Get Mystery Box with random crypto!

ከ560 ሺህ በላይ ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና በመውሰድ ላይ ናቸው - ትምህርት ሚኒስቴር | Educate Ethiopia

ከ560 ሺህ በላይ ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና በመውሰድ ላይ ናቸው - ትምህርት ሚኒስቴር

በ130 ማዕከላት ከ560 ሺህ በላይ ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና በተረጋጋና በሰላም እየወሰዱ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር ገለጸ።

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እንዲሁም ሚኒስትር ዴኤታዎች የፈተናውን አጀማመርና አጠቃላይ ሂደት በሚመለከት መግለጫ ሰጥተዋል።

በዚህም በ130 ማዕከላት ከ560 ሺህ በላይ ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና በተረጋጋና በሰላም እየወሰዱ መሆኑን አብራርተዋል።

በሐዋሳ ዩኒቨርስቲ በዋናው ግቢ የሚገኝ ድልድይ ተደርምሶ በተወሰኑ ተማሪዎች ላይ አደጋ መድረሱንም ሚኒስትሩ ጠቁመዋል።

በአደጋው ጉዳት ለደረሰባቸው ተማሪዎች ሃዘናቸውን ገልጸው፤ በአደጋው ጉዳት ያጋጠማቸው ተማሪዎች ህክምና እየተደረገላቸው መሆኑን አስታውቀዋል።

በአደጋው ጉዳት የገጠማቸው ተማሪዎች ካገገሙ በኋላ ፈተናውን እንዲወስዱ ይደረጋል ብለዋል።

ከተጠቀሱት አካባቢዎች በስተቀር በሌሎች ትምህርት ቤቶች ግን ፈተናው በሰላምና በተረጋጋ መልኩ እየተሰጠ መሆኑን ሚኒስትሩ ገልጸዋል።

ምንጭ - ኢዜአ