Get Mystery Box with random crypto!

ጎንደር ዩኒቨርሲቲ አዲስ ሞዴል ፋርማሲ በይፋ ሥራ አስጀምሯል። ሞዴል ፋርማሲው የአካባቢውን ማህበ | Educate Ethiopia

ጎንደር ዩኒቨርሲቲ አዲስ ሞዴል ፋርማሲ በይፋ ሥራ አስጀምሯል።

ሞዴል ፋርማሲው የአካባቢውን ማህበረሰብ ከማገልገሉ በተጨማሪ ለበርካታ ወጣቶች የሥራ ዕድል እንደሚፈጥር የጎንደር ዩኒቨርሰቲ ፕሬዝዳንት አስራት አጸደወይን (ዶ/ር) ገልጸዋል።

ለጎንደር ዩኒቨርሲቲ የፋርማሲ ትምህርት ቤት መማሪያነትም እንደሚያገለግል ጠቁመዋል።

ሞዴል ፋርማሲው ማህበረሰብን እያገለገለ ገቢ እንዲያመነጭ የተቋቋመው "እቴጌ ምንትዋብ ንግድና ማማከር አገልግሎት ኢንተርፕራይዝ" አካል መሆኑ ተመላክቷል።

የኢንተርፕራይዙ መጠናከር ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ለሚያደርገው ራስ ገዝ (ኦቶኖመስ) የመሆን ጉዞ ወሳኝነት ይኖረዋል ተብሏል።

ለበለጠ ትምህርታዊ መረጃ @educate_ethiopia ቤተሰብ ይሁኑ

Credit: tikvah