Get Mystery Box with random crypto!

ብሒላተ አበው ወእመት ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ

የቴሌግራም ቻናል አርማ behlateabew — ብሒላተ አበው ወእመት ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ
የቴሌግራም ቻናል አርማ behlateabew — ብሒላተ አበው ወእመት ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ
የሰርጥ አድራሻ: @behlateabew
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 13.08K
የሰርጥ መግለጫ

የቀድሞ አበው እና እመት የተናገሯቸው መንፈሳዊ ጥበብ
"የእግዚአብሔር ልጅ ሰው የሆነው እኛ አማልክት ዘበጸጋ እንሆን ዘንድ ነው።"
ቅዱስ አትናቴዎስ
👇👇👇👇👇👇👇👇
👉 @behlateabew 👈
👉 @behlateabew 👈
👆👆👆👆👆👆👆👆
https://t.me/joinchat/AAAAAESAiVPCib48ZxL1Pw

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2023-06-12 15:22:04
371 views12:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-07 13:34:52
2ኛ ዙር ኦርቶዶክሳዊ የፆታ ትምህርት

ከ ሰኔ 4 ጀምሮ
ዘወትር እሁድ ከ10:00 እስከ 12:00
ለሦስት ወር
770 views10:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-05 13:32:06 //ወረደ መንፈስ ቅዱስ//

ሃሌ ሃሌ ሉያ ወረደ መንፈስ ቅዱስ/፪/
ላዕለ ሐዋርያት ከመ ዘእሳት/፪/

ትርጉም፡- ቅድመ ዓለም የነበረ አሁንም ያለ ዓለምን አሳልፎ የሚኖር መንፈስ ቅዱስ በሐዋርያት ላይ በእሳት አምሳል ወረደ፡፡
1.1K viewsedited  10:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-05 13:31:00 መዝሙር በእንተ ጰራቅሊጦስ
.
.///ሐዋርያት ተባበሩ

ሐዋርያት ተባበሩ
በአዲስ ቋንቋ እየተናገሩ
ቃሉን አስተማሩ/፪/

ከዐረገ በኋላ በዐሥረኛው ቀን
ወደ ዓለም ላከው ጰራቅሊጦስን
በዝግ ቤት ውስጥ ቆዩ ቀኑን ሲጠብቁ
የተሰጣቸውን ተስፋውን እስኪያውቁ

አዝ
ቀኑም ደረሰና ሃምሣኛው ዕለት
ተሰብስበው ሳሉ በአንድነት ጸሎት
መንፈስ ቅዱስ ታየ በነደ እሳት

አዝ
ያ የተናገረው ያ የተስፋ ቃል
ወረደ ከሰማይ በእሳት አምሳል
ጴጥሮስ አሳመነ ሦስት ሺ ነፍሳት
ያን ጊዜ ገሊላ በሰጠው ትምህርት

አዝ
ከሦስት አካል አንዱ መንፈስ ቅዱስን
ልኮ አናገራቸው ኹሉን በልሳን
1.0K views10:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-05 07:45:42 #ጾመ_ሐዋርያት

‹‹ይኽ ጾም በአላዋቂዎችን እና በቤተክርስቲያን ጠላቶች የሽማሌዎች ጾም እየተባለ ምዕመናን እንዳይጾሙት ብዙ ተለፍቷል..››

በየዓመቱ በዕለተ ሰኑይ የሚዠምሩ ሶስት አጽዋማት ብቻ አሉ ፡፡ ከእነርሱ መሀከል አንዱ ጾመ ሐዋርያት ነው ፡፡ ቅበላው በዕለተ እሑድ ይሆንና ጾሙ ሰኞ ይውላል ፡፡ የ2015 ዓ.ም ጾመ ሐዋርያት ግንቦት 28 ይገባል ፡፡

ይህ ጾም እራሱ ጌታቸን ኢየሱስ ክርቶስ ትንቢት የተናገረለት ጾም ነው፡፡
ይኽ ታላቅ ጾም የዛሬ 1902 ዓመት በፊት በራሳቸው በቅዱሳን ሐዋርያት የተጀመረ ጾም ነው ፡፡ ከሰባቱ አጽዋማት መሀከልም አንዱ ነው ፡፡
ፈሪሳውያ ጌታችንን ደቀ መዛሙርትህ አይጾሙም ብለው በጠየቁት ጊዜ እርሱም ‹‹ ሚዜዎች ሙሽራ ከእነርሱ ጋር ሳለ ሊያዝኑ ይችላሉን ? ነገር ግን መሽራው ከእነርሱ የሚወሰድበት ወራት ይመጣል ፤ በዚያ ጊዜም ይጾማሉ ፡፡ በአረጀ ልብስ አዲስ እራፊ የሚያኖር የለም ፤ መጣፊያው ልብሱን ይቦጭቀዋልና ፤ መቀደዱም የባሰ ይሆናል ፡፡ በአረጀ አቁማዳ አዲስ የወይን ጠጅ የሚያኖር የለም ፤ ቢደረግ ግን አቁማዳው ይፈነዳል የወይን ጠጁም ይፈሳል ፡፡አቁማዳው ይጠፋል ፡፡ ነገር ግን አዲሱን የወይን ጠጅ በአዲስ አቁማዳ ያኖረዋል ሁለቱም ይጠባበቃሉ ፡፡›› ማቴ 9 ፥ 14-17 አላቸው ፡፡ይኽ ቃለ እራሱ ጌታችን መድኀኔዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ ራሱ ስለ ጾመ ሐዋርያት የተናገረው ትንቢት ነው ፡፡

‹‹#መሽራው_ከተወሰደ በኃላ›› ማለት ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ሰማይ ካረገ በኃላ ማለት ሲኾን ይኽን ጾም ከዕረገት በኋላ የምንዠምረው ፤ ይኽን ምሳሌ በማድረግ ነው ፡፡ ዐሥር ቀን ዘግይቶ መዠመሩም የሐዋርያት ሰውነት ለጾሙ መዘጋጀት ነበረበትና ነው ፡፡

ይኽ ጾም በአላዋቂዎችን እና በቤተክርስቲያን ጠላቶች የሽማሌዎች ጾም እየተባለ ምዕመናን እንዳይጾሙት ብዙ ተለፍቷል ልናውቅ የሚገባው ነገር ግን ሐዋርያት ዓለምን ዞረው ከማስተማራቸው በፊት ይህን ጾም ጾመዋል ፡፡ በዚህም ጌታችን የተናረው ተንቢት ተፈጽሟል፡፡ ከሰባቱ አጽዋማትን አንዱ ነው ፡፡ በዚህ ምክንያት ይህን ጾም ታላቅ እና ልዩ ያስብለዋል ፡፡ ይኽንን አውቀን ሁላችንም በሕግ በሥርዓት ልንጾመው ይገባል ፡፡
1.1K views04:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-05 07:45:24
1.1K views04:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-30 07:56:11 “እራሷን ባሪያ ብላ በትህትና ዝቅ ስላደረገች እንጂ ባሪያ ውስጥ ያደረ እንዳይመስልህ በእጅ ባልተሰራች እና በተቀደሰችው ድንኳን አደረ ይህችም ድንኳን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ናት።”

ቅዱስ ዲዮናስዮስ ዘአርዮስፋጎስ
2.0K views04:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-28 09:43:37
"ሰንበት ከሁሉ ዕለት ትበልጣለች ሰውም ከሁሉ ፍጥረት ይበልጣል ኖኀ በታቦት (በመርከቡ) ውስጥ ከፍ ከፍ አደረጋት አብርሃምም በመሠዊያው አከበራት ሙሴ ደግሞ ሕዝበ እስራኤል ሰንበትን በአንድነት ሆነው በእውነት እንዲያከብሩዋት አዘዛቸው፡፡"
       ሊቁ ቅዱስ ያሬድ
መልካም ዕለት ሰንበት!!!
2.2K views06:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-27 18:02:40 ብሒላተ አበው ወእመት ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ pinned «የነገረ ቤተ ክርስቲያን የጥናት ጉባኤ ነገ ግንቦት ፲፱ /፳፻፲፭ ዓ.ም (May 27/2023) ከምሽቱ 2፡00-4፡00 (19፡00-21፡00 CET) ሰዓት የ ነገረ ቤተ ክርስቲያን ጉባኤ በ ዙም (zoom) ይካሄዳል። ተሳታፊዎች ከየትኛው የዓለም ክፍል የጉባኤው አካል እንዲሆኑ ተጋብዘዋል። ለመሳትፈ ይህንን ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ ፡- https://us06web.zoom.us/j/88662226009? p…»
15:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-27 18:02:19 የቤተክርስቲያን ታላላቅ ችግሮች የሚመጡት ከየት ይመስልሃል?

ባስልዮስ ሆይ! እስኪ ንገረኝ! በቤተ ክርስቲያን እንዲህ ያሉ ታላላቅ ችግሮች ከየት የሚመጡ ይመስልሃል? እኔ እንደሚመስለኝ የእነዚህ ብቸኛ ምንጫቸው ጳጳሳትና ካህናት የሚመረጡበት መንገድ ጥንቃቄ የጎደለውና እንዲሁ በዘፈቀደ በመኾኑ ነው፡፡

ከእርሱ በታች ካሉ ከሌሎች የሰውነት ክፍሎች የሚመነጨውን ክፉና ደካማ አሳብ ለመግዛትና ለመቈጣጠር ይችል ዘንድ ራስ ከኹሉም በላይ ጠንካራና ጽኑዕ ሊኾን ይገባዋልና፡፡ ራስ ደካማ ከኾነና እነዚህን ለመቈጣጠር ካልቻለ ግን ራስም ደካማ ከኾኑት አካላት የባሰ ደካማ ይኾናል፡፡ ሌላውን የሰውነት ክፍልም ያጠፋል፡፡"

(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
በእንተ ክህነት መጽሐፍ
ገብረ እግዚአብሔር ኪደ የተተረጎመው)
1.7K views15:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ