Get Mystery Box with random crypto!

#አሮጌ_ስልክን_እንደ_ሴኩይሪቲ_ካሜራነት_እንዴት_መጠቀም_እንችላለን? አዲስ ሞባይል ስልክ ስንገዛ | ƝƲƦƲ ሳይቴክ

#አሮጌ_ስልክን_እንደ_ሴኩይሪቲ_ካሜራነት_እንዴት_መጠቀም_እንችላለን?

አዲስ ሞባይል ስልክ ስንገዛ አሮጌው ስልክ ይቀመጣል(ካልሸጥነው)። ነገር ግን አሮጌውን ስልክ እንደ ሴኩሪቲ ካሜራነት ልንጠቀምበት እንችላለን።

ለምሳሌ አንድ ጨቅላ ህፃን ያላት እናት ልጇን ቤት ለሰራተኛ ትታ ወደ ስራ ስትሄድ ትጨነቃለች። ስራ ላይ ሆኗ "ልጄ እንዴት ይሆን..." እያለች ስትጨነቅ ትውላለች። ነገር ግን አሮጌ ስልክ ካላት አሮጌውን ስልክ ቤት አንድ ጥሩ ቦታ ታስቀምጠውና አሁን በምትጠቀምበት ስልኳ አማካኝነት ስራ ቦታዋ ሆና የልጇን ሁኔታ መከታተል ትችላለች። ይህ ብቻ አይደለም ቤቷ ማን መጥቶ እንደነበረ፣ቤቷ ውስጥ ምን እየተካሄደ እንደሆነ መከታተል ትችላለች።

ይህ አንድ ምሳሌ ነው። አሮጌው ስልክ ሴኩሪቲ ካሜራ በማድረግ ለተለያዩ ጉዳዬች ልትጠቀሙበት ትችላላችሁ።

እንዴት? ቀላል ነው። እነዚህን ስቴፖች በመከተል አሮጌውን ስልክ ሴኪዩሪቲ ካሜራ ማድረግ እንችላለን።

1ኛ፦ Seecitv የሚል አፕሊኬሽን አለ። ነፃ ነው።ይህንን አፕሊኬሽን ሁለቱም ስልኮች(አሮጌው እና አዲሱ) ላይ እንጭነዋለን።

የአፕሊኬሽኑ ሊንክ ይሄው፦ https://play.google.com/store/apps/details?id=com.code.bluegeny.myhomeview

2ኛ፦ አፕሊኬሽኑ ዳውንሎድ አድርጎ ሲጨርስ #Start ላይ ክሊክ ማድረግ።ከዚያም #Viewer የሚለውን መምረጥ። በመጨረሻ #Next የሚለውን ክሊክ ማድረግ ።

3ኛ፦ 2ኛውን ስቴፕ ስትጨርሱ "Sign in with google" የሚል ይመጣል።በጎግል አካውንታችሁ Sign in ማድረግ

4ኛ፦ 2ኛ ስቴፕ ላይ የተጠቀሱትን አሮጌው ስልክ ላይም ታደርጋላችሁ። ነገር ግን አዲሱ ስልክ ላይ #Viewer ብለን መርጠናል።አሁን አሮጌው ስልክ ላይ #Camera የሚለውን እንመርጣለን

5ኛ፦ በቃ አለቀ።አሁን አሮጌውን ስልክ አንድ ጥሪ ቦታ መርጦ ማስቀመጥ።

የቴሌግራም ቻናላችን https://t.me/nurudish
Via dotcomshow