Get Mystery Box with random crypto!

' በደብዳቤው ላይ የተገለጹት ሁለት መልዕክቶች በ2014 ዓ/ም የሁለተኛ ደረጃ ማጠቃለያ ፈተና ላይ | Educate Ethiopia

" በደብዳቤው ላይ የተገለጹት ሁለት መልዕክቶች በ2014 ዓ/ም የሁለተኛ ደረጃ ማጠቃለያ ፈተና ላይ ይተገበራሉ " የትምህርት ሚኒስቴር

ከላይ ደብዳቤ የ2014 ዓ/ም የሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ያለውን የትምህርት ይዘት እንደሚሸፍን እንዲሁም የኢኮኖሚክስ ትምህርት ፈተና እንደማይሰጥ ይገልጻል።

በትምህርት ሚኒስቴር የስርዐተ ትምህርት ዝግጅትና ምርምር ጄነራል ዳይሬክተር ዶክተር ቴዎድሮስ ሸዋርገጥ ደብዳቤው ትክክለኛ መሆኑንና ለክልሎችና ለከተማ አስተዳደሮች መላኩን አረጋግጠዋል።

ዳይሬክተሩ በደብዳቤው ላይ የተገለጹት ሁለት መልዕክቶች በ2014 ዓ/ም የሁለተኛ ደረጃ ማጠቃለያ ፈተና እንደሚተገበሩም አጽኖት ሰጥተዋል።

በደብዳቤው ላይም ተማሪዎች ይህን አውቀው መዘጋጀት እንዳለባቸው ተጠቅሷል።

Credit : ኢትዮጵያ ቼክ

ለበለጠ ትምህርታዊ መረጃ @educate_ethiopia ቤተሰብ ይሁኑ