Get Mystery Box with random crypto!

ሞባይል ዳታ በሚከፈትበት ጊዜ ካርድ ወይም የተሞላውን የዳታ ጥቅል በቶሎ የሚጨርስበት ምክንያትቶችና | ƝƲƦƲ ሳይቴክ

ሞባይል ዳታ በሚከፈትበት ጊዜ ካርድ ወይም የተሞላውን የዳታ ጥቅል በቶሎ የሚጨርስበት ምክንያትቶችና መፍትሔዎች:

ምክንያቶች :-
1.የሞባይል ዳታ ተከፍቶ ሲረሳና ሳይዘጋ ሲቀር
2.ኢንተርኔት ክፍት ሆኖ ከተለያዩ ደህረ ገፆች ላይ ቀጥታ ቪዲዮች ሲታዩ
3.System settings እና Applications በራሳቸው ጊዜ አፕዴት ሲያደርጉ
4.በሞባይሉ ላይ የሚገኙ አፕሊኬሽኖች ተጠቃሚው በማያቸው መንገድ ከበስተጀርባ ሲሰሩ
5.በሞባይል ስልኩ ውስጥ ቫይረስ ሲኖር
---------------------------
መፍትሔዎች :-
ሞባይል ዳታ ተከፍቶ ሲረሳና ሲቆይ እንደ ሶሻል ሚዲያና ኦንላይን የሚሰሩ አፕሊኬሽኖች ከተጠቃሚው እይታ ውጪ ስራቸውን ያከናውናሉ። በዚህ ጊዜ በሞባይሉ ላይ የተሞላው ክሬዲት ሰዓት ይቀንሳል ወይም ያልቃል ስለዚህም ኢንተርኔት ተጠቅመው ከጨረሱ በኋላ የሞባይሉን ዳታ ያጥፉ።

በሞባይል ዳታ ኢንተርኔት ከፍቶ ከተለያዪ ድህ ገፆች ላይ በቀጥታ ቪዲዮ መመልከት የተሞላውን ካርድ መጠን በጊዜ ከሚያሳጥሩት ነገሮች ወስጥ አንደኛው ሲሆን ለዚህም ዋነኛው
ምክንያት በኢንተርኔት ቪዲዮ ቀጥታ መመልከት የሚቆጥረው የዳታ መጠን ከፍተኛ ስለሆነ ነው ስለዚህ ቪዲዮ ማየቱ ግዴታ ከሆነ በ Vidmate እና በሌሉች ቪዲዮ ዳውሎደር አፕሊኬሽኖች የቪዲዮ ይዘት በመቀነስ ጭኖ መመልከቱ ወጪን
ይቆጥባል።

System settings እና Application በራሳቸው ጊዜ አፕዴት ሲያደርጉ የተሞላውን ዳታ(ካርድ) ይወስዳሉ ታዲያ ይህን ለማስቀረት Free wifi ከተገኘ አፕዴት ማድረግ ይህ ማድረግ የማይቻል ከሆነ system settings አፕዴት እንዳያደርግ ማስቆም:
Settings ----About----Software Update---
Automatic update የሚለውን ማጥፋት
Applications አፕዴት እንዳያደርጉ ከተፈለገ ደግሞ
-Google Play መክፈት.
- hamburger የሚመስለውን በለ ሶስት ሆሪዞንታል ምልክት ያለበትንም አናት ላይ በስተግራ በኩል Settings በመንካት
Auto-update apps.- disable automatic app updates, የሚለውን በመክፈት እና በመምረጥ መዝጋት
ይቻላል

በሞባይሉ ላይ የሚገኙ አፕሊኬሽኖች ተጠቀሚው በማያቸው መንገድ ከበስተጀርባ ሲሰሩ ከእይታ ውጪ በመሆን የክሬዲት መጠን ይቀንሳሉ ታዲያ ይህን ለመከላከል:
Settings----
data usage ---Restricted Background data
የሚለውን መክፈት... ከዚህ ይበልጥ ደግሞ Mobile data
saver አፕሊኬሽኖች በመጫን መጠቀም

በሞባይል ሰልክ ውስጥ ቫይረስ ሲኖር የተሞላውን ሞባይል
ዳታ ከመቅስፈት እድሜው እንዲያጥር ያደርጋል ብሎም ቫይረሱ በራሱ ጊዜ የሞባይሉን ኦፕሬቲንግ ሲስተም በማዘዝ ያለማንም ትዕዛዝ ዳታ ይከፍታል ዳውንሎድ ያደርጋል አላስፈላጊ ነገሮችና ማስታወቂያዋች ይለቃል ከዚህም የተነሳ በፍጥነት የሞባይል ካርድ( ዳታ ጥቅል) ይጨርሳል ይህ ነገር በሞባይሉ ላይ ቢከሰት አንቲ ቫይረስ በመጫ ሰካን ማድረግ ይህ መፍትሔ የማይሆን ከሆነ ለባለሙያ ማሳየቱ ተገቢ ነው::

መረጃዎች ቶሎ ቶሎ እንዲደርሳችሁ ቻናላችንን #Mute ያደረጋችሁት #UNMUTE በማድረግ ተባበሩን "

የዩቲዩብ ቻናላችንን Subscribe በማድረግ የቴክኖሎጂ እውቀትዎን ያሳድጉ!



https://www.youtube.com/channel/UCr1PSR41Dom6j2qYe80LxjQ?

▬▬▬ Share ▬▬▬▬