Get Mystery Box with random crypto!

በስልካችን ኢንተርኔት በምንጠቀምበት ሰዓት ብዙ ብር እየወሰደ ካስቸገሮት ይሚከተለውን መፍትሄ ያንብ | ƝƲƦƲ ሳይቴክ

በስልካችን ኢንተርኔት በምንጠቀምበት ሰዓት ብዙ ብር እየወሰደ ካስቸገሮት ይሚከተለውን መፍትሄ ያንብቡ። ያነበቡትንም ለሌሎች ያጋሩ።
****  ሼር ማድረግ አይርሱ!!
*
መጀመሪያ የስልኮን በመክፈት Setting  Connection ( Wireless and networks) ከሚለው ስር Data usage የሚለው ውስጥ ስንገባ ኢንተርኔት በጣም የሚጠቀሙ አፕሊኬሽኖችን በደረጃ ተዘርዝረው ያገኟቸዋል። ሁሉንም አፕ በየተራ ይክፈቷቸው። Foreground (ከፍተው የተጠቀሙት) እና Background (ሳይታዩ አፕሊኬሽኑ በራሱ የተጠቀመው) ምን ያህል Mega Bytes እንደሆነ ይነግረናል፤ ከታች ደግሞ Limit background process የሚል አማራጭ አለ። ከእሱም ፊት ያለውን [ √ ] በማድረግ ካለ እኛ ፈቃድ አፑ ኢንተርኔት እንዳይጠቀም መከልከል እንችላለን። ወደ ሗላ እየተመለስን ሁሉንም Data usage ውስጥ የተዘረዘሩ አፖች እየከፈትን መዝጋት (Limit) ማድረግ የሚወስድብንን ብር መቀነስ እንችላለን። በተጨማሪም ሁሌም አዲስ አፕ በጫን ቁጥር እየገባን መዝጋት ይኖርብናል።
አንድሮይዳቸው ከ 4.0 በታች ለሆኑ Data usage የላቸውም፣ በዚህ ምትክ Setting  Accounts and Sync ገብተን Background data የሚለውን አለመምረጥ ።
በተጨማሪም Setting  Privacy የሚለውን በመክፈት Back up my data የሚለውን እንዲሁ አለመምረጥ።
ለHuawei ስልኮች Data usage
ለመግባት፣ Setting  wireless & Networks  more..  Data Usage ->
Restrict background data የሚለውን [ √ ] በማድረግ መምረጥ
Setting -> personal ከሚለው ስር Location access የሚለው ውስጥ ገብተን እሱን መዝጋት።
ይሄም ስልካችን ያለንበትን ቦታ ለማወቅ ኢንተርኔት እንዳይጠቀም ያደርጋል።
Setting -> Developer option (About phone ከሚለው ከፍ ብሎ ያገኙታል) የሚለውን ከፍተን ወደ ታች ስንወርድ Background Process limit የሚለውን እንክፈት። ይሄ ሁሌም ስልኩ በራሱ Standard Limit የሚለውን ይመርጠዋል። እዚህ ላይ No background process የሚለውን እንምረጥ። ሁሌም ስልካችንን አጥፍተን ካበራነው በራሱ ወደ Standard limit ስለሚቀየር እየገባን መቀየር ይኖርብናል። Standard Limit ላይ ከሆነ ቢያንስ እስከ 10 አፕሊኬሽኖች ያለ እኛ ፈቃድ ኢንተርኔት ጋ ይገናኛሉ ማለት ነው። ይሄም ከፍተኛ ገንዘብ ይወስዳል።
Developer option የሚለውን Setting ውስጥ ካጡት
የሚከተለውን ያድርጉ። Setting  About phone የሚለው ውስጥ እንግባና Build number የሚለውን 7 ጊዜ በፍጥነት እንካው። ከዚያ ሲመለሱ Setting ውስጥ About Phone ከሚለው ከፍ ብሎ Developer option ያገኙታል።
የስልካችን ሶፍትዌር ራሱን እንዳያድስ (update) መዝጋት።
ለዚህም Setting  About phone (device)  Software update ገብተን Auto update የሚለው
የተመረጠ ከሆነ [√] እሱን ማንሳት ወይንም አለመምረጥ።
GPS መዝጋት.
ኢንተርኔት ክፍት እንዳደረግን ኢንተርኔት የማይጠይቁ አፖችን (ጌም) አለመጠቀም። ይሄም አፖቹ ከአምራቻቸው ጋ በመገናኘት ፣ ማስታወቂያ እንዲመጣ በማድረግ የሚጠቀሙትን ኢንተርኔት ያስቀራል።
Play store በ Wi–fi ካልሆነ በስልካችን ኢንተርኔት አለመግባት።
Opera Mini የምንጠቀም ከሆነ Opera Setting ውስጥ Image quality የሚለውን Low quality ማድረግ። ይሄም ኦፔራ ፈጣን እንዲሆን እና ብዙ ገንዘብ እንዳይወስድ ያደርጋል።

የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ  https://t.me/nurudish