Get Mystery Box with random crypto!

ብሒላተ አበው ወእመት ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ

የቴሌግራም ቻናል አርማ behlateabew — ብሒላተ አበው ወእመት ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ
የቴሌግራም ቻናል አርማ behlateabew — ብሒላተ አበው ወእመት ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ
የሰርጥ አድራሻ: @behlateabew
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 13.08K
የሰርጥ መግለጫ

የቀድሞ አበው እና እመት የተናገሯቸው መንፈሳዊ ጥበብ
"የእግዚአብሔር ልጅ ሰው የሆነው እኛ አማልክት ዘበጸጋ እንሆን ዘንድ ነው።"
ቅዱስ አትናቴዎስ
👇👇👇👇👇👇👇👇
👉 @behlateabew 👈
👉 @behlateabew 👈
👆👆👆👆👆👆👆👆
https://t.me/joinchat/AAAAAESAiVPCib48ZxL1Pw

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 9

2023-04-04 15:34:52 " #ጥቂት_ቆዩ_እንጂ... ? "
_______
በአንድ ወቅት አባ ጳኩሚስ አንዲት ሴት ብዙ አጋንንት ሰፍረውባት ደዌ ጸንቶባት አየ።

"ጌታዬ የሰው ባህሪ ደካማ ነው እባክህን የዚህችን ደካማ ሴት ደዌ እኔ ልሸከመው በእኔ ላይ አድርገው" አለ ። በዚህ ጊዜ አንድ ቀፎ ንብ ተገልብጦ በሌላ ቀፎ እንደሚሰፍር በዚህች ሴትዮ አድረው ደዌ አጽንተውባት የነበሩት አጋንንት በአባ ጳኩሚስ ላይ ሰፈሩ።

እሱም ማቅ ለብሶ አመድ ነስንሶ በፆም በፀሎት አሰቃያቸው። አጋንንት እንዲህ በፆም በፀሎት የተጋ ሰውነት አይድማማቸውም እና እንሂድ እንውጣ እያሉ ጮሁ ።

አባታችንም እንግዳ እኮ ከገባበት ቤት ጥቂት ያርፋል ቆዩ እንጂ አላቸው። እኛ ከገነት ካስወጣነው ከአዳም በስተቀር እንዲህ ያለ ሰው አላየንም ብለው ከእርሱ ወጥተው ሄዱ።

-ቅዱሳን ለእኛ ያላቸውን ፍቅር ተመልክታችሁን ?

" ይህ ዓይነት ጋኔን ከጸሎትና ከጦም በቀር አይወጣም አላቸው።" ማቴ 17÷21

የቅዱሱ በረከት በሁላችንም ላይ ይደርብን
446 views12:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-04 07:39:43
††† እንኳን ለጥንተ በዓለ ምሴተ ሐሙስ በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †††

††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††

††† ምሴተ ሐሙስ †††

††† ስም አጠራሩ ከፍ ከፍ ይበልና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ "ምሴተ ሐሙስ - ጥንተ በዓል ቀን ነው" በምትባለው በዚህች ዕለት:-
1.በወዳጁ በአልዓዛር ቤት የዓለማት ፈጣሪ ሲሆን በትሕትና ዝቅ ብሎ የደቀ መዛሙርቱን እግር አጥቧል::
2.ለእኛ ድኅነት ይሆነን ዘንድ ቅዱስ ሥጋውን : ክቡር ደሙን ለመጀመሪያ ጊዜ ሰጥቷል::
3.በጌቴሴማኒ ላበቱ እንደ ደም እየተንጠፈጠፈ ጸልዮ "ወደ ፈተና እንዳትገቡ ጸልዩ" ሲል አስተምሯል::
4.ምሽት 3 ሰዓት አካባቢ ይሁዳ ሊቃነ ካህናቱን አስከትሎ መጥቶ ለ30 ብር አሳልፎ ሰጥቶታል:: (ማቴ. 26:26 / ዮሐ. 13:1)

ይህ ሁሉ ለእኛ ድኅነት ተፈጽሟልና ምስጋናና ክብር ለፈጣሪያችን ኢየሱስ ክርስቶስ ይሁን::

††† "ሥጋዬን የሚበላ ደሜንም የሚጠጣ የዘለዓለም ሕይወት አለው:: እኔም በመጨረሻው ቀን አስነሳዋለሁ:: ሥጋዬ እውነተኛ መብል: ደሜም እውነተኛ መጠጥ ነውና:: ሥጋዬን የሚበላ ደሜንም የሚጠጣ በእኔ ይኖራል:: እኔም በርሱ እኖራለሁ::"  †††
(ዮሐ. 6:53-56)

††† "እግራቸውን አጥቦ: ልብሱንም አንስቶ ዳግመኛ ተቀመጠ:: እንዲህም አላቸው:- 'ያደረግሁላችሁን ታስተውሳላችሁን? እናንተ መምህርና ጌታ ትሉኛላችሁ:: እንዲሁ ነኝና መልካም ትላላችሁ:: እንግዲህ እኔ ጌታና መምህር ስሆን እግራችሁን ካጠብሁ እናንተ ደግሞ እርስ በርሳችሁ እግራችሁን ትተጣጠቡ ዘንድ ይገባል::' " †††
ዮሐ. 13:12-14
176 views04:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-02 07:15:24 ኒቆዲሞስ

ሰው ሥልጣን ቢኖረው ዕውቀት ሊጎድለው እንዲሁም ሀብት ላይኖረው ይችላል፡፡ ዕውቀት ቢኖረው ደግሞ ሀብትና ሥልጣን ማካበት ያዳግተዋል፡፡ ሀብት ቢኖረውም እንኳን ዕውቀት ይጎድለዋል፤ ሥልጣንም አይኖረውም፡፡ ኒቆዲሞስ ግን ሦስቱንም አንድ ላይ አስተባብሮ የያዘ የአይሁድ አለቃ ነበር፡፡

ከፈሪሳዊያን ወገን የሆነው ኒቆዲሞስ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመዋዕለ ስብከቱ ያስተማረውን ወንጌልን ለመማር ከአይሁድ ሁሉ ቀድሞ በሌሊት ወደ ጌታችን ይሄድ ነበር፡፡ ፈሪሳውያን ማመን በተሳናቸው በዚያን ጊዜ ጆሮውን ለቃለ እግዚአብሔር፣ ልቡን ለእምነት የከፈተ ሰው ነው፡፡

እናውቃለን በማለት የሚመካኙ በርካታ ሰዎች ከመልካም ነገር ሲከለከሉ እርሱ ግን “ዐዋቂ ሳለ ራሱን ዝቅ አድርጎ፣ እምነት በማጣት የነጠፈችውን የፈሪሳውያንን ኅብረት ጥሎ፣ ሐዋርያትን መስሎ ጌታውን አግኝቶታል፡፡” ቀርቦም እንዲህ አለው፤ ‹‹መምህር ሆይ፥ ልታስተምር ከእግዚአብሔር ዘንድ እንደ መጣህ እናውቃለን፤ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ከሆነ በቀር አንተ የምታደርገውን ይህን ተአምር ሊያደርግ የሚችል የለምና፡፡›› ጌታችን ኢየሱስም መልሶ ‹‹እውነት እውነት እልሀለሁ፤ ዳግመኛ ያልተወለደ ሰው የእግዚአብሔርን መንግሥት ለማየት አይችልም›› አለው፡፡

ነገር ግን ኒቆዲሞስ ምሥጢሩ ስላልተገለጠለት ‹‹ሰው ከሸመገለ በኋላ ዳግመኛ መወለድ እንደምን ይቻላል? ዳግመኛ ይወለድ ዘንድ ወደ እናቱ ማኅፀን ተመልሶ መግባት ይችላልን?›› በማለት ጌታን መልሶ ጠየቀው፡፡ ጌታችንም እንዲህ ብሎ መለሰለት፤ ‹‹እውነት እውነት እልሀለሁ፤ ዳግመኛ ከውኃና ከመንፈስ ቅዱስ ያልተወለደ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ሊገባ አይችልም፡፡ ከሥጋ የተወለደ ሥጋ ነው፡፡ ከመንፈስ የተወለደ መንፈስ ነውና፡፡››

አሁንም ግን ኒቆዲሞስ ምሥጢሩ አልተገለጠለትም ነበርና ‹‹ይህ ሊሆን እንዴት ይቻላል?›› በማለትም ጌታን ጠየቀው፡፡ ጌታችንም ‹‹አንተ የእስራኤል መምህራቸው ነህ፤ ነገር ግን እንዴት ይህን አታውቅም? በምድር ያለውን ስንነግራችሁ ካላመናችሁኝ በሰማይ ያለውን ብንነግራችሁ እንደምን ታምናላችሁ? ከሰማይ ከወረደው የሰው ልጅ በቀር ወደ ሰማይ የወጣ የለም፤ እርሱም በሰማይ የሚኖረው ነው፡፡ ሙሴ በምድረ በዳ እባቡን እንደ ሰቀለ የሰው ልጅ እንዲሁ ይሰቀል ዘንድ አለው፡፡ ያመነበት ሁሉ ለዘለዓለም ሕያው ሆኖ እንዲኖር እንጂ እንዲጠፋ አይደለም…›› በማለት አስረድቶታል፡፡ (ዮሐ.፫፥፪-፲፭)

የዓለም መድኃኒት ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በዕለተ ዓርብ ቅድስት ነፍሱን ከቅዱስ ሥጋው በለየባት በዚያች ሰዓት፣ ሐዋርያት በተበተኑባትና አይሁድ በሠለጠኑባት ጊዜ እንኳን ከጌታችን ሳይል በድፍረት ከእግረ መስቀሉ የተገኘ እንዲሁም ቅዱስ ሥጋውን በድርብ በፍታ ገንዞ የቀበረ ሰው ኒቆዲሞስ ነው፤ ስለዚህም ሰባተኛው የዐቢይ ጾም ሳምንት በእርሱ ስም ተሰይሟል፡፡

ለኒቆዲሞስ ምሥጢሩን ገልጾ ያዳነውና ያከበረው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለእኛም ምሥጢሩን ይገልጽልን ዘንድ ቅዱስ ፈቃዱ ይሁንልን፤ አሜን፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
290 views04:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-26 21:39:03 11 ዓመት ባልሞላ ጊዜ ከነሐሴ 10/2014 ዓ.ም ጀምሮ 2 ፓትርያርኮችና 21 በላይ ጳጳሳት አርፈዋል
ደጋጎች አባቶች እየተጠሩ ነው
ብጹእ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ፓትርያርክ
ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ፓትርያርክ
አቡነ ሚካኤል ዘሽሬ
አቡነ ማትያስ ዘከናዳ
አቡነ መልከ ጼዴቅ ዘጎንደር
አቡነ በርናባስ ዘባህር ዳር
አቡነ ዜና ማርቆስ ዘጎንደር
አቡነ መልከ ጼዴቅ ዘጉራጌ
አቡነ ኤልሳዕ
አቡነ ኤጲፋንዮስ
አቡነ ጢሞቴዎስ
አቡነ አረጋዊ በ106 ዓመታቸው ያረፉ
አቡነ ዳንኤል
አቡነ ቶማስ ዘፍኖተ ሰላም
አአቡነ በርተሎሜዎስ
አቡነ ጴጥሮስ ዘባህርዳር
አቡነ መርሐ ክርስቶስ
አቡነ ይስሀቅ ዘባሌ
አቡነ ናትናኤል ዘአርሲ
አቡነ ገብርኤል
አቡነ ኤፍሬም
አቡነ ባስልዮስ
አቡነ አረጋዊ

ብጹአን ወቅዱሳን አባቶቻችን ሆይ
ቤተ ክርስቲያንን ለማን ነው የተዋችኃት?
ያለችበት ዘመን ፈተና ላይ ናት።
በአስተብቁኦታችሁ በረድኤታችሁ አትርሷት ቅድስት
ጸሎታችሁ ንጹህ ሃይማኖታችሁ ትጠብቀን።

የከበረች በረከታቸው ፤
ድል የማትነሣ ረድኤታቸው ፤
ጥርጥር የሌለባት ሃይማኖታቸው ከሁላችን ጋር ይሁን።
203 views18:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-26 19:34:46 በቅርቡ በተቋቋመው በኦሮሚያ ክልል ሸገር ከተማ አስተዳደር ውስጥ በቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን፤ በአገልጋዮቿ እና በምእመናን ላይ እየተፈጸመ ያለውን ግፍ እና በደል አስመልክቶ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የተሰጠ መግለጫ ።
++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++
ክርስትና ወደ ኢትዮጵያ ከገባበት ጊዜ ጀምሮ  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ከሰሜን እስከ ደቡብ፣ ከምዕራብ እስከ ምስራቅ በተለያየ ዘመን በተነሱ ቅዱሳን ክርስትና እንዲሰበክ በማድረግ ለሺህ ዓመታት የሀገሪቱ የሃይማኖት፣ የታሪክ እና የሞራል ምንጭ ሆና ኖራለች፡፡ ቤተ ክርስቲያን ራሷ የሆነው ክርስቶስን በመስበክ ያላመኑትን ከማሳመን፣ ያመኑትን ከማፅናት እና የፀኑትን ከመቀደስ ውጪ ሌላ ምድራዊ ዓላማ ሳይኖራት ነገስታቱንም ሆነ ምዕመኑን እኩል ንስሀ አባት መድባ አና ንስሀ አቀብላ፣ ቀድሳ አቁርባ እና ከዚህ ዓለም በሞት ሲለዩም ለሁሉም እኩል ፍትሃት አድርጋ የምትሸኝ ሰውን በፆታው፣ በቋንቋው፣ በነገዱ እና በማንነቱ አድሎ ሳታደርግ የኖረች ናት። ሆኖም ግን ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በሀገራችን ውስጥ ያለአንዳች ማስረጃ የተፈጠሩ የሀሰት ትርክቶች እና እነዚህን ትርክቶች መሠረት ተደርገው በሰፊው ሲነዙ የነበሩ ሀሰተኛ መረጃዎች ቤተ ክርስቲያንን ዋጋ እያስከፈላት ይገኛል፡፡

አሁን አሁን የቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች እና ምእመናን በሃይማኖታቸው ብቻ ተለይተው በመንግሥት መዋቅር ውስጥ ባሉ አካላት ካህናት አባቶቻችን የአምላካችንንና የመድኃኒታችንን የኢየሱስ ክርስቶስ ስጋና ደሙን ቀድሰውና አክብረው ለሰዎች ድህነት ይሆኑ ዘንድ በተሰጣቸው ስልጣነ ክህነት ምእመናን ለርስት መንግሥተ ሰማያት የሚያበቁ ሁነው ሳለ በተለያዩ ጊዜ ለሞት እና ለእንግልት እንዲሁም ለስደት እና ለእስራት ሲዳረጉ ማዬት የእለት ተእለት ተግባር ከሆነ ሰንበትበት ብሏል፡፡

በአዲሱ መንግስታዊ መዋቅራዊ አደረጃጀት በአዲስ አበባ ዙርያ በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ሸገር ከተማ በሜጢ ሆርሲሳ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ ካህን የነበሩት ቄስ አባይ መለሰ በመጋቢት ፲ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም ከቅዳሴ ወጥተው ወደ መኖሪያ ቤታቸው ሲሄዱ ለጊዜው ማንነታቸው ባልታወቁ ግለሰቦች በተፈጸመባቸው ድብደባ ሕይወታቸው ሊያልፍ መቻሉን ተረድተናል፡፡
መንግሥት የዜጎችን በሰላም ወጥቶ የመግባት ደኅንነት የማስጠበቅ እና ዋስትና የመስጠት እንዲሁም ጭካኔ እና አረመኔያዊ ከሆኑ ጥቃቶች የመጠበቅ መንግሥታዊ ኃላፊነት ሊኖርበት ይህንን ባለመወጣቱ ምክንያት የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች እና ዜጎች በሕይወት የመኖር መብት በየእለቱ እየተሸረሸረ ይገኛል፡፡ በመሆኑም ሀገረ ስብከታችን በቀሲስ አብይ መለስ ሞት የተሰማንን መሪር ኃዘን እየገለጽን የሚመለከተው የፌዴራል፤ የአዲስ አበባ ከተማ እና የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ እና የፍትህ አካል ጉዳዩን ልዩ ትኩረት በመስጠት ተገቢውን ምርምራ በማድረግ ይህንን አስነዋሪ እና ጭካኔ የተሞላበትን የግድያ ወንጀል የፈጸሙ ወንጀለኞችን ለፍርድ እንዲያቀርብ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡

ከዚህም በተጨማሪ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ስር የሚተዳደሩ ቁጥራቸው ከዐሥራ ሦስት በላይ የሆኑ አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት በአዲሱ የከተማ ድንበር ማካለል ወደ ኦሮሚያ ክልል ሸገር ከተማ ክልል ውስጥ የተካለሉ ቢሆኑም ለዓመታት ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን ገንብተው መንፈሳዊ አገልግሎት ሲሰጡ ከቆዩ አብያተ ክርስቲያናት ውስጥ

፩ የኤርቱ ሞጀ ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ እና የቅዱስ ጊዮርጊስ አብያተ ክርስቲያናትን ለማፍረስ ተሞክሮ ከእነዚህ ውስጥ የቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ሙሉ በመሉ በአፍራሽ ግብረ ሀይል እንዲፈርስ ከመደረጉም በላይ የፈረሰውን ቤተ ክርስቲያን በውስጡ ከሚገኙ ንዋያተ ቅድሳት ጋር በሙሉ እንዲቃጠሉ እና እንዲወድሙ ተደርጓል፡፡

፪. በኤርቱ ሞጆ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያንን አጥሩን ማፍረስ ተጀምሮ ምእመናን እና የቤተ ክርስቲያኒቱ አባቶች ባደረጉት ርብርብ የማፍረስ : ሒደቱ ለጊዜው ቢቆምም አሁንም ይህን ቤተ ክርስቲያንም ሆነ በሸገር ከተማ ውስጥ ያሉ አብያተ ክርስቲያናት በከፍተኛ ስጋት ውስጥ እንደሚገኙ ለመረዳት ተችሏል፡፡

ስለሆነም ለሀገር ባለውለታ የሆነችን ቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን በማሳደድ እና በማውደም ታሪካዊ መሠረቷን ለመናድ እና ከሌሎች ቤተ እምነቶች በመነጠል በቤተ ክርስቲያናችን ላይ እየተፈጸመ ያለው አድሏዊ እና ኢ-ሕገ መንግስታዊ የሆነው ድርጊት በአስቸኳይ እንዲቆም እንዲደረግ እያሳሰብን የፌዴራል እና የክልሉ መንግሥትም የድርጊቱን ፈጻሚ አካላት ላይ ተገቢውን እርምት እንዲወስድ ስንል እንጠይቃለን፤

በመጨረሻም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እና የሚመለከተው ባለስልጣን አካል በየካቲት ፳፫ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም በገነተ ጽጌ ቅዱስ
ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ላይ የተፈጸመውን እና ሕገ ወጥ ተግባርን በተመለከተ የድርጊቱን ፈጻሚ አካላትን በ፭ ቀናት ጊዜ ውስጥ ተለይተው በሕግ ተጠያቂ በማድረግ ለሕዝብ እንዲያሳጡት ጥሪ ያስተላለፈች ቢሆንም ይህ መግለጫ  አስከሚሰጥ ድረስ ለድርጊቱ ተጠያቂ የሆኑ አካላት ተለይተው ተጠያቂ አለመሆናቸው ቤተ ክርስቲያናችንን በእጅጉ ያሳዘነ ተግባር ነው፡፡ በመሆኑም መንግሥት ቤተ ክርስቲያን ያቀረበችውን ጥያቄ ምላሽ ሊሰጥ ያልቻለ በመሆኑ የድርጊቱን መነሻ ምክንያት የደረሰውን ጉዳት እና የድርጊቱን ፈጻሚዎች ለይቶ ለሕዝብ ይፋ የሚያደርግ የሕግ ባለሙያዎች ኮሚቴ በማዋቀር ወደሥራ የተገባ መሆኑን እያሳወቅን ኮሚቴው የደረሰበትን ጥቅል መረጃ በአጭር ቀናት ጊዜ ውስጥ ለሕዝብ ሪፖርቱን የሚያቀርብ እና የድርጊቱ ፈጻሚዎች ቤተ ክርስቲያንን በይፋ ይቅርታ እንዲጠይቁ እና አጥፊዎችም ለድርጊታቸው ተገቢውን ሕጋዊ ቅጣት እንዲያገኙ እየሠራን መሆኑን እናሳውቃለን።

በመሆኑም፡

፩. መንግሥት የቤተ ክርስቲያን አገልጋይ በመሆናቸው ምክንያት በአሰቃቂ ሁኔታ በመንገድ ላይ ተደብድበው ሕይወታቸው እንዲያልፍ የተደረጉት የቄስ ዐብይ መለሰ ገዳዮችን ተከታትሎ ለፍርድ እንዲያቀርብ እና ችግሩን ከሥር ከመሠረቱ በመፍታት የአገልጋዮችንና የምእመናን መብት እንዲያስከብር

፪. በሸገር ከተማ አስተዳደር እየተፈፀመ ያለው አብያተ ክርስቲያናትን የማፍረስ ድርጊት በአስቸኴይ እንዲቆም እንዲደረግ፣

፫. የፈረሱትን አብያተ ክርስቲያናት ቦታ ተመላሽ እንዲያደርግ እና የፈረሰውን ቤተ ክርስቲያንም በራሱ ወጪ እንዲያሠራ እንዲደረግ እንጠይቃለን።

የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ምእመናን እና ምእመናት እንዲሁም የቤተ ክርስቲያን አገልጋይ አባቶች ዘመነ ቤተ ክርስቲያንን በጉልበታችን፤ በዕውቀታችን እና በገንዘባችን የምናገለግልበት ብቻ ሳይሆን በአካላችን፣ በጤናችን እና በሕይወታችንም መስዋዕትነትን የምንከፍልበት የሰማዕትነት ዘመን ነው፡፡ ይህ የሰማዕትነት መከራም በሀገራችንና በየቤታችን እየመጣ ያለ የመከራ ዘመን በመሆኑ አብዝቶ ወደ እግዚአብሔር በመጸለይ፤ ሥጋችንን በጾም እና በስግደት በመግራት ከአባቶቻችሁ አባታዊ መመሪያ በመቀበል በሃይማኖታችሁ ጸንታችሁ እንድትቆሙ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡

እግዚአብሔር ሀገራችንን እና ሕዝቦቿን ይባርክ ።
መጋቢት ፲፯ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም
373 views16:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-23 22:32:23 _ወሊድን በተመለከተ__
ልጅን መውለድ ብዙ ተባዙ ያለውን አምላካዊ ቃል መፈጸም ስለሆነ ትልቅ ክብር ነው። ወላድ እናቶቻችንም ክቡራት ናቸው። ባለማወቅ (ላለዝበው ብየ ነው እንጂ በድንቁርና ልል ነበር) የወለደች ሴት እስላም ናት፣ ርኵስ ናት የሚሉ ሰዎች ከእውቀት ጋር የተጣሉ ሰዎች ናቸው። ወንድ ከወለደች በኋላ ለ40 ቀን ቤተክርስቲያን አትገባም። የማትገባበት ምክንያት ግን እስከዚያ ድረስ ደም ስለሚፈሳት ነው። ደም የሚፈሰው ሰው ደግሞ ቤተክርስቲያን አይገባም። ይህ ለወላድ ሴት ብቻ የተወሰነ ሳይሆን ወንዱም ቢሆን እንቅፋት መትቶት አካሉ ቢደማ ቤተክርስቲያን አይገባም። አፍንጫው ቢነስር ብቻ ከመድማት ወገን በአንዱ ቢደማ ቤተክርስቲያን አይገባም። ርስሐት (ዝንየት) ካገኘውም 24 ሰዓት ጠብቆ ይገባል እንጂ ከዚያ በፊት እንዲገባ ሥርዐት አልተሠራም። ሴት ልጅ የወለደች እናትም እስከ 80 ቀን ቤተክርስቲያን አትገባም። ይኽውም ደም ስለሚፈሳት ነው። በወር አበባ ያለች ሴትም ቤተክርስቲያን አትገባም ይኽም ደም ስለሚፈሳት ነው። ቤተክርስቲያን መፍሰስ ያለበት የክርስቶስ ደም ብቻ ነው። የፍጡር ደም መፍሰስ የለበትም። ይህ ሥርዐት የተሠራውም ለቤተክርስቲያን ክብር ተብሎ እንጂ የወር አበባ፣ በወሊድ ጊዜ የሚፈሰው ደም ርኵሰት ሆኖ አይደለም። ክቡራት ወላድ እናቶቻችንን እንደ ርኵስ ማሰብ የርኵስ ሰዎች እሳቤ ነው። እናቶችን ልጅ ስለወለዱ እናከብራቸዋለን እንጂ ርኵስ ናቸው አንልም። የወለዱ እናቶችን በወለዱ ቀን በሌላ ቀንም ሄዶ "እንኳን ማርያም ማረችሽ" ማለት የክርስቲያን ሥራ ነው። ከቤተክርስቲያን መግባት፣ ሥጋውን ደሙን ከመቀበል አይከለክልም።


ፍትሐ ነገሥት አንቀጸ ቀሳውስት ላይ ቁጥር ፪፻፴፯ (237) ላይ፣ በደስ ፰ (8)፣ አቡሊዲስ በጻፈው መጽሐፍ በስምንተኛው አንቀጽ ቄስ ሚስቱ ብትወልድ ከአገልግሎት አይከልከል ይላል። ቀሲስ ሶበ ወለደት ብእሲቱ ኢይትከላእ እንዲል። አንዳንድ ቦታ ላይ ገጠር የወለደችን ሴት በአሥረኛው ቀን ጸበል የሚረጩ ቄሶች አሉ። ጸበል በረከት ያለው ስለሆነ መረጨቷ ጉዳት የለውም። ነገር ግን ርኵሰቷን ስለሚያስለቅቅ ተብሎ ከሆነ የሚረጨው ነውር ነው። መጀመሪያም ልጅ በመውለዷ ርኵስት አልሆነችምና። ይሄ ከትምህርቷ ገፋ ያለማድረግ ችግር ነው። ጸበል ተረጨችም አልተረጨችም ምንም ዓይነት ነውር የለባትም። ያ ብቻ ሳይሆን በማየ ገቦ (ሕጻኑ በተጠመቀበት ማይ) እናቲቱንና ክርስትና የሚያነሱ ሰዎችን መርጨት ትልቅ ውንብድና ነው። ማየ ገቦ ልጅነት የሚያሰጥ ስለሆነ ሕጻኑ ብቻ ይጠመቅበታል እንጂ ለሌላ ሰው አይረጭም።

ስለ አዋላጆች (መወልዳት) በፍትሐ ነገሥት ተነግሯል። ይኽውም ሴት ያዋለዱ አዋላጆች እስከ ፵ ቀን ቤተክርስቲያን እንዳይገቡ፣ ወንድ ያዋለዱ አዋላጆች ደግሞ እስከ ፳ ቀን እንዳይገቡ ሥርዓት ተሠርቷል። በዘመናችን ደግሞ አዋላጅ ነርሶች (Midwives) አሉ። ሥራቸው ማዋለድ ነው። ለእነርሱ ዘለዓለም ቤተክርስቲያን አይግቡ የሚል ትምህርት የለንም። ሥርዓቱ ሲሠራ በነበረው ዘመን የነበሩ አዋላጆች እና አሁን ያሉ አዋላጆች ሚናቸው የተለያየ ስለሆነ ለአሁን ዘመን አዋላጆች የሚመጥን ሥርዓት እንዲሠራልን በዚሁ አጋጣሚ ለቅዱስ ሲኖዶስ የምናሳስበው ይሆናል ማለት ነው። ምክንያቱም የአሁን አዋላጆች ያለምንም ደም ንክኪ ሊያዋልዱ የሚችሉበት መንገድ ስለሚኖርና ጥንቃቄያቸው ከቀድሞው ከፍ ያለ ስለሆነ ነው። ሕክምናን በተመለከተ የቀዶ ሕክምና ሐኪሞችን ሁሉ ያካተተ ሥርዓት ቢሠራ መልካም ነው።

ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን።
357 views19:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-21 20:40:47
በቅርብ ጊዜ ውስጥ በቅዱሳን ጳጳሳት በኩል እግዚአብሔር ምን እየነገረን ነው ??

"የአባቶቻችን የከበረች በረከታቸዉ ድል የማትነሣ ረድኤታቸዉ ጥርጥር የሌለባት ሃይማኖታቸው ከኛ ጋር ትሁን"

ብፁዕ አባታችን በረከትዎ ይደርብን
779 viewsedited  17:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-21 20:39:57 ብሒላተ አበው ወእመት ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ pinned «"የከበረች በረከታቸው ድል የማትነሣ ረድኤታቸው ጥርጥር የሌለባት ሃይማኖታቸው ከእኛ ጋር ትኹን ሥሉስ ቅዱስን ያለ ማጉደል ያለ መጨመር እናምናለንና ክፋዎች ሰዎች ከመከሩት ምክር ከሰይጣን ጠላትነት ታድነን ለዘለዓለሙ አሜን፡፡" @behlateabew @behlateabew @behlateabew»
17:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-21 20:39:33 ብሒላተ አበው ወእመት ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ pinned «“ክርስቶስ አምላኬና ተስፋየ ነው ፣ የአባቱም ስም የመድኃኒቴ ዘውድ ነው፣ የመንፈስ ቅዱስም ስም የቅድስናየ መገኛ ነው፡፡ እመቤታችን ማርያም የገነት መክፈቻየ ናት፣ የከበረች ቤተክርስቲያን የጥምቀት ጉድጓዴ ናት፣ ሐዋርያትም አጥማቂወቼ፣ የበለሳን ቅባትም የእምነቴ ማህተም ነው፣ የቅዱሳንም ሁሉ ገድል የሐጢአቴ ማስተሰሪያ ነው፤ ለዘላለሙ አሜን፡፡” (አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ - መፅሃፈ ምስጢር) …»
17:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-21 20:39:22 ብሒላተ አበው ወእመት ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ pinned «ወዮ ይህች ዕለት አብ የቀደሳት ወልደ የባረካት መንፈስ ቅዱስ ከፍ ከፍ ያደረጋት ናት፡፡ በርሷ ደስ ይበለን፡፡ በርስዋም ኀሤት እናደርጋግ ትከብሩባት ዘንድ አክብሯት ዘመን ወር ለመባል በርሷ የታወቃችሁ ሌሎች ዕለታት ሆይ የበዓላትን በኩር ኑ አመስግኗት ይህችውም የከበረች ሰንበተ ክርስቲያን ናት፡፡ ቅዳሴ አትናቴዎስ @behlateabew»
17:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ