2023-01-27 14:58:02
የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ በሰጡት መግለጫ ምን ምን ጉዳዮችን አነሱ ?
- በ2014 የትምህርት ዘመን ለፈተና የተመዘገቡ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች በጠቅላላ 985 ሺህ 354 ተማሪዎች ሲሆኑ ለፈተና የቀረቡት 92 ነጥብ 2 % 908 ሺህ 256 ተማሪዎቹ ሲሆኑ 77 ሺህ 98 ተማሪዎች ፈተና አልወሰዱም።
- በደንብ ጥሰት ፣ለመኮራረጅ በመፈለግ እና በሌሎች ምክንያቶች 50 ሺህ 170 ተማሪዎች ሳይፈተኑ ቀርተዋል።
- በ2014 የትምህርት ዘመን 899 ሺህ 520 ተማሪዎች ተፈትነዋል ።
- በፆታ ማዕከልነት የአማካይ ውጤት በወንዶች 30 ነጥብ 2 እንዲሁም ሴቶች 28 ነጥብ 09 % አማካይ ውጤት አስመዝግበዋል።
- በትምህርት ዘርፍ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ከማህበራዊ ሳይንስ በተሻለ ውጤት ያስመዘገቡ ሲሆን የተፈጥሮ ሳይንስ 31 ነጥብ 63 ከመቶ እንዲሁም የማህበራዊ ሳይንስ 27 ነጥብ 79 ከመቶ በአማካኝ አስመዝግበዋል።
- በክልል ደረጃ ይህየ ነው የሚባል የውጤት ልዩነት የሌለ ሲሆን አዲስ አበባ ፣ ሐረሪ እና ድሬደዋ ከተማ አስተዳደር የተሻለ ውጤት አስመዝግበዋል።
- ከተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ወንድ ከ 700፤ 666 ያስመዘገበ ሲሆን 650 ሴት ተማሪ አስመዝግባለች ።
- በማህበራዊ ሳይንስ ከ600 ወንድ 524 አስመዝግቧል።
- ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች በትምህርት ሚኒስቴር እውቅና እና ሽልማት ይሰጣቸዋል።
Credit : WMCC
4.9K views11:58