2023-04-15 07:38:53
አክፍሎትን ማን ጀመረው
የሰሙነ ሕማማት የመጨረሻው አክፍሎት ይባላል የበረታ ከሐሙስ ጀምሮ አብዛኛው ከዓርብ ጀምሮ እስከ ትንሣኤ ያከፍላል የአክፍሎት መሠረቱ ሐዋርያት ናቸው
በመጀመሪያ የጌታን ትንሣኤ ሳላይ እህል ውሃ አልቀምስም ያለው ያዕቆብ እኹ ለእግዚእነ ወይም የጌታ ወንድም በመባል የሚታወቀው የአረጋዊው የዮሴፍ ልጅ ከጌታ ጋር ያደገው ቅዱስ ያዕቆብ ነው
ይህ አባት ቅዱስ ያዕቆብ የጌታችንን መከራ የተመለከተ የእመቤታችንን ሐዘን በዐይኑ ያየ በመጀመሪያ ቅዱስ የሴፍ የልጆቹ እናት በሞት ተለይታ ነበረና አራት ወንዶች ሦስት ሴቶች ልጆች እናታቸው የሞተችባቸውን ልጆች ያሳድግ የነበረው ጻድቁ ዮሴፍ እናታቸውን በሞት የነጠቀ እግዚአብሔር እናት ከቤተ መቅደስ አመጣላቸው እመቤታችን እናታቸው ለሞተችባቸው እናት ኾና መሰጠቷ በኃላ በመስቀል እንታችን ለሞተችብን ለሔዋን ልጆች ለኛ እናት ኾና እንደምትሰጠን የሚያመለክት ነበር ከጻድቁ ዮሴፍ ልጆች ከአራቱ ይህ ቅዱስ ያዕቆብ ትንሣኤውን ሳላይ አልቀምስም በማለቱ ሁሉም ተከተሉት እኛም አንበላም ብለዋል እመቤታችን ናት የጀመረችው የሚባለው እሷ ከልደት እስከ ቀራንዮ በመከራ ነው የኖረችው ደግሞም የሐኬትን እንጀራ አትበላም ተብሎ ተጽፏል ከልጇ የመከራ ጽናት አልተለየችም በመስቀል ለቅዱስ ዮሐንስ እናትህ ናት ብሎ በዮሐንስ አንጻር ለኛ የተሰጠች ናትና ከዚያን ሰዓት ጀምሮ ደቀመዝሙሩ ወደ ቤቱ ወሰዳት ምግቧም ሰማያዊ መና ነው ዐይኗም ማየት የለመደው ሥዕለ ኪሩብ ነው
ጆሮዋም መስማት የለመደው ትንቢተ ነቢያትን ቅዳሴ መላእክትን ነው
እግሯም የለመደው ወደ ቤተ መቅደስ መሄድ ነው
እጇም የለመደው ሐርና ወርቅ መፍተል መሶበወርቅ መስፋት ለተጠማ ውሻ ውሃ ቀድታ መስጠት ነበረ እመቤታችን ሰውነቷ በጾም አንደበቷ በትእግስት በጸሎት የታወቀ ስለኾነ እመቤታችን አክፍሎትን ጀመረችው መባሉ አያስደንቅም ታላቁ ሊቅ በረከታቸው ይደርብንና የኔታ ገብረ ሥላሴ ቅዱስ ያዕቆብ ወልደ ዮሴፍ እንደ ጾመ ሌሎችም እንደተከተሉት ተናግረዋል መጋቤ ብሉይ አለቃ ታየ በረከታቸው ይደርብንና እሳቸውም በተመሳሳይ የገለጹት ይንኑ ነው
ቅዱስ ያዕቆብ የጌታ ወንድም የተባለበት በቤተ የሴፍ አብረው ስላደጉ ነው ይህ ቅዱስ ያዕቆብ አብዝቶ በመቆም ይጸልይ ስለነበር እግሩን ያመው ነበረ በዚህ ምክንያት የኢየሩስ አሌም ኤጲስ ቆጶስ ኾነ የመጀመሪያውን የሐዋርያት ጉባኤ ሲኖዶስ በሊቀመንበርነት የመራው ይህ ቅዱስ ያዕቆብ የጌታ ወንድም የተባለው ነው በመጽሐፍ ቅዱስ ባለ አምስት ምዕራፍ መልእክት የጻፈ እሱ በሌላም ይህ አባት በሶርያ ቤተክርስቲያን ጻድቁ ያዕቆብ በ60 ዓም የደረሰው የእመቤታችን ቅዳሴ ይገኛል The Anaphora Of St Mary The Liturgy Of St James The Just 60 (A D )ነው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ከሐዋርያት የቀጠለ ትምሕርት አሠረ ክህነት ያላት ተሰምቶ የማይጠገብ ትምህርት ሥርዓት ጸሎት ዜማ ወዘተ ከፈጣሪ የተሰጣት ብቸኛ በምድር ያለች ሰማያዊት የእግዚአብሔር መንግሥት ናት ለሁላችሁም መልካም የትንሣኤ በዓል ይሁንላችሁ።
686 views04:38