2022-06-19 04:56:33
የሰኔ ፲፪ በዐላት ዐርኬ ከነትርጕሙ
፩ ፤ አፎምያ ።
ሰላም ፡ ለአፎምያ ፡ ዘሞዐቶ ፡ ለመስቴማ ።
በቃለ ፡ ትምይንት ፡ ሶበ ፡ ተቃወማ ።
በዛቲ ፡ ዕለት ፡ በከመ ፡ ዐደማ ።
ሥዕሎ ፡ ለሚካኤል ፡ እንዘ ፡ ታነብር ፡ በፍጽማ ።
ውስተ ፡ ዘለዐለም ፡ ዕረፍት ፡ ፈለሰት ፡ እምፃማ ።
ትርጕም፦
ሰላም ለአፎምያ ሰይጣንን ላሸነፈችው፤
በሽንገላ ቢቃወማት አሳፍራ ለላከችው።
ሚካኤል በቀጠራት በዛሬው ቀን በከበረው፣
ሥዕሉን ከደረቷ እንደ ያዘች ሳትነጥለው፣
የዐለምን ከንቱ ድካም በዕረፍቷ አለፈችው።
፪ ፤ ዮስጦስ ።
ሰላም ፡ ለዮስጦስ ፡ ማርቆስ ፡ ዘአጥመቆ ።
ምስለ ፡ አቡሁ ፡ ወእሙ ፡ በአስተላጽቆ ።
ረሢኦ ፡ በንጽሕ ፡ ወበቅድስና ፡ ልሂቆ ።
በዛቲ ፡ ዕለት ፡ ዘአልቦ ፡ ናፍቆ ።
በድሮ ፡ ፈጸመ ፡ ወሠለጠ ፡ ፃሕቆ ።
ትርጕም፦
ሰላም ለዮስጦስ ማርቆስ ላጠመቀው፤
ከአባቱና ከእናቱ ጋር በክርስቶስ ላሳመነው።
ንጽሕና ቅድስናን አስተባብሮ እስከ እርጅናው፣
ሩጫውን አጠናቆ ከድካሙ እፎይ ያለው፣
ሚካኤል በዋለባት በዛሬዋ ልዩ ቀን ነው።
፫ ፤ ቄርሎስ ።
ሰላም ፡ ዕብል ፡ ለቄርሎስ ፡ ሊቅ ።
ጵጵስናሁ ፡ ዘኮነ ፡ በትንቢተ ፡ ብእሲ ፡ ጻድቅ ።
ለዝ ፡ ማእምር ፡ እምስብሐተ ፡ ዐለም ፡ ርሑቅ ።
በውኂዘ ፡ ቃሉ ፡ ለምለሙ ፡ አዕፁቅ ።
ወበትምህርቱ ፡ ነበሩ ፡ ወልህቁ ፡ ደቂቅ ።
ትርጕም፦
ሰላም እላለኹ ለቄርሎስ ለምሁሩ ለኾነው ሊቅ፤
ለጵጵስና ለበቃው ትንቢቱ ደርሶ በአንድ ጻድቅ።
በዚኽ ምሁር ታላቅ ጳጳስ ከውዳሴ ከንቱ የሚርቅ፣
በቃሉ ፈሳሽነት ለመለመ የዛፎች ዐፅቅ፤
በትምህርቱም ተለወጡ ከልሂቅ እስከ ደቂቅ።
፬ ፤ ላሊበላ ።
ሰላም ፡ ለላሊበላ ፡ ሐናፄ ፡ መቅደስ ፡ በጥበብ ።
በዕብን ፡ ይቡስ ፡ እንበለ ፡ መሬት ፡ ርጡብ ።
ነሢኦ ፡ መባሕተ ፡ እምእግዚአብሔር ፡ አብ ።
በዘይትአመር ፡ ሎቱ ፡ ምስፍና ፡ ወምግብ ።
ወዝንቱ ፡ መዐር ፡ ተድላ ፡ ነገሥት ፡ ወሕዝብ ።
በዕለተ ፡ ተወልደ ፡ ተውህቦ ፡ ተዐግተ ፡ በንህብ ።
ትርጕም፦
ሰላም ለላሊበላ መቅደስን የሠራ በጥበብ፤
በደረቅ ድንጋይ ብቻ ሳያስነካ አፈር ርጥብ።
ሀብተ መንግሥቱ ታውቆለት ሹመቱ ከእግዚአብሔር አብ፣
ሀገርን እንዲያስተዳድር ሰው እንዲመራ ያለ ጠብ፣
ምልክት ይኾነው ዘንድ በሥልጣኑ እንዲመግብ፣
ይኼ መዐር የነገሥታት ደስታቸው የኹሉም ሕዝብ፣
ገና ሲወለድ ተሰጠው ተከቦ በነጭ ንብ።
ምንጭ፥ የሰኔ ፲፪ ቀን ስንክሳር፣
ትርጕም፦ ኤፍሬም የኔሰው።
4.8K views01:56