2022-06-12 19:45:15
<<እንጾማለን!!>>
አስ 4፥16
ከነገ ጀምሮ ኦርቶዶክሳዊ የሆነ ሁሉ ሊናገረው ይሚገባ ቃል፣ ሊተገብረው የሚገባ መንፈሳዊ ተግባር ይህ ነው።
<<ለእኔም ጹሙ ሦስት ቀን ሌሊቱንና ቀኑን አትብሉም፥ አትጠጡም እኔና ደንገጥሮቼ ደግሞ እንዲሁ እንጾማለን።>>
ይህን ያለችው አስቴር ናት።ይህን እንድትል ያስገደዳት መከራ ነው።በወገኖቿ ላይ ሞት አንዣቦ ነበር። ሞቱን ወደሕይወት ለመለወጥ ከሚያስፈልጉ ነገሮች ዋነኛው ጾም ነው። ስለዚህ ነው <<እንጾማለን !>> ያለችው እኛስ? ከመከራ ከሞት ነፃ ነን ? እኛም ከመከራ፣ከሞት ያድናልና። <<እንጾማለን>>
እኛም ከነገ ጀምሮ እንጾማለን ምክንያቱም ዛሬ በዓለ መንፈስ ቅዱስን አክብረናል ።በዓለ ፋሲካን ፈጽመናል። ነገ ጾመ ሐዋርያት ይጀምራል።ስንበላ ቆይተናል።አሁን <<እንጾማለን!>> በቃ ሰው በእንጀራ ብቻ አይኖርም። በእግዚአብሔር ቃልና በጾምም ነው እንጂ።ስለዚህ እንጾማለን። ጌታችን እንዲህ አስተምሮናልና።
<<በዚያን ጊዜ የዮሐንስ ደቀ መዛሙርት ወደ እርሱ ቀርበው፦ እኛና ፈሪሳውያን፥ ብዙ ጊዜ የምንጦመው፥ ደቀ መዛሙርትህ ግን የማይጦሙት ስለ ምንድር ነው? አሉት።
ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፦ ሚዜዎች ሙሽራው ከእነርሱ ጋር ሳለ ሊያዝኑ ይችላሉን? ነገር ግን ሙሽራው ከእነርሱ የሚወሰድበት ወራት ይመጣል፥ በዚያ ጊዜም ይጦማሉ።>>
ማቴ ፱÷፲፬
ሙሽራው ክርስቶስ ነው የሚወሰድበት ጊዜው ዕርገት ነው ጌታችን አርጓል ሚዜዎች የሚጾሙበት ጊዜደርሷል። በአሮጌ አቆማዳ የተመሰለ የሐዋርያት ሰውነታቸው በመንፈስ ቅዱስ መውረድ ታድሷል።አሮጌው አቆማዳ ከአሬጌው ወይን ጋር አልፏል።አሁን አዲሱ የወይን ጠጅ በመንፈስ ቅዱስ በታደሰው አዲስ አቁማዳ የሐዋርያት ሰውነት ተጨምሯል።
<<ያን ጊዜ ይጾማሉ።>> ይጾማሉ የተባለው ጾመ ሐዋርያት ነው። የሥራቸው መጀመሪያ ጾም ነው። ስለዚህም እኛም ኦርቶዶክሳውያን ክርስቶስን መስለን ሐዋርያትን ተከትለን <<እንጾማለን!>> ሀገራችን ከመከራ ሕዝባችን ከሞት እንዲተርፍ በረከተ ሥጋን በረከተ ነፍስን ለማግኘት <<እንጾማለን>>
የቅዱሳን ሐዋርያት ጾም የእኛም የልጆቻቸው ጾም ነው። ስለዚህ ኦርቶዶክሳዊ ሁሉ ከነገ ሰኔ ፮-፲-፳፻፲፬ ዓም ጀምሮ እስከ ሀምሌ ፭-፲-፳፻፲፬ ድረስ <<እንጾማለን!!!>>
እንበላለን ማለት ሳያሳፍር እንጾማለን ማለት ሊያሳፍር አይገባም!!።
ስለዚህ ሁላችን እንጾማለን !!
ጾሙን ፈጽመን የቅዱሳን ሐዋርያትን በረከት እንድናገኝ አምላካችን ይፍቀድልን !!
መልካም ጾመ ሐዋርያት
መጋቤ ሐዲስ ምስጢረ ሥላሴ ማናዬ
ሰኔ ፭-፲-፳፻፲፬ ዓ/ም
4.5K views16:45