች ቆርጦ ርዝመቱ ከ 60 ሳንቲሜትር ያላነሰ ተወርዋሪ ገመድ (Jump Caple) በሁለቱም በኩል የሴቴ ወይም (Female Connector) የያዘ ገመድ ማዘጋጀት፡፡ የገመዱ ጫፍ አንደኛው ወደ የዲሹ ጭንቅላት (LNB) ላይ የሚታሰር ሲሆን ሌሌኛው ጫፍ ፋይንደሩ ላይ (To LNB) በሚለው አቅጣጫ የሚታሰር ይሆናል፡፡ የፋይንደርን አጠቃቀም ወደ ፊት ሰፋ ያለ ትንታኔ የምንሰጥበት ስለሆነ ለዛሬው እዚህ ላይ እንግታው፡፡
-ተወርዋሪ ገመድ ወይም ከዲሹ ጋር አብሮ የሚመጣውን ገመድ ጫፎች ለመላጥ፣ Female Connector ችን ለማያያዝ፣ ገመዶችን ለማሳጠር ወይም ለመቀጠልና ለማስረዘም እንዲረዳን አንድ ጥሩ የሆነ ፒንሳ ያስፈልገናል፡፡ በአቅራቢያችን ማግኘት የምንችል ከሆነ ደግሞ ኬብል ስትሪፐር ወይም ኬብል ከተር መግዛት ስራችንን ቀልጣፋ ያደርግልናል፡፡
-የዲሹን LNB ማቀፊያ ለማጥበቅና ለማላላት ብሎም LNB ለመቀየርና አዳፕተሮችን ለመፈታታትና ለማጥበቅ ሊረዳን የሚችል በሁለቱም በኩል ሲቀያያር ጠፍጣፋና ባለ መስቀል አናት የሚሰጥ ካቻቢቴ መያዝ ይጠበቅብናል፡፡
-የዲሹን ሳህን እግር በሁለት አቅጣጫ ረዘም ካሉ ጣውላዎች ጋር መምቻና የዲሹን ገመዶች በየግድግዳው በኬብል ክሊፕ ለማያያዝና ሌሎች ጠንከር ያለ ሀይል የሚጠይቁ ስራዎችን ለማከናወን የሚጠቅመንን አጠርያለ የፕላስቲክ እጀታ ያለው መዶሻ ያስፈልገናል፡፡
ከላይ የጠቀስናቸው መሳሪያዎች እጅግ መሰረታዊና አስፈላጊ ሲሆኑ ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ደግሞ አስፈላጊነታቸው በጣም ብዙም ባይሆን እንኳን መያዛችን ግን ጥቅሙ እጅግ ያመዘነ ይሆናል፡፡
-በማንኛውም ሁኔታ ቢሆን ሊጠቅሙን ስለሚችሉ በርከት ያሉ የ Female connector, Audio Video Splittor Conector ንና ከሁለት ያላነሱ Disqe Switch መያዝ፡፡
-እንደየ ፍላጎታችን የምንሞላውን ሳተላይት መሠረት ያደረጉ የተለያዩ ፊሪክዌንሲዎችና፣ ፖላራይዜሽሮች ዝርዝር በጥንቃቄ ለማወቅ ይረዳን ዘንድ እና አዳዲስ መረጃዎችን በማይረሱ መልኩ ለመፃፍና በአስፈላጊ ጊዜ ዋቢ ለማድረግ ለመፃፊያነት የሚረዱን መጠናቸው እንደየ ግል ፍላጎታችን በሚወሰኑ ማስታወሻ ደብተሮች ላይ ማስፈር፡፡ ለዚህም ይረዳን ዘንድ ለአያያዝ አመቺ የሆኑ ማስታወሻ ደብተሮችን በአቅራቢያችን ከሚገኙ የፅህፈት መሳሪያ መደብሮች ገዝቶ መያዝ፡፡
-የስራው ባህሪ ሆኖ ብዙዎች ተገልጋዮችን የምናገኛቸው በተንቀሳቃሽ ሞባይል ስልኮች ከመሆኑ የተነሳ የኔትወርክ ግኑኝነት በማይኖረበት ቦታ የኔትወርክ ግኑኝነትን አስሰውና ፈልገው የሚያመጡልንን ዘመኑ ኖርማል ሀንድሴት ብሎ የሚጠራቸውን ግን በባትሪ ቆይታቸውና ጣበት ወቅት ከፍተኛ ጥንቃቄዎችን ማድረግ ይገባናል፡፡
-ምንም እንኳን የተቻለንን ጥንቃቄ ብናደርግም በተለያየ የስራ አጋጣሚ ሊደርሱብን የሚችሉ ቀለል ያሉ ጉዳቶች ሊኖሩ ይችላሉ፡፡ በመሆኑም አንድ አነስ ያለች የመጀመሪያ ህክምና እርዳታ መስጫ መሳሪያዎችን የያዘች ሳጥን ቢኖረን እጅግ በጣም ጥሩ ነው፡፡ በውስጧም በርከት ያሉ የቁስል ፕላስተሮች፣ ንፁህ ጥጥ፣ ፋሻ፣ የተጠቀለለ ነጭ የቁስል ፕላስተር፣በፕላስቲክ ጠርሙስ የታሸገ አልኮል (በተለምዶ ጂቢ የምንለው) እና ሌሌችንም የያዘች ብትሆን እጅግ በጣም ተመራጭ ነው፡፡ ያስታውሱ ምንጊዜም ቢሆን ለጥንቃቄ ቅድሚያ መስጠት ይኖርብናል፡፡
2.8K viewsƝƲƦƲ ሳይቴክ, 07:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ