Get Mystery Box with random crypto!

ድንገት እንኳን በዛገ ቆርቆሮ ወይም ሚስማር የመቆረጥ ወይም የመወጋት አደጋ ቢገጥመን የመንጋጋ ቆል | ƝƲƦƲ ሳይቴክ

ድንገት እንኳን በዛገ ቆርቆሮ ወይም ሚስማር የመቆረጥ ወይም የመወጋት አደጋ ቢገጥመን የመንጋጋ ቆልፍ በሽታ ተጠቂ እንዳንሆን በፍጥነት በአልኮል በተነከረ ንፁህ ጥጥ የተቆረጠውን የሰውነታችን ክፍል በማከም በቁስል ፕላስተር አሽገን በአቅራቢያችን ወደሚገኝ የህክምና ተቋም መሄድ ይኖርብናል፡፡
-በክረምት ወራት በዝናብ ምክኒያት በሚኖር ርጥበት መሰላሎችና ጣራ ላይ አዳልጦን የመውደቅ አደጋ እንዳይደርስብን ርጥበቱ ሙሉ በሙሉ ተወግዶ እንኪደርቅ ድረስ መጠበቅ ይኖርብናል፡፡ በበጋና እጅግ ፀሀያማ በሆነ ወቅት በፀሀይ ብርሃን ምክኒያት የቆርቆሮ ጣራዎች በተለይም ከ ረፋዱ 5፡30 ሰአት ጀምሮ እስከ ቀትሩ 9፡30 እጅግ ከፍተኛ ሙቀትና ግለት ስለሚፈጥሩ ስራችንን በአግባቡና በተዝናኖት እንዳናከናውን ከፍተኛ የሆነ መሰናከል ሊሆኑብን እንደሚችል ግልፅ ነው በመሆኑም በተቻለ መጠን ከተጠቀሱት ሰአታት ውጭ ባሉት ጊዜያት ስራችንን በአግባቡና በተረጋጋ መንፈስ ማድረግ ይሮርብናል፡፡ በከፍተኛ ሙቀት ላይ ጣራ ላይ ወጥቶ ለረጅም ጊዜ መቆየት የአይን ብዥታን፣ያልታሰበ በአፍንጫ ውስጥ ደም መውረድ (ነስር) ፣ ራስ ማዞርና የእይታ በከፊል መጋረድ፣ ከባድ ራስ ምታትና ማናጃይትስ ወይም ማጅራት ገትር እንደሚያስከትል ጥናቶች ይጠቁማሉ፡፡ ወደ አለባበሳችን ደግሞ ስንመጣ እግራችንን እንደፈለግን የሚያንቀሳቅሱንን ሱሪዎችንና (እንደ ቱታ ያሉ) በቀለማቸው ሙቀትን የማይስቡ (ከጥቁር ከነጭ ውጭ የሆኑ) ነፀብራቅን የማይፈጥሩ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡ ጫማዎቻችን የታችኛው ሶላቸው በደንብ መሬት መቆንጠጥ የሚችልና ሙቀት አዝልቀው የማያስገቡ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡ ኮፍያዎችን የፀሀይ ሙቀት ሃያል በሚሆኑባቸው ጊዜያቶች ማድረግ ጥቅሙ የጎላ ሲሆን ነገር ግን ኮፍያዎችን ለረጅም ጊዜ ማድረግ ራሰ በራነትን ሊያስከትል ስለሚችል አደራረጋችን ላይ ገደብ ልናበጅለት ይገባል፡፡
ማንኛውም የዲሽ ባለሞያ ሊኖረው የሚገቡ ስነ-ምግባራት:-
-ሁሉንም የህብረሰብ ክፍል ፍፁም ትህትና በተሞላበትና በቀና መንገድና በእኩል አይነት መንገድ ማስተናገድ
-በስልክም ሆነ በአካል ከማንኛውም የህብረሰብ ክፍል የሚመጡ ቅሬታዎችን በቅን አእምሮ ተቀብሎ በአግባቡ ትህትና በተሞላበት መልኩ ማስተናገድ
-ለሰራበት ስራ ተገቢውን የሆነ ክፍያ መጠየቅና በተቻለ መጠን በኢኮኖሚያቸው ዝቅተኛ ደረጃ ላይ ለሚገኙ የማህበረሰብ ክፍሎች አስተያየት በማድረግ መጠነኛ ክፍያ ማስከፈል
-አገልግሎት በሚሰጥበት ሰዓት የመጨረሻ አቅሙን ተጠቅሞ ጥራት ያለው የማያዳግም ስራ በመስራት ደንበኞቹን ለማርካት የላሰለሰ ጥረት ማድረግ፡፡ -ከአቅም በላይ ለሚሆኑ ችግሮች ቀደም ያለ ጥልቅ እውቀትና ግንዛቤ ላላቸው የስራ አጋሮች ግልፅ የሆነ ጥያቄ ማድረግ፡፡
-አገልግሎት እንዲሰጥ ጥሪ በሚደረግለት ሰዓት ቦታው ለመድረስ የሚወስድበትን ጊዜ ገምቶ ማሳወቅና በሰዓቱ መገኘት፡፡ በስራ መደራረብ ወይም በተለያያ ግላዊ ምክኒያቶች ደንበኞችን ማስተናገድ የማይችልበት ሁኔታ ሲከሰት ለሌሎች በቅርብ ለሚገኙ የስራ አጋሮቹ ማስተላለፍ ወይም እንደማይመቸው መግለፅ፡፡
-በገበያው ላይ የሚገኙትን ትክክለኛ የዲሽ እቃ ዋጋዎች ለህብረተሰቡ ግልፅ በማድረግ ግልፀኝነትን ማስፈን
-በራስ ላይ አደጋ ሊጥሉ የሚችሉ ወይም ተመሳሳይ ይዘት ያለቸውን ስራዎችን ለራስ ክብርና ለሀገሪቱ ህልውና ሲባል ባለመስራት የዜግነት ግዴታን መወጣት
-ባለው እውቀት ያለመመካትና ከሌሎች ዲሽ ቴክኒሻኖች ጋር ያለ ምንም ክፍያ የሚያውቁትን በግልፅ ማካፈልና በተለያዩ የመወያያ መድረኮች የሚገበዩትን እውቀት ለአጋር ባለሞያዎች በስፋት ማዳረስ፡፡
እና ሌሌች መልካም ስነምግባርን የሚያመላክቱ ስራዎችንና ባህሪያትን ማዳበር
ውድ አንባቢያን ከፅሁፉ መጠነኛ ትምህርት እንዳገኛችሁበትና እንደወደዳችሁት ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ በቀጣይ ከዚህ ፅሁፍ ጋር በተያያዘ ተከታታይ ፅሁፎችን በጥሩ ትንታኔ አጅበን ይዘን እንድንመጣ ያግዘን ዘንድ የፌስቡክ ገፃችንን ላይክ በማድረግ ኮሜንት በመፃፍና ኮፒ ፔስት ከማድረግ ታቅበው ይህንን ፅሁፍ ሼር በማድረግ ጥቂት አእምሮአዊ እርካታ እንድናገኝ እንዲረዱን በትህትና እንጠይቃለን፡፡ በቀጣይ አስተማሪ ፅሁፋችን እንስክንገናኝ ድረስ ሰላሙን ሁሉ ያብዛላችሁ
Like! Like! Like! Like! Like! Like! Like! Comment and Share!
ለበለጠ መረጃ ፣ለአዳዲስ ፍሪኩዌንሲዎች፣ ለትኩስ ቴክኖሎጂ ነክ መረጃዎች እና ለሞያ አዘል ፅሁፎች የቴሌግራም ቻናላችንን አሁኑኑ ይቀላቀሉ በርግጠኝነት ብዙ ነገር ይማሩበታል።

የቴሌግራም ቻናላችን https://t.me/nurudish