Get Mystery Box with random crypto!

የጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ አህመድ(ዶ/ር) መልዕክት ለ12ኛ ክፍል ተፈታኞች የሀገራችን የነገ ተስፋ | Educate Ethiopia

የጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ አህመድ(ዶ/ር) መልዕክት ለ12ኛ ክፍል ተፈታኞች

የሀገራችን የነገ ተስፋዎች ሆይ

ኢትዮጵያ እናንተን ስታይ ተስፋ ነው የሚታያት። ይህ የምትፈተኑት የ12ኛ ክፍል ፈተና ለኢትዮጵያ እውነተኛ ተስፋዎች መሆናችሁን የምታረጋግጡበት እንደሚሆን አምናለሁ። እናንተን እዚህ ለማድረስ ወላጆች፣ መምህራን እና መላው ማኅበረሰብ ለዓመታት ለፍቷል። ውጤቱን የምታሳዩት ከኩረጃና ከስርቆት ነጻ ሆናችሁ፣ በራሳችሁ ተማምናችሁ፣ ፈተናውን ስትፈተኑ ነው።

የተሰጣችሁን መመሪያ አክብሩ፤ ተረጋግታችሁ ፈተናችሁን ሥሩ፤ በምንም አትሸበሩ፤ የኢትዮጵያ አምላክ ዕውቀቱን ይግለጥላችሁ።