Get Mystery Box with random crypto!

#የዳታ_መቆጣጠሪያ_አፕሊኬሽን_ልጠቁማችሁ በሞባይል ስልካችን ኢንተርኔት ስንጠቀም የሚያሳስበን ዋና | ƝƲƦƲ ሳይቴክ

#የዳታ_መቆጣጠሪያ_አፕሊኬሽን_ልጠቁማችሁ

በሞባይል ስልካችን ኢንተርኔት ስንጠቀም የሚያሳስበን ዋናውና ትልቁ ነገር የዓየር ሰዓት(የሞባይል ካርድ) ወጪ ነው፡፡ የሞባይል ካርድ እየሞላን #ፌስቡክ፤#ዩቲዩብ፤#ኢንስተግራም፤#ቴሌግራም እና አንድ አንድ መረጃዎችን ብራውዝ እናደርጋለን፡፡

ነገር ግን ይበቀኛል ብለን የሞላነው የሞባይል ካርድ(በጥቅል መልኩም ይሁን በመደበኛ) ድንገት ሙልጭ ብሎ ያልቅና ያበሳጨናል፡፡

ለምንድን ነው የሞላነው ሞባይል ካርድ ቶሎ የሚያልቅብን?

1ኛ፡- የዓየር ሰዓትና የኢንተርኔት ጥቅል ዋጋ ውድ በመሆኑ፣

2ኛ፡- የኛ የአጠቃቀም ችግር፦

የመጀመሪያው ችግር አሁን ለግዜው ምንም ማድረግ አንችልም፡፡ ሁለተኛው ምክንያት ማለትም የኛ የአጠቃቀም ችግር ግን ማስተካከል ይቻላል፡፡

የአጠቃቀም ችግር ማለት ምን ማለት ነው?

ኢንተርኔት ስንጠቀም ቢያንስ 4 ዓይነት ኮንተንቶችን ብራውዝ እናደርጋለን፡፡ እነሱም #ቪዲዮ፤#ፎቶ፤#ሙዚቃ(ድምፅ)፤#ፁሁፍ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡እነዚህ ኮንተንቶች ዳታ አጠቃቀማቸው ይለያያል፡፡ ለምሳሌ #ቪዲዮና #ፎቶ እኩል ዳታ አይጠቀሙም፡፡#ቪድዮ የበለጠ ዳታ ይጠቀማል፡፡ስለዚህ #ቪዲዮ ውድ ነው ማለት ነው፡፡በተመሳሳይ መልኩ በኢንተርኔት #ሙዚቃ ከማዳመጥ እና የተለያዩ #ፁሆፎች ከማንበብ፤ሙዚቃ ማዳማጥ ይበልጥ ሞባይል ካርዳችንን ይበላል፡፡

ስለዚህ ኢንተርኔት ስንጠቀም የሞላነውን ካርድ የሚበሉብን ኮንተንቶች በቅደም ተከተል የሚከተለውን ይመስላሉ፡-

1ኛ፡- #ቪዲዮ
2ኛ፡- #ፎቶ
3ኛ፡- #ፁሁፎች…

የሆነ ፁሁፍ ለማንበብ ብለን ሞባይል ካርድ ሞልተን ኢንተርኔት መጠቀም ስንጀምር ፁሁፉን ትተን ቪዲዮ ማየት ከጀመርን(ቪዲዮ ብዙ ይበላል) ካርዱ ሲያልቅ ያሰብነውን ስላላረግን ያበሳጨናል፡፡

ስለዚህ ማቀድ ያስፈልጋል፡፡ከዚያም ያቀድነውን ማድረግ ያስፈለጋል ማለት ነው፡፡

ሞባይል ካርድ ሞልተን ኢንተርኔት ብራውዝ ስናደርግ ያቀድነውን ለማድረግ ዳታችንን መቆጣጠር ይኖርብናል፡፡ዳታ መቆጣጠር ማለት ለምሳሌ 1Gb ኢንተርኔት ጥቅል ሞልታችሁ ከሆነ ኢንተርኔት መጠቀም ስትጀምሩ ለምሳሌ ፌስቡክ ብራውዝ አድርጋችሁ ስትጨርሱ ከ1Gb ውስጥ ምን ያህል ቀረኝ የሚለውን መቆጣጠር ማለት ነው፡፡

የሞላችሁት የኢንተርኔት ጥቀል ለመቆጣጠር “Internet Speed Meter Lite” የሚባል አፕሊኬሽን አለ፡፡ ነፃ ነው፡፡ አፕሊኬሽኑን ዳውንሎድ ታደርጉታላችሁ፡፡ ከዚያ ስታስነሱት ዳታችሁን ይቆጣጠርላችኋል ፡፡

ይህ አፕሊኬሽን ፡-

1ኛ፡-ምን ያህል ዳታ እንደተጠቀማችሁ ወይም እየተጠቀማችሁ መሆኑን ይነግራችኋል፣

2ኛ፡-የትኛው አፕሊኬሽን ብዙ ዳታ እየበላባችሁ እንደ ሆነ ይነግራችኋል፡፡..ወዘተ

ስለዚህ በዚህ ዓይነት መልኩ ዳታችሁን እየተቆጣጠራችሁ እና እየቆጠባችሁ በመጠቀም ቢያንስ የሞላችሁትን ሞባይል ካርድ ድንገት ሙልጭ ብሎ ከማለቅ ትድናላችሁ፡፡

የአፕሊኬሽኑ ሊንክ ይሄው፡-
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.internet.speed.meter.lite

#ሼር_ይደረግ