Get Mystery Box with random crypto!

የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች መሰጠት ተጀመረ የተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች የ1 | Educate Ethiopia

የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች መሰጠት ተጀመረ


የተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ማስፈተን ጀምረዋል።

በመደወላቡ፣ በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ፣ በጂማ፣ በኦዳ ቡልቱም እና ነቀምቴ ዩኒቨርሲቲዎች ተገኝተው እንደተመለከቱት ፈተናው ተጀምሯል።

ምልከታ ከተደረገበት መካከል አንዱ የመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ሲሆን ከ11 ሺህ የሚበልጡ ተማሪዎች መፈተን ጀምረዋል።

ለፈተና የሚያስፈልጉ ቅድመ ሁኔታዎችን ቀድመው መጠናቀቃቸውን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶ/ር አህመድ ከሊል ለኢዜአ ተናግረዋል።

ተፈታኞችን ለፈተና የሚያዘጋጁ አጠቃላይ ገለጻ እንደተደረገላቸውም ጠቅሰዋል።

ተማሪዎች የፈተና ሕጉን በመጠበቅ ተረጋግተው እንዲፈተኑም መክረዋል።

በዩኒቨርሲቲው የተመደቡ ተፈታኞች በበኩላቸው፣ በራሳችን ጥረት የተሻለ ነጥብ ለማስመዝገብ ተዘጋጅተናል ብለዋል።

አዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲም በተመሳሳይ ከ10 ሺህ በላይ ተማሪዎች ፈተና መውሰድ ጀምረዋል።

የጂማ ዩኒቨርሲቲም በሁሉም ካምፓሶቹ 25 ሺህ ተማሪዎችን ማስፈተን ጀምሯል።

የኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ ከ9 ሺህ በላይ ተመሪዎችን ማስፈተን ጀምሯል።

ምንጭ - ኢቢሲ