Get Mystery Box with random crypto!

የኮምፒውተር ቫይረስ ሰለባ መሆንዎን እንዴት ማወቅ ይችላሉ 1 ድንገተኛ የሆነ የአገልግሎት መቋረጥ፡ | ƝƲƦƲ ሳይቴክ

የኮምፒውተር ቫይረስ ሰለባ መሆንዎን እንዴት ማወቅ ይችላሉ
1 ድንገተኛ የሆነ የአገልግሎት መቋረጥ፡ ከዚህ ቀደም ድንገተኛ የሆነ የአገልግሎት መቆራረጥ አጋጥሞዎት በተደጋጋሚ ሰማያዊ ቀለም ያለው ገጽታ የሚያሳይ ከሆነ ኮምፒውተርዎ አደጋ ላይ መውደቁን ጠቋሚ ነው፡፡
2. የኮምፒውተር ስርዓት ማዝገም /Slow System/፡ በሲስተምዎ ላይ ብዙ ቦታ የማይፈልጉ መተግበሪያዎችን(applications)
ሳይጠቀሙ የኮምፒውተር ስርዓቱ ዝግ ማለት የኮምፒውተርዎ ስርዓት በቫይረስ መጠቃትን ሊያመለክት ይችላል።
3. ከልክ ያለፈ የሃርድ ድራይቭ እንቅስቃሴ( 3. Excessive Hard Drive Activity) ምንም እንኳን ኮምፒተርዎ ስራ እየሰራ ባይሆንም ጥቂት የማይባሉ የሃርድ ድራይቭ እንቅስቃሴን ካስተዋሉ ይህ ምናልባትም በቫይረስ ስለመጠቃትዎ የማስጠንቀቂያ ምልክት ሊሆን ይችላል፡፡
4. ያልተለመዱ የዊንዶው ምልክቶች ሲስተዋሉ፡ ኮምፒውተርዎን በሚከፍቱበት ወቅት እንግዳ የሆኑ ነገሮች ብቅ ካሉ እና በተለይ በኮምፒተርዎ ላይ የተለያዩ ድራይቭዎች /drive/ ከጠፉ ችግር መፈጠሩን አመላካች ነው፡፡
5. የተለዩ መልእክቶች፡ በተለያዩ መልእክቶች ወደ እርስዎ የመልእክት መለዋወጫዎች ሲገቡ እና ፋይሎችን በሚከፍቱበት ጊዜ ካልተከፈተ የተፈጠረ ችግር አለ ማለት ነው፡፡
6. መጥፎ የፕሮግራም እንቅስቃሴ፡- ፕሮግራሞችዎ ከጠፉ ፣ ከተበላሹ ፣ ወይም ያለ እርስዎ ፍቃድ እራሳቸውን በራሳቸው መክፈት ከጀመሩ ፣ እንዲሁም ያለ እርስዎ ትእዛዝ ኢንተርኔት ለመድረስ እየሞከረ መሆኑን የሚገልጽ ማሳሰቢያ ከደረሰዎ ይህም የቫይረስ ሰለባ መሆንዎን ጠቋሚ ነው፡፡
7. የዘፈቀደ አውታረ-መረብ እንቅስቃሴ /Random Network Activity/ ምንም ጉልህ የሆኑ ፕሮግራሞችን ወደስራ ሳያስገቡ አልያም ከፍተኛ የበይነ-መረብ ዳታን በማይጠቀሙበት ጊዜ የእርስዎ ራውተር በቋሚነት ብልጭ ድርግም የሚል ምልክት የሚያሳይ ከሆነ ፣ የሆነ ችግር መፈጠሩን አመላካች ነው፡፡
8. የተሳሳቱ የኢሜይል መልእክቶች፡- እርስዎ ለማንም ኢ-ሜይል ባይልኩም ከእርስዎ የኢሜይል አድራሻ ለእርስዎ ኢ-ሜይል መልእክት ከደረስዎ የእርስዎ ስርዓተ ኮምፒውተር ተጥሷል (ወይም የኢ-ሜይል የይለፍ ቃልዎ እንደተሰረቀ የሚያሳይ ጠንካራ ማስረጃ ነው)
9. የአይፒ አደራሻዎ በበይነመረብ ፕሮቶኮል አድራሻ በጥቁር መዝገብ ከተቀመጠ/
Blacklisted IP Address/ የእርስዎ የአይፒ አድራሻ በጥቁር መዝገብ መያዙን የሚገልጽ ማስታወቂያ ከደረሰዎት ኮምፒተርዎ በጥሩ ሁኔታ ላይ አለመሆኑን የሚያሳይ ምልክት፡፡
10. ያልተጠበቀ የፀረ-ቫይረስ አገልግሎት መቆም፡- ብዙ ተንኮል-አዘል ሶፍትዌር /malware/ ፕሮግራሞች ፀረ-ቫይረስ አገልግሎት የማስተጓጎል ወይም ከጥቅም ውጪ የማድረግ ተልእኮ በመያዝ የተቀየሱ ናቸው፡፡ ስለሆነም የፀረ-ቫይረስ ስርዓትዎ በድንገት የማይሠራ ከሆነ የኮምፒውተር ስርዓቱ ትልቅ ችግር ላይ መውደቁን የሚያሳይ በመሆኑ የመፍትሄ እርምጃዎችን መውሰድ የግድ ይላል፡፡