#MoE
የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና በ2015 ዓ/ም ተግባራዊ መሆን ይጀምራል።
ከዚህ ፈተና ጋር በተያያዘ በትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ልማት ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ የተናገረቱ ፦
" የመውጫ ፈተና ስትራተጂ የማዘጋጀት ስራ ተጠናቋል። ስትራቴጂውን ማስተግበሪያ መመሪያ በትምህርት ሚኒስቴር ተዘጋጅቷል።
ዝርዝር እቅድ ይህ የመውጫ ፈተና እንዴት ? ፤ መቼ ? ፤ በማን ? እንደሚሰጥ ፤ ፈተናው በማን እንደሚዘጋጅ ፤ የትምህርት ሚኒስቴር ሚና የዩኒቨርሲቲዎች ሚና ምን እንደሚመስል በዝርዝር ምላሽ የሚሰጥ የድርጊት መርሃ ግብር ተዘጋጅቷል።
የመውጫ ፈተና ሌላ ከውጪ የሚጫን ፈተና አይደለም። በስርአተ ትምህርቱ ውስጥ የተቀመጡትን የምሩቃኑን ፕሮፋይል መሳካት አለመሳካቱን ፤ መጨበጥ አለመጨበጡን የሚያረጋግጥ ነው። "
ለበለጠ ትምህርታዊ መረጃ @educate_ethiopia ቤተሰብ ይሁኑ