Get Mystery Box with random crypto!

ብሒላተ አበው ወእመት ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ

የቴሌግራም ቻናል አርማ behlateabew — ብሒላተ አበው ወእመት ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ
የቴሌግራም ቻናል አርማ behlateabew — ብሒላተ አበው ወእመት ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ
የሰርጥ አድራሻ: @behlateabew
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 13.08K
የሰርጥ መግለጫ

የቀድሞ አበው እና እመት የተናገሯቸው መንፈሳዊ ጥበብ
"የእግዚአብሔር ልጅ ሰው የሆነው እኛ አማልክት ዘበጸጋ እንሆን ዘንድ ነው።"
ቅዱስ አትናቴዎስ
👇👇👇👇👇👇👇👇
👉 @behlateabew 👈
👉 @behlateabew 👈
👆👆👆👆👆👆👆👆
https://t.me/joinchat/AAAAAESAiVPCib48ZxL1Pw

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 7

2023-04-11 07:48:48 "አይሁድም ከሰው ልጅ ይልቅ ደም ግባቱ በሚያምር በጌታችን በኢየሱስ ፊት ላይ ምራቅ ያበዛላቸው ዘንድ ባፋቸው ውሃ እየጨመሩ ምራቃቸውን ሰባ ሦስት ጊዜ ተፉበት። ፊቴን አይቶ የሚድን የለም ብሎ በተናገረ በጌታችን ፊት ላይ ተፉበት።
እሱ ግን ምራቃቸውን ተጸይፎ ፊቱን አልመለሰም። ጌታችን ኢየሱስም የሚያጸይፍ ምራቅን በፊቱ ላይ በመቀበሉ በኃጢአት የጠቋቆረና የኃጢአት ቅባት የተቀባ ፊታችንን ደስ በሚያሰኝ ቅባቱ ብሩህ ያድርገው።"

የማክሰኞ ድርሳነ ማኅየዊ
429 viewsedited  04:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-10 07:07:04 ... ይሁዳም ያን ጊዜ መምህር ቸር ውለሃል? ብሎ በተንኰል ሳመው። ጌታችን ኢየሱስም ይሁዳን ወዳጄ የሰውን ልጅ በመሳም አሲዘህ ልታስገድለው መጣህን አለው። ጠላቱ ሲሆን ጠላቴ አላለውም፤ ወዳጄ አለው እንጂ። ኀዳጌ በቀል ልቡናው ትሑት ጠላቱን ወዳጅ ነውና። ይሁዳ ግን እጁን ዘርግቶ አንገቱን በቀሚሱ ያዘው።
ይሁዳም አይሁድን ዓሥራችሁ ይዛችሁ ውሰዱት። ከእንግዲህ ወዲህ ቢያመልጣችሁ ዕዳ የለብኝም አላቸው።

ድርሳነ ማኅየዊ ዘሰኑይ
499 viewsedited  04:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-10 05:40:15 ✥✥✥ ዕለት ሰኞ ✥✥✥

- ይህ ዕለት አንጽሖተ ቤተ መቅደስ እና መርገመ በለስ የተፈጸመበት ዕለተ ነው፡፡ በቅዱስ ማርቆስ ወንጌል እንደተገለጠልን ጌታችን ከቢታንያ ወጥቶ ወደ ኢየሩሳሌም ሲሄድ ተራበ፡፡ በለስም ከሩቅ ዓየ፣ በለስዋ ግን ከቅጠል ብቻ በቀር ፍሬ ምንም ኣላገኘባትም ስለዚህ ከእንግዲህ ወዲህ ለዘለዓለም ፍሬ ኣይገኝብሽ ከአንቺ ፍሬ የሚበላ ኦይኑር አላት ያን ጊዜውንም በለሲቱ ደርቃለች (ማር.11፥12-19/ማቴ.21፥19/ሉቃ.19፥45-46)

በለስ የተባለች ኦሪት ናት፡- በለስ አገኘ ማለቱ ኦሪት በዚህ ዓለም ሰፍና አገኛት ሲል ነው፡፡ ወደ እርስዋም ሄደ ማለት ፈጻሜ ሕግ ተባለ (ሥርዓተ ኦሪትን ማለት በ8ኛው ቀን መገዘር በ40 ቀን መሥዋዕት ማቅረብን... እየፈጸመ አደገ) ማለት ነው፣ ፍሬ አላገኘባትም አለ ሕግ ከመባልዋ በቀር ድኅነትን አላደረገባትም፣ ፍሬ አይገኝብሽ አላት ሲል፡- ባንቺ ድኅንነት አይደረግ አላት፡፡ ይህም ቅዱ ዳዊት ‹‹መሥዋዕትን ቁርባንን አልወደድሁም ሥጋህን ኣንጻልኝ፣ የሚቃጠለውንና ስለኃጢኣት የሚቀርበውን መሥዋዕት አልወደድሁም ሲለ የኦሪትን ሕግ (ዐሠርቱ ትዕዛዛትን) አሳለፋቸው ማለት አይደለም፡፡ ቅዱስ ዳዊት እንደነገረን በመሥዋዕተ ኦሪት ፍፁም ድኅንነት ኣለመገኘቱን አውቆ ማሳለፉን እና ፍፁም ድኅንነት የምናገኝበትን ቅዱስ ሥጋውን እና ክቡር ደሙን መሥዋዕት አድርጎ ማቅረቡን ያሳያል፡፡››

አንድም፦ በለስ ያለው ኃጢኣትን ነው፡፡ የበለስ ቅጠል ሰፊ እንደሆነ ኃጢኣትን በዚህ ዓለም ሰፍና ኣገኛት፡፡ ወደ እርሷ ሄደ ፍሬም አላገኘባትም ማለት በአይሁድ አንደበት በሐሰት ኃጢኣተኛ ተባለ እንጂ (ስለ እኛ መተላለፍ እንደበደለኛ ተቆጠረ እንጂ) ኃጢኣትን አልሠራም ሲል ነው፡፡ ፍሬ አይገኝብሽ ሲል፡- ባንቺ በመጣ ፍዳ የሚያዝ አይኑር አላት ማለት ነው፡፡

ከዚህ በመቀጠል ጌታችን ወደ ኢየሩሳሌም በደረሰ ጊዜ ወደ ቤተ መቅደስ ገባ፡፡ ቤተ መቅደሱም ቤተ ጸሎት፣ ቤተ መሥዋዕት መሆኑ ቀርቶ ቤተ ምስያጥ (የንግድ ቤት) ሆኖ ቢያገኘው ቤቴ የጸሎት ቤት ትባላለች እናንተ ግን የወንበዴዎች ዋሻ አደረጋችኋት ብሎ በዚያ ያሉትን ሁሉ አስወጣቸው፡፡ ይኸም በጠቅላላው ማደሪያው ቤቱ የነበርን የአዳም ለጆች ኃጢኣት ሰፍኖብን ስንኖር ቢያገኘን ኃጢኣታችንን ሁሉ እንዳራቀልን የሚገልጽ ነው፡፡ (ማቴ.21፥12-17/ማር.11፥15-24/ሉቃ.19፥4)
594 views02:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-10 05:40:11
508 views02:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-09 16:27:39
464 views13:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-09 06:16:59 “ፍቅርህ ከዘባነኪሩብ አውርዶ በአህያ ጀርባ ላይ እንድትቀመጥ አስገደደህ፡፡ ብዙ ዐይንና ብዙ ገጽ ካላቸው ከሰራዊተ መላክእት ይልቅ በዲዳዋ አህያ ትመሰገን ዘንድ ወደድክ፡፡ በሰማይ ሰራዊት ሠረገላ ተቀምጠህ ክብርህን ማሳየት አልወደድክም፤ በውርንጭላይቱ ላይ ተቀምጠህ ወደ ሰማይ ሰራዊት መሄድን መረጥክ እንጂ፡፡ በአርያም እሳታውያን የሚሆኑ ኪሩቤል ያመሰግኑሃል፤ በምድርም ሕፃናት ይዘምሩልሃል፡፡ በአርያም ብርሃናውያን መላእክት በብርሃን ክንፋቸው መንገድህን ያነጥፉልሃል፤ በምድርም ደቀ መዛሙርትህ ልብሳቸውን አንጥፈው መንገድህን አስተካከሉ፡፡

ወዮ! አርያማዊ ሲሆን ምንም ሳይንቀን ይጐበኘን ዘንድ ከአባቱ መጣ፡፡ እርሱም በገዛ ፈቃዱ ሰው እስከመሆን ደርሶ መጣ፡፡ በአህያ ላይ ተጭኖም ይጐበኘን ዘንድ መጣ፡፡ ነቢዩ ዘካርያስ የመንፈስ ቅዱስን እንዚራ ይዞ በደስታ ትንቢትን ለመናገር ይቻኰላል፡፡ እየደረደረም የጽዮንን ልጅ ይጠራታል፡፡”

#ሊቁ_ያዕቆብ_ዘሥሩግም
174 views03:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-08 23:02:32
"ከመድኃኒትነቱ የተነሳ ከቤቱ መሠረት ሳይናወጥ ከልዑል መንበሩ ወረዶ ጸጋንና ኃይልን አሳየ ። ሆሣዕና በአርያም ሆሣዕና በአርያም ሆሣዕና በአርያም። "
          ቅዳሴ ጎርጎርዮስ

እንኳን ለበዓለ ሆሣዕና በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ። አምላከ ቅዱሳን ለብርሃነ ትንሣኤ በሰላም ያድርሰን!!!
335 views20:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-08 12:55:09 ወገኖች! Apostolic Succession (ሐዋርያዊ ሰንሰለትን) በመጠበቅ ተወዳዳሪ የሌላት ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ላለፉት 2000 ዓመታት በተቀደሰው ትውፊት (Holy Tradition) አማካኝነት ቅዱሳት መጻሕፍትንና ከእነርሱ የሚመነጨውን ርቱዕ (የቀና) አስተምህሮ ያስረከበችን፣ ማንም የመሰለውን መላምት እያመጣ ከቀጥተኛው (ኦርቶዶክሳዊ) መንገድ እንዳይወጣ አጥር ሆነው የሚጠብቁ Holy Canons (ቅዱሳት ቀኖናት) ስላሏት ነው፡፡ ይህን ለመረዳት ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያለውን የአምልኮ ውበት እና ሥርዓት፣ Protestantism ውስጥ ካለው ቀውስ (chaos/anarchy) ጋር በማነጻጸር መረዳት ይቻላል፡፡ ኢየሱስ ስላልን ተወገዝን ተባረርን የሚሉ አካላት ይህንን በመናድ ቤተክርስቲያኒቱን ማተረማመስ የሚሹ አካላት ናቸው።

በጥራዝ ነጠቅ አካሔድና አነጋገር፣ በዘመናት ተፈትኖ ያለፈውንና በምድር ላይ ሆነን ሰማያዊ ሐሴትን እንድንለማመድ የሚያደርገንን ኦርቶዶክሳዊ ሥርዓተ አምልኮ ሸርሽረን እንደ አንዳንድ ሥርዓት እንደሌላቸው ቤተእምነቶች ወደ ሥርዓት አልበኝነት እንዳንገባ የሚያደርጉ ስሑት አስተምህሮዎችንና አካሔዶችን ታርማለች ትመክራለች ትገስጻለች አልሰማም ካለ ሌላውን እንዳይበክልና መለያየት እንዳይፈጠር አውግዛ ትለያለች። በዚህ ስህተታቸው ሲወገዙ ኢየሱስ ስላልን ተወገዝን ብለው መሸሸጊያ ፍለጋ ሊያሳብቡ ይችላሉ። ኢየሱስ ስላለ የሚባረርና የሚወገዝ ቢኖር ኖሮ አንድም ቀዳሽም ሆነ ኪዳን አድራሽ ካህን ባልተገኘ ነበር። ውሸት ነውና ዝም ብለው ለሚዋሹ ዋሾዎች ስንሰማ ጥንቃቄ ልናደርግ ይገባል፡፡

ከአባ ጌዴዎን ዘደብረሊባኖስ ለሶፍያ ሽባባውና መሰል ምልከታ ላላቸው ሁሉ ተጻፈ 29/07/2015 ዓም
618 views09:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-08 12:55:07 አሁን በክርስቶስ ልትድን የምትችለው ነፍስ ክርስቶስን ከማመን በላይ ከፍ ብላ በማደግ ክርስቶስን መምሰል አለባት። ይህም ሦስት ነገሮችን አጠቃሎ ማለትም፦ ሥጋን ፣ነፍስንና መንፈስን በመጠበቅና በመቀደስ ቅዱስ የሆነ ኑሮ ስንኖር እግዚአብሔርን ስንመስል መዳናችን ተጠብቆ እውን ይሆናል።ይህም በሀይማኖት ጸንቶ መኖር በሚል ተገልጧል።

"የደቀ መዛሙርትን ልብ እያጸኑ በሃይማኖትም ጸንተው እንዲኖሩ እየመከሩና። ወደ እግዚአብሔር መንግሥት በብዙ መከራ እንገባ ዘንድ ያስፈልገናል እያሉ(ሐዋ 14:21-22) ተብሎ ተጽፏል።

ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ክርስቶስ የመሠረታት ሐዋርያት ያስፋፏት ናትና ቅዱሳን ሐዋርያት በመልእክታቸው እንዲህ ብለውናል።
"ወደ እግዚአብሔር መንግሥት በብዙ መከራ እንገባ ዘንድ ያስፈልገናል" እያሉ የእውነትን ወንጌል ሰበኩ። ከዚህ መልእክት አንጻር፦

የሐዋርያት ቃል ሲብራራ "ድኛለሁ ተፈውሻለሁ ዘና በል" የሚል ወንጌል አለመኖሩ ነው።The Lord Jesus opened heaven, not closed hell (ጌታ ኢየሱስ ገነትን ከፈተ እንጂ ሲኦልን አልዘጋም)። ከአዳም የኃጢአት ውጤት ያዳነን ብቸኛው አዳኝ እርሱ ቢሆንም ክርስቶስ መስቀሌን ተሸከመልኝ ብለን የምንተወው መስቀል የለም።

"የተጠራችሁለት ለዚህ ነውና፤ ክርስቶስ ደግሞ ፍለጋውን እንድትከተሉ ምሳሌ_ትቶላችሁ ስለ እናንተ መከራን ተቀብሎአልና።" ብሎናል። (1ኛ ጴጥ 2:21) የተወልን ፍለጋው Living in struggle and carrying the cross(መስቀሉን መሸከም በተጋድሎ መኖር) ነው። ስለዚህ "በጠበበው በር ለመግባት ተጋደሉ፤ እላችኋለሁና፥ ብዙዎች ሊገቡ ይፈልጋሉ አይችሉምም" ብሎ እውነቱን ነግሮናል።(ሉቃ 13:24) ባለው ቃል መሠረት ድህነትን መጠበቅ ማሳደግና መጋደል መስቀሉንም መሸከም ግድ ነው።

ስለዚህ ለመዳን አራት ነገሮችን መያዝ ግድ ይልሃል

በሥርዓተ አምልኮ መጽናትና መሳተፍ ይህም
ምስጢራትን መፈጸም(መጠመቅ ሜሮን
ቁርባን መቀበል)
መንፈሳዊ ተጋድሎ(ጾም ጸሎት ስግደት)።
መልካም ስራ (ትህትና ፍቅር ምጽዋት)
ያስፈልግሃል።

በአጠቃላይ ያለ ክርስቶስ ኦርቶዶክስን ማሰብ መኪና ያለነዳጅ ያለምንም ኃይል መብረሩን ያቁም እንደማለት ነው። ክርስቶስን “እኛ ራሳችን ሰምተነዋልና፤ እርሱም በእውነት ክርስቶስ የዓለም መድኃኒት እንደ ሆነ እናውቃለንና” (ዮሐ4፥42) እንደተባለ እኛም እንዲሁ እንላለን።

እምነታችን በሐዋርያው እንደተገለጸው ይህ ነው። “መዳንም በሌላ በማንም የለም፤ እንድንበት ዘንድ የሚገባን ለሰዎች የተሰጠ ስም ከሰማይ በታች ሌላ የለምና።” — ሐዋርያት 4፥12 ጌታችንን አምላካችንንና መድኃኒታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን የተቀበልንው መዳን በእርሱ የሆነ አዳኝ መድኃኒት ስለሆነ ነው። እኛስ ኢየሱስ በተባለ በ ክርስቶስ ስም አምነናል አውቀናል በእርሱ እንኖራለን ደግሞም እንድናለን ድነንማል።

በተረፈ ጠቀለል አድርጌ ስመልስ ስለመጽሐፍ ቅዱስ ላነሳሽው።፦ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ የእምነት አስተምህሮ መሠረቶች 3 ናቸው።


1, ዶግማ= (የማይሻር የማይሻሻል የመጽሐፍ ቅዱስ ሙሉ መልእክት ሲሆን ለድርድር የማይቀርብ ጽኑ መሠረት ነው)
2, ቀኖና = (ቤተክርስቲያን እየተጠበቀች እዚህ የደረሠችበት የአባቶች ሲኖዶሳዊ ውሳኔዎች)
3, ትውፊት = (በቅብብሎሽ ሲወርድ ሲወራረድ የመጣ የዶግማ መጠበቂያ አጥር)

የትውፊት ትክክለኛነት 3 መመዘኛዎች

, ማንኛውም ትውፊት የመጽሐፍ ቅዱስን ሐሳብ ተጻርሮ ወይም ተቃርኖ ከተገኘ በምንም ዓይነት ሁኔታ ተቀባይነት የለውም።

, ማንኛውም ትውፊት እርስ በእርሱ ተጣርሶ ከተገኘ በጭራሽ ተቀባይነት የለውም።

, ማንኛውም ትውፊት የሌሎች አኃት አብያተ
ክርስቲያናትን አስተምህሮ ተቃርኖ ከተገኘ
ተቀባይነት የለውም።

ትውፊት እነደየ ሁኔታው ሊሻሻል ይችላል። ትውፊትን የማሻሻል ሥልጣን ያለው ቅዱስ ሲኖዶስ ብቻ ሲሆን የሕዝብ አስተያየትን መነሻ በማድረግ የሊቃውንት ጉባኤ መርምሮ የውሳኔ ሐሳብ ሲያቀርብለት ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል ሊያሻሽለው ይችላል።

ትውፊት እንዲሻሻል የሚያደርጉ 3 ገፊ ምክንያቶች

, ከሕዝብ ንቃተ ኅሊና ጋር መጣጣም ካልቻለ
የአካባቢ ሁኔታ ቢቀየር (enviromental change) ለምሳሌ ለመጾም የማያስችል የአየር ሁኔታ ቢፈጠር
የፖለቲካ ሁኔታ በተቃራኒዎች በብልጫ ሲመራና እንደ ቀድሞው ለመገልገል አስቸጋሪ ሲሆን

በዝርዝር ለማሳየት ያህል እስኪ ዶግማ ምንድን ነው? ቀኖና ትውፊትስ?

ዶግማ በዓለም አቀፍ ጉባኤያት (ecumenical councils) የጸደቀ የኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን እምነት ሲሆን፤ ቤተ ክርስቲያን ከአበው የተቀበለችውን እምነት የምትገልጥባቸው አስተምህሮዎች ደግሞ doctrines ይባላሉ፡፡ ለምሳሌ፡- “ኢየሱስ ክርስቶስ የባሕርይ አምላክ ነው” ይህ ዶግማ ነው፤ “ድንግል ማርያም ወላዲተ አምላክ ናት” ይህም እንደዚሁ፡፡ የክርስቶስን አምላክነት ለማይቀበሉ አርዮሳውያን፣ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን የቅዱስ አትናቴዎስ ዘእስክንድርያን አስተምህሮ (doctrine) ተከትላ መልስ ሰጥታለች፤ ስትሰጥም ትኖራለች፡፡ ድንግል ማርያምን ወላዲተ አምላክ (Theotokos) ብለው ለመቀበል ለሚቸገሩ ንስጥሮሳውያን ደግሞ፣ እንዴት ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም “ወላዲተ አምላክ” እንደምትባል የምንገልጥበት ወይም የምናስተምርበት ዶክትሪን፣ ቅዱስ ቄርሎስ ዘእስክንድርያ ያስተማረው ትምህርት ነው፡፡

እነዚህ አስተምህሮዎች በዓለም አቀፍ ጉባኤያት የተወሰኑ ሲሆን፣ ውሳኔያቱን ከተጨማሪ ጉዳዮች ጋር የቤተ ክርስቲያን አበው በቀኖናት (canons) አጽድቀዋቸዋል፡፡ ለምሳሌ እንደ አውሮጳውያኑ አቆጣጠር በ325 ዓመተ እግዚእ (AD) የተጠራው ጉባኤ ኒቅያ 20 ቀኖናት አሉት፡፡ እነዚህንና ሌሎቹን ዓለም አቀፋዊና ብሔራዊ ውሳኔያት፣ ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ከርስቲያን Holy Canons (ቅዱሳት ቀኖናት) በማለት ትጠራቸዋለች፡፡ ስለዚህ እነዚህ ቅዱሳት ቀኖናት በመንፈስ ቅዱስ መሪነት በዓለም አቀፍ ጉባኤያተ አበው የጸደቁና የቤተ ክርስቲያንን ዶግማ የሚያንጸባርቁ (ከዶግማዋ ጋር የሚስማሙ እንጂ፣ የማይጋጩ) ናቸው፡፡

“ቀኖናት ይሻሻላሉ/ ይለወጣሉ” ሲባል “እንደ ቀኖናው ዓይነት ይወሰናል፤ የሚለወጥና የማይለወጥ አለ”፡፡ ለምሳሌ የክርስቶስን የባህርይ አምላክነት ወይም የመለኮትና ትስብእትን ተዋሕዶ አስመልክቶ ቅዱሳን አባቶቻችን የወሰኗቸው ቀኖናት Dogmatic Canons ስለሆኑ ማንም ተነሥቶ ሊለውጣቸው አይችልም፡፡ Practical የሆኑ ጉዳዮችን በሚመለከቱ ቀኖናት ላይ ግን፣ በሐዋርያት መናብርት የተሾሙ አበው ወይም የእነርሱ ተከታዮች (ተላውያነ አበው) የሆኑ የብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ጉባዔ (ቅዱስ ሲኖዶስ) ማሻሻያ ማድረግ ይችላል፡፡ ማሻሻያ ከተደረገባቸው practical canons መካከል አንዱን ልጥቀስ፡፡ በጥንቷ ቤተ ክርስቲያን፡- ቅስና መሾም የሚገባው ሰው 30 ዓመት የሞላው እነደሆነና ኤጲስቆጶስ ደግሞ በ50 ዓመቱ መሾም እንዳለበት የሚደነግግ ቀኖና ነበር፡፡ በሂደት ግን ቤተ ክርስቲያን ተምረውና በቅተው ለተገኙ ልጆቿ 30 ወይም 50 ዓመት ባይሞላቸውም የቅስና እና ጵጵስና መዓርግ ሰጥታለች፡፡
521 views09:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-08 12:55:07 እነዚህ ሁሉ ከክርስቶስ የማዳን ተግባራት ጋር የተቆራኙት መንፈሳዊ መጋቤ ምላሾች ወይም አምልኮኣዊ መንፈሳዊ ግብረ መልሶች ዓላማቸው ነገረ ድህነት ወይም መዳን ላይ የተመሠረቱ ናቸው።

የኦርቶዶክስ ክርስቲያን የመጨረሻ ግብቡ ክርስቶስን መልበስ ወይም በክርስቶስ መኖር ወይም በባዕድ ቋንቋ ቴዎሲስ (Thosis) ለባሴ እግዚአብሔር ወይም ለባሴ ክርስቶስ መሆን ነው። ይህም ማለት ("መለኮትነት_deification ሱታፌ አምላክ") ወይም ከእግዚአብሔር ጋር በምስጢራዊ አንድነት መተባበር ነው። (mystical union with God) or (conformity to and intimate union with God)ማለት ነው።

እነደ ቤተክርስቲያኒቱ አስተምህሮ ኦርቶዶክሳዊ መዳን (Orthodox salvation) የሰው ልጅ የተፈጠረበትን መልክ ባለመታዘዝ ምክንያት በመጣሉ ያጣውን መልክ በክርስቶስ ኢየሱስ አግኝቶ ያገኘውን ሰማያዊ መልክ ጠብቆ መኖር ነው። ሰው እንዴት እንደተፈጠረና የነበረውን መልክ ሲያስረዳ ኦሪት ዘፍጥረት እንዲህ ይላል፦

ዘፍ 1
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²⁶ እግዚአብሔርም አለ፦ ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌአችን እንፍጠር፤ የባሕር ዓሦችንና የሰማይ ወፎችን፥ እንስሳትንና ምድርን ሁሉ፥ በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትንም ሁሉ ይግዙ። ²⁷ እግዚአብሔርም ሰውን በመልኩ ፈጠረ፤ በእግዚአብሔር መልክ ፈጠረው፤ ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው።

ባለመታዘዝ ምክንያት ሰማያዊ መልኩ ስለተገፈፈለሚያፍር ማንነት ተላልፎ ከልጅነት ወደባርነት ተሰጠ። ያጣነውን እግዚአብሔርን መምሰል በክርስቶስ መስቀል እንደተመለሠልን ሲያስረዳ “የመለኮቱ ኃይል፥ በገዛ ክብሩና በበጎነቱ የጠራንን በማወቅ፥ ለሕይወትና እግዚአብሔርን ለመምሰል የሚሆነውን ነገር ሁሉ ስለ ሰጠን፥ በእግዚአብሔርና በጌታችን በኢየሱስ እውቀት ጸጋና ሰላም ይብዛላችሁ።” — 2ኛ ጴጥሮስ 1፥2-3 ይላል።

ባለመታዘዝ ከጸጋው ልብስ የተራቆተውን የሰውን ልጅ “ለእውነትም በሚሆኑ ጽድቅና ቅድስና እንደ እግዚአብሔር ምሳሌ የተፈጠረውን አዲሱን ሰው ልበሱ።” — ኤፌሶን 4፥24 በማለት ያዘዋል።

ይህም በጥምቀት እንደሚከናወን ሲያስረዳ ፦“ከክርስቶስ ጋር አንድ ትሆኑ ዘንድ የተጠመቃችሁ ሁሉ ክርስቶስን ለብሳችኋልና።” — ገላትያ 3፥27 ይላል።

በዚህ የተጀመረው ሕይወት ተጠብቆና አድጎ ከክርስቶስ ጋር አንድ ሆኖ ለመኖር ጥረት ያደርጋል። ይህም የለበስንውን የጸጋ ልብስ የተመለሠልን የጠፋ ሰማያዊ መልክ መልሶ እንዳይጠፋ ሐዋርያው እንዲህ እያለ ያሳስባል፦

ኤፌሶን 4
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²⁵ ስለዚህ ውሸትን አስወግዳችሁ፥ እርስ በርሳችን ብልቶች ሆነናልና እያንዳንዳችሁ ከባልንጀሮቻችሁ ጋር እውነትን ተነጋገሩ። ²⁶ ተቆጡ ኃጢአትንም አታድርጉ፤ ²⁷ በቁጣችሁ ላይ ፀሐይ አይግባ፥ ለዲያብሎስም ፈንታ አትስጡት።
²⁸ የሰረቀ ከእንግዲህ ወዲህ አይስረቅ፥ ነገር ግን በዚያ ፈንታ ለጎደለው የሚያካፍለው እንዲኖርለት በገዛ እጆቹ መልካምን እየሠራ ይድከም … ³⁰ ለቤዛም ቀን የታተማችሁበትን ቅዱሱን የእግዚአብሔርን መንፈስ አታሳዝኑ።
³¹ መራርነትና ንዴት ቁጣም ጩኸትም መሳደብም ሁሉ ከክፋት ሁሉ ጋር ከእናንተ ዘንድ ይወገድ። ³² እርስ በርሳችሁም ቸሮችና ርኅሩኆች ሁኑ፥ እግዚአብሔርም ደግሞ በክርስቶስ ይቅር እንዳላችሁ ይቅር ተባባሉ።

ምክንያቱም ድህነት በአንድ ቀን ብቻ የሚጠናቀቅ ሳይሆን በኑሮ ሁሉ የሚጠበቅ መሆኑን ሲያስረዳ ዳግም፦ “ስለዚህ፥ ወዳጆቼ ሆይ፥ ሁልጊዜ እንደ ታዘዛችሁ፥ በእናንተ ዘንድ በመኖሬ ብቻ ሳይሆን ይልቁን አሁን ስርቅ፥ በፍርሃትና በመንቀጥቀጥ የራሳችሁን መዳን ፈጽሙ፤” — ፊልጵስዩስ 2፥12 ይላል። ድህነት የሚጠበቅ መሆኑን ካልጠበቅነው ተመልሰን በባርነት ቀንበር የምንወድቅ መሆኑን ሲያስረዳ ጌታችን በወንጌል ይህን ምሳሌ መስሎ አስተምሯል፦

ማቴዎስ 18
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²³ ስለዚህ መንግሥተ ሰማያት ባሮቹን ሊቈጣጠር የወደደን ንጉሥ ትመስላለች። ²⁴ መቈጣጠርም በጀመረ ጊዜ፥ እልፍ መክሊት ዕዳ ያለበትን አንድ ሰው ወደ እርሱ አመጡ።
²⁵ የሚከፍለውም ቢያጣ፥ እርሱና ሚስቱ ልጆቹም ያለውም ሁሉ እንዲሸጥና ዕዳው እንዲከፈል ጌታው አዘዘ። ²⁶ ስለዚህ ባሪያው ወድቆ ሰገደለትና፦ ጌታ ሆይ፥ ታገሠኝ፥ ሁሉንም እከፍልሃለሁ አለው። ²⁷ የዚያም ባሪያ ጌታ አዘነለትና ለቀቀው፥ ዕዳውንም ተወለት። ²⁸ ነገር ግን ያ ባሪያ ወጥቶ ከባልንጀሮቹ ከባሮቹ መቶ ዲናር ዕዳ ያለበትን አንዱን አገኘና፦ ዕዳህን ክፈለኝ ብሎ ያዘና አነቀው። ²⁹ ስለዚህ ባልንጀራው ባሪያ ወድቆ፦ ታገሠኝ፥ ሁሉንም እከፍልሃለሁ ብሎ ለመነው።
³⁰ እርሱም አልወደደም፥ ግን ሄዶ ዕዳውን እስኪከፍል ድረስ በወኅኒ አኖረው። ³¹ ባልንጀሮቹ የሆኑ ባሮችም ያደረገውን አይተው እጅግ አዘኑ፥ መጥተውም የሆነውን ሁሉ ለጌታቸው ገለጡ። ³² ከዚያ ወዲያ ጌታው ጠርቶ፦ አንተ ክፉ ባሪያ፥ ስለ ለመንኸኝ ያን ዕዳ ሁሉ ተውሁልህ፤ ³³ እኔ እንደ ማርሁህ ባልንጀራህ የሆነውን ያን ባሪያ ልትምረው ለአንተስ አይገባህምን? አለው። ³⁴ ጌታውም ተቈጣና ዕዳውን ሁሉ እስኪከፍለው ድረስ ለሚሣቅዩት አሳልፎ ሰጠው። ³⁵ ከእናንተ እያንዳንዱ ወንድሙን ከልቡ ይቅር ካላለ፥ እንዲሁ ደግሞ የሰማዩ አባቴ ያደርግባችኋል።

ከዚህ የምንረዳው መክፈል የማንችለው በአዳም ምክንያት ተላልፎ የመጣዊ የቀዳማዊ በደል ውጤት በእርሱ በክርስቶስ የተከፈለ ሲሆን ከእኛ የሚጠበቀውን መንፈሳዊ ተግባር የማንወጣ ከሆነ የተከፈለው ዕዳ ድጋሜ ተሰርዞ በበደሉ ውጤት ተጠያቂ እንደምንሆን ነው።

ስለዚህ ኦርቶዶክሳዊው ነገረ ድህነት ከስሜታዊነት ይልቅ መንፈሳዊነትን ያገናዘበ በመሆኑ እንደዚህ በመሆን ውስጥ የሚገለጥ ነው። እንጅ ""መዳን በእምነት ብቻ ነው"" ብሎ ከሕይወት የሚፋታና የሚጠበቀውን ኃላፊነት እንዳይወጣ በሚያግድ ንድፈ ሐሳብ የታጠረ አይደለም።

ቴኦሎጃዊያን አባቶች ይህንን “God became man so that Man might become god.ሰው አምላክ ይሆን ዘንድ እግዚአብሔር ሰው ሆነ” በማለት የነገረ ድኅነትን መንገድ ተዋሕዶ መሆኑን ያስረዳሉ።

እግዚአብሔር ሰው በመሆኑ ምክንያት ያገኘነውን ሰማያዊነት ወይም ከእርሱ ጋር የምንኖርበት ምስጢራዊ አንድነት የተጠበቀለት ሰው መዳን ከዘላለማዊ የሞት እስራት ማምለጥ ብቻ ሳይሆን እዚህ እና አሁን በክርስቶስ ወደ ሕይወት መግቢያ በር ሆኖሎት በዚያም ማደግንና መጠበቅን ማእከል አድርጎ በእድሜው ሙሉ የሚጓዘው መንፈሳዊ ሕይወት ነው።

የኖቲክ መታደስ በመንፈሳዊ ሕክምና በምስራቃዊ ክርስትና ውስጥ ያለው ማዕከላዊ ንድፈ ሐሳብ ኑስ Nous በተለምዶ "አእምሮ" ወይም "ማወቅ ወይም መገንዘብ"mind" ወይም "understanding ተብሎ ይተረጎማል)፣ የግንዛቤው ማዕከል ይህም የአማኙ ወይም የግለሰቡ መሃል፣ ልብ (heart), ወይም መንፈስ (spirit) ነው።

ኑስ (nous) የሰው ውሳጣዊ ዓይን ወይም ነፍስ (soul) ነው። ይህም ማለት አመክንዮአዊ እና ሊታወቅ የሚችል ግንዛቤ ማለት ነው። ኦርቶዶክሳዊ መዳን የሚሰራው በዚህ ክፍል ነው። ምክንያቱም በአዳም ኃጢአት እና ውድቀት የተጎዳው በጭለማ አእምሮ የተገለጠው የሰው ልጅ ነፍስ ነበር። ለዚህ ነው ዮሐንስ ክርስቶስን ለዓለም የሚያበራ እውነተኛ ብርሃን ያለው።
348 views09:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ