Get Mystery Box with random crypto!

ብሒላተ አበው ወእመት ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ

የቴሌግራም ቻናል አርማ behlateabew — ብሒላተ አበው ወእመት ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ
የቴሌግራም ቻናል አርማ behlateabew — ብሒላተ አበው ወእመት ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ
የሰርጥ አድራሻ: @behlateabew
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 13.08K
የሰርጥ መግለጫ

የቀድሞ አበው እና እመት የተናገሯቸው መንፈሳዊ ጥበብ
"የእግዚአብሔር ልጅ ሰው የሆነው እኛ አማልክት ዘበጸጋ እንሆን ዘንድ ነው።"
ቅዱስ አትናቴዎስ
👇👇👇👇👇👇👇👇
👉 @behlateabew 👈
👉 @behlateabew 👈
👆👆👆👆👆👆👆👆
https://t.me/joinchat/AAAAAESAiVPCib48ZxL1Pw

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2023-05-27 13:26:23 የነገረ ቤተ ክርስቲያን የጥናት ጉባኤ
ነገ ግንቦት ፲፱ /፳፻፲፭ ዓ.ም (May 27/2023)
ከምሽቱ 2፡00-4፡00 (19፡00-21፡00 CET) ሰዓት የ ነገረ ቤተ ክርስቲያን ጉባኤ በ ዙም (zoom) ይካሄዳል። ተሳታፊዎች ከየትኛው የዓለም ክፍል የጉባኤው አካል እንዲሆኑ ተጋብዘዋል። ለመሳትፈ ይህንን ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ ፡-
https://us06web.zoom.us/j/88662226009?
pwd=T2VvZDFhVTVSN0FqV3dOK0ovWkJaUT09
በጉባኤው እነዚህ ጥናቶች ይርባሉ፡-
1. ከመካከለኛው ዘመን ጀምሮ ያጋጠሙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ውጪያዊ ፈተናዎች ዳሰሳ
በ ቀሲስ ፕሮፌሰር ሰሙ ምትኩ
2. ጥቃት፣ ምእመናንና የጋራ ኦርቶዶክሳዊ ማንነት
በዶ/ር እንግዳ ግርማ
3.0K views10:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-25 08:05:05
“አምላክ በእልልታ፥ እግዚአብሔር በመለከት ድምፅ ዐረገ።”
  — መዝሙር 47፥5

እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ዕርገት በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን!!

መልካም በዓል
1.9K views05:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-21 10:54:42 ክህነት ምን ያህል የከበረ እንደሆነም በቅዳሴው ‹‹ከባሕርይ አባቱ ከአብ ጋር በልዕልና የሚቀመጥ እርሱ በዚያች ሰዓት በሁሉም ካህናት እጅ ይያዛል፤ ሊቀበሉትና ሊዋሐዱት ለሚፈልጉትም ለሁሉም ራሱን ይሰጣል። ወዮ የእግዚአብሔር ቸርነት ምን ይደንቅ? ምን ይረቅ? መጠንና ልክ የሌለውን እሳት በእጁ የሚይዝ ካህን!›› በማለት የክህነትን ታላቅነት አሳይቷል፡፡

ለወንድሙ ቅዱስ ባስልዮስ በላከው መልእክቱ ደግሞ ‹‹ክርስቶስ እንደሚፈልገው አድርጌ ይህን ኃላፊነት ለመወጣት የበቃሁ ሆኜ ሳለሁ እምቢ ብዬ ሸሽቼ ቢሆን ኖሮ አነጋገሬ ሰዎችን ሊያጠራጥራቸው በቻለም ነበር።

ነገር ግን የመንፈሴ ደካማነት ለዚህ አገልግሎት የማልጠቅም ስለሚያደርገኝ ንግግሬ ለምን በጥያቄ ውስጥ ይወድቃል? መንጋው በደኅናና በጥሩ ምግብና ላይ ሳለ የጥበቃውን ኃላፊነት ብወስድና ከዚያ በኋላ ግን በእኔ አላዋቂነትና ጥበብ የለሽነት ምክንያት ባጠፋቸው እነርሱን ለማዳንና ለመቤዠት ሲል ራሱን የሰጠላቸውን እግዚአብሔርን በራሴ ላይ አነሳሳዋለሁ ብዬ እፈራለሁና›› ሲል ተናግሯል፡፡

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ከክህነት ሸሽቶ መኖር ቢፈልግም ወደ ክህነት መምጣቱ አልቀረም። በአንዲት ሌሊትም ሲጸልይ የእግዚአብሔር መልአክ እንደ በረድ ነጭ በሆነ ልብስ ተገለጠለት፤ ቅዱስ ዮሐንስም ሲያየው ደንግጦ በምድር ላይ ወደቀ፤ መልአኩም አርአያውን ለውጦ እንደ ሰው ሆኖ ታየው፤ ‹‹ወዳጄ አዲስ ዳንኤል ሆይ፤ አትፍራ፤ ተነሣ›› አለው። መልአኩ አዲስ ዳንኤል ብሎ የተጠራበት ምክንያት የናቡከደነፆር ራእይ ንባቡ ከነትርጓሜው ከጠፋ በኋላ ንባቡ ከነትርጓሜው በመንፈስ ቅዱስ ተገልጾለት እንደተናገረ እርሱም ራእየ ዮሐንስን ንባቡ ከነትርጓሜው ከጠፋ በኋላ በመንፈስ ቅዱስ ተገልጾለት ተርጉሞታልና። ዳግመኛም ዳንኤል ጸዋሚ ተሐራሚ እንደሆነ ሁሉ እርሱም ጸዋሚ ተሐራሚ በመሆኑ ዳንኤል ሐዲስ ብሎታል።

የቅዱስ ዮሐንስም ልቡናው ተጽናንቶ ‹‹ጌታዬ አንተ ማን ነህ? ግርማህ አስፈርቶኛልና›› አለው የእግዚአብሔር መልአክም ‹‹ትሠራው ዘንድ የሚገባህን ልነግርህ ወደ አንተ የተላኩ ነኝ›› አለው። ‹‹አሁንም እግዚአብሔር አምላክ ያዘዘህን ለመሥራት ልብህን አበርታ፤ ቃልህ ከጽንፍ እስከ ጽንፍ በአራቱ ማእዘን ይደርሳልና። እልፍ አእላፍትም ትምህርትህን ተቀብለው ትእዛዝህን ሰምተው ወደ ፈጣሪያቸው እግዚአብሔር ተመልሰው ይድናሉና።

በእግዚአብሔር መንግሥት ውስጥ የጸና የብርሃን ዓምድ ትሆናለህ። እነሆ የአንጾኪያ ሊቀ ጳጳስ ወደ አንተ ይመጣል፤ የሚያዝዝህንም አድርግ፤ የእግዚአብሔር ትእዛዝ ነውና ልትተላለፍ አይገባህም›› አለው፡፡ ከዚያም በኋላ ያ መልአክ ለአባ ፊላትያኖስ ተገልጦ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅን ቅስና እንዲሾመው አዘዘው። በማግሥቱም ሊቀ ጳጳሳቱ መጣ ከእርሱ ጋራም ካህናት አሉ ቅዱስ ዮሐንስንም ይዞ ቅስና ሾመው።

የቊስጥንጥንያ ሊቀ ጳጳስ ባረፈ ጊዜ ንጉሥ አርቃዲዮስ ልኮ አስመጥቶ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅን በቊስጥንጥንያ ላይ ሊቀ ጵጵስና እንዲሾም አደረገው። ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅም እንደ አባቶቹ በጵጵስናው ሥራ ጸና፤ ሕይወትነት ባላቸው ትምህርቶችና ተግሣጾች ሕዝቡን ሁልጊዜ የሚያስተምር ሆነ። ማንንም ሳይፈራ ሕግ ተላላፊዎችን ከቤተ መንግሥትም ከቤተ ክህነት ወገንም ይገሥፃቸው ጀመር። በዚህም ፊት አይቶ የማያዳላ መምህና መገሥፅ በመባል የሚታወቅ ሆነ። አንድ ቀን የንጉሥ አርቃዲዮስ ሚስት አውዶክስያ የአንዲት ድኃ መበለት ቦታዋን በግፍ ወሰደች፤ ያች መበለትም ወደ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ መጥታ ንግሥቲቱ ቦታዋን እንደ ነጠቀቻት ነገረችው።

እርሱም ‹‹የድኃዋን ቦታ መልሽላት›› ብሎ ከብዙ ምክር ጋር እንድትመልስላት ንግሥቲቱን ለመናት፤ እርሷ ግን እንቢ አለች። ቅዱስ ዮሐንስም ስለ አንዲት መበለት ንግሥቲቱን ሳያፍርና ሳይፈራ ወደ ቤተ ክርስቲያን ገብታ ሥጋውን ደሙን እንዳትቀበል አውግዞ ለያት። ንግሥቲቱም እርሱ ከሹመት የሚሻርበትን ነገር መሥራት ጀመረች፤ ስለ ክፉ ሥራቸው ከሹመታቸው እርሱ የሻራቸውን
ኤጲስቆጶሳት ሰበሰበች፤ እነርሱም ንግሥቲቱን ስለተቃወመ ስደት እንደሚገባው ተስማምተው ጻፉ፤ እርሷም አጥራክያ ወደ ሚባል ደሴት ሰደደችው።

የሮሜ ንጉሥ አኖሬዎስና ሊቀ ጳጳሳቱ ዮናክኒዶስ ስለ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ስደት በሰሙ ጊዜ እጅግ አዘኑ፤ በንጉሥ አርቃድዮስ ላይም እንዲህ የሚል ደብዳቤ ጽፈው ላኩ፤ ‹‹ከዚህ ከክፉ ሥራ ተጠበቅ፤ ትእዛዛችንንም ተቀብለህ የከበረ ዮሐንስን ከስደቱ ካልመለስከው በአንተና በእኛ መካከል ሰላም አይኖርም።›› መልእክታቸውንም ባነበበ ጊዜ እጅግ አዘነ፤ ሚስቱንም አግዶ ልኮ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅን ከስደቱ መለሰው። ከጥቂት ቀኖችም በኋላ ንግሥቲቱ ወደ ክፋቷ ተመልሳ ሁለተኛ ወደ አጥራክያ ደሴት ሰደደችውና በዚያው ዐረፈ።
በዚህ ዕለት ዓመታዊ በዓላቸው የሚከበሩ ቅዱሳን
አቡነ ተክለ ሃይማኖት
ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን፤ እኛንም በዚህ አባት ጸሎት ይማረን፤ በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘለዓለሙ አሜን።
630 views07:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-21 10:54:40
617 views07:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-14 16:28:54 "ኹለቱም አንድ አካል ይኾናሉ፤ ይኽ ነገር ጥልቅ፤ ረቂቅ ምሥጢር ነው፤ እኔም ለክርስቶስና ለቤተክርስቲያን ምሳሌ አድርጌ እናገረዋለኹ፡፡"

       ሃይማኖተ አበው  ዘስምዓት
614 views13:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-14 08:46:44
" ጋብቻ ንጹሕ ነው የወንድና የሴት አንድ መሆንንም እግዚአብሔር አክብሮታል "
             መጽሐፈ ዲድስቅልያ
861 views05:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-12 20:51:44 "ወደ መሬት ወድቀን በሰገድን ጊዜ ኃጢአት እንዴት ወደ ታች ጎትታ እንደጣለችን እናስታውሳለን። ዳግመኛም ከወደቅንበት በተነሣን ጊዜ የእግዚአብሔር ጸጋ እና ምሕረት እንዴት ከመሬት እንዳነሣንና የሰማዩን ርስት እንደሰጠን እንመሰክራለን"
ቅዱስ ባስልዮስ
383 views17:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-09 08:10:48 “ኦ ድንግል አኮ በፍትወተ ደነስ ዘተፀነስኪ አላ በሩካቤ ዘበሕግ እምሐና ወኢያቄም ተወለድኪ”

"ድንግል ሆይ በኃጢአት ፍትወት የተፀነስሽ አይደለም ፤ በሕግ በሆነ ሩካቤ ከሐና ከኢያቄም ተወለድሽ እንጂ።"

#አባ ሕርያቆስ በቅዳሴው
1.4K views05:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-09 06:01:43
“ይህ በዓል በሐዲስና በብሉይ ኪዳን መካከል መገኛ ሆነ፡፡ ምስሌዎቹ በእዉነታ፣ አሮጌው በአዲስ ቃል ኪዳን ተተኩ፡፡ ፍጥረት ሁሉ በደስታ ይዘምራል የዚህን ቀንም ደስታ ይካፈላል፡፡ ይህ መቅደሱን የሰራበት ዕለት ነው፡፡ ይህ ዕለት ትልቅ ሕንፃ የታነጸበትና ፍጡር የፈጣሪ ማደሪያ ለመሆን የተዘጋጀበት ዕለት ነው፡፡”
የቀርጤሱ ቅዱስ እንድርያስ

እንኳን ለባሕርያችን መመኪያ ለንጽሕናችን መሠረት አምላካችን አማኑኤልን ለወለደች ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም የልደት በዓል በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ፡፡
1.5K views03:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-07 19:29:16
“ የኔታ ዘብሔረ ጽጌ “ ህጻናት ላይ ብቻ ያተኮረ መንፈሳዊ መርሃ ግብር ሲሆን ተዘጋጅቶ ሚቀርበው
በብሔረ ጽጌ ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተክርስቲያን ፍኖተ ብርሃን ሰንበት ት/ቤት በቤተልሔም ሕጻንት ጽ/ቤት
ዘውትር እሁድ ጠዋት ጠዋት በEOTC TV ይጠብቁን
https://t.me/yeneta_forkids ቴሌግራም
https://www.facebook.com/profile.php?id=100091243222413 ፌስቡክ
https://www.youtube.com/channel/UC396qj8dpP6_CQJCJPDOk5A ዩቲዩብ http://tiktok.com/@fenoteberhanzbeheretsige ቲክቶክ
1.4K views16:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ