Get Mystery Box with random crypto!

ሰኔ 30 የቅዱስ ዮሐንስ መጥምቀ መለኮት ልደቱ ነው በዚህች ቀን የጌታን መንገድ ጠራጊው፤ ሐዋርያ | ብሒላተ አበው ወእመት ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ

ሰኔ 30 የቅዱስ ዮሐንስ መጥምቀ መለኮት ልደቱ ነው

በዚህች ቀን የጌታን መንገድ ጠራጊው፤ ሐዋርያው፤ ነብዩ ሰማዕቱ ቅዱስ ዮሐንስ የልደት ቀኑ ነው፤ መስከረም 2 አንገቱ የተቆረጠበት ነው ሚያዚያ 15 እረፍቱ ነው፤ አንገቱ ከተቆረጠ በኋላ የተቆረጠች አንገቱ ክንፍ አውጥታ ለ15 ዓመት በሳውዲ አረቢያና አካባቢው ወንጌልን ሰብካለች፤ የካቲት 30 ቀን የዮሐንስ ራስ የተገለጸችበት ቀን ነው። ከነዚህ አራት በዓላት ሁለቱን ቤተክርስቲያን ታቦተ ህጉን አውጥታ በደማቁ ታከብረዋለች እነዚህም ሰኔ 30 ልደቱና መስከረም ሁለት አንገቱ የተቆረጠበትን ቀን ነው።

ጨካኝ ሄሮድስ የቤተልሔም ህጻናትን ሲጨፈጭፍ መጥምቁ ዮሐንስ ከእናቱ ከቅድስት ኤልሳቤጥ ጋር ወደ ሲና በርሃ ተሰደደ፤ ኤልሳቤጥ በጣም አርጅታ ነበር ያን በረሃ ታዲያ እንዴት ቻለችው ያውም ልጅ አዝላ ልጅ ተሸክማ ረዳት ሳይኖራት ብቻዋን፤ አባቱ ዘካርያስ በምኩራብ በመሰዊያው ፊት ልጅህን አምጣ ብለው አንገቱን ቆርጠው ገደሉት። ኤልሳቤጥም ሲና በርሃ ላይ ሞተች ህጻኑ ዮሐንስ ብቻውን ቀረ፤ የእናቱን በድነ ስጋ አቅፎ አለቀሰ፤ሁሉን ቻይ ሁሉን የሚያይ፤ ሁሉን የሚመረምር ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለእመቤታችን እናቴ ሆይ ዘመድሽ ኤልሳቤጥ በበርሃ አርፋለች እንቀብራት ዘንድ እንሂድ አላት ደመና ጠቅሰው ዮሴፍና ሰሎሜን አስከትለው ሄደዋል ገንዘውም ቀብረዋታል፤ ከዚህ በኋላ እመቤታችን ልጄ ወዳጄ ሆይ ዮሐንስን ይዘነው እንሂድ አለችው የለም እናቴ፤ እርሱ እዚው ይቆያል መንገዴን ጠራጊ ነው፤ ኑሮው በዚሁ በርሃ ነው፤ ጊዜው ሲደርስ ወደ ዮርዳኖስ ይመጣል ያጠምቀኝማል ያኔ አንድነቴ ሶስትነቴ ይገለጣል አላት፤ ትተውት ተመለሱ።

ከመሞቷ በፊት እናቱ ያሰፋችለትን የግመል ቆዳ አገልድሞ አንቦጣ የሚባል ቅጠልና የበርሃ ማር እየበላ በበርሃ ኖረ 30 ዓመት ከ 6 ወር ሲሆነው፤ “የጌታን መንገድ አዘጋጁ ጥርጊያውንም አቅኑ” እያለ ከበርሃ ወጣ ሉቃ 3፥3። "እውነት እላችኋለሁ፥ ከሴቶች ከተወለዱት መካከል ከመጥምቁ ዮሐንስ የሚበልጥ አልተነሣም፤" ማቴ 11፥11። ይህ የጌታችን ምስክርነት ነው።

ከበዓሉ በረከት ያሳትፈን።