Get Mystery Box with random crypto!

ብሒላተ አበው ወእመት ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ

የቴሌግራም ቻናል አርማ behlateabew — ብሒላተ አበው ወእመት ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ
የቴሌግራም ቻናል አርማ behlateabew — ብሒላተ አበው ወእመት ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ
የሰርጥ አድራሻ: @behlateabew
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 13.08K
የሰርጥ መግለጫ

የቀድሞ አበው እና እመት የተናገሯቸው መንፈሳዊ ጥበብ
"የእግዚአብሔር ልጅ ሰው የሆነው እኛ አማልክት ዘበጸጋ እንሆን ዘንድ ነው።"
ቅዱስ አትናቴዎስ
👇👇👇👇👇👇👇👇
👉 @behlateabew 👈
👉 @behlateabew 👈
👆👆👆👆👆👆👆👆
https://t.me/joinchat/AAAAAESAiVPCib48ZxL1Pw

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 5

2023-04-15 07:38:53
622 views04:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-15 06:48:37 "በወገቡ የታጠቀውን ማድረቂያ አይተው መላእክት አደነቁ፤ ስሙ ከፀሓይና ከጨረቃ በፊት የነበረ ርሱ አገልጋይ ኾነ፤ ሕያው ጌታን ሱራፌል ያመሰግኑታል፤ ቦታውን ግን አያውቁም፤ ሱራፌልን የፈጠረ ርሱ በራት ጊዜ ወገቡን ዘርፍ ባለው ዝናር ታጠቀ፤ እንዳያቃጥል በመፍራት የማይታይ እሳት ለሐዋርያት አገልጋይ ኾኖ አብነት ይኾናቸው ዘንድ የትሕትና ሥራን የሚሠራበትን ውሃ በኩስኩስት ቀዳ የደቀ መዛሙርቱን አለቃ ጴጥሮስንም እግሩን ሊያጥበው ጠራው"

ሃይ. አበው ዘያዕቆብ ዘሥሩግ ክፍል 9
647 views03:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-15 06:30:34 #ቀዳም_ሥዑር (የተሻረችው ቅዳሜ)

የዐቢይ ጾም የመጨረሻዋ ቅዳሜ ብዙ ስያሜዎች አሏት፦

#ቀዳም_ሥዑር፡-
በዚች ዕለች ከድሮው በተለየ መልኩ የጌታችንን መከራ በማሰብ በጾም ታስባ ስለምትውል የተሻረችው ቅዳሜ ትባላለች፡፡ የማትጾመዋ ቅዳሜ ስለምትጾም ስዑር /የተሻረች/ ተብላለች በዓል መሻርን አይመለከትም በቀዳም ሥዑር ሌሊት ሥርዓቱ የሚጀመረው በመኀልየ ሰሎሞን ምንባብ ነው፡፡ ማኀሌቱም እዝሉ እየተቃኘ እየተመጠነ፣ እየተዘመመ እየተመረገደ እየተጸፋ ያድራል፡፡ ጥዋት አቡን መዋሥዕት ውዳሴ ማርያም ዜማ ተደርሶ ወለመልአከ ሕይወትሰ ሰቀልዎ በሚለው ሰላም ይጠናቀቃል፡፡በዚህ ዕለት ልብሰ ተክህኖ የለበሱ ካህናትና ዲያቆናት ቄጤማ ተሸክመው ቃጭል ሲያቃጨሉ መታየታቸው ዕለተ ትንሣኤውን ለሚናፍቅ ምእመን ትልቅ ብስራት ነው፡፡

#ለምለም_ቅዳሜ፡-
ካህናቱ ለምእመናን ለምለም ቀጤማ የሚያድሉበት ዕለት ስለሆነ በዚህ ተሰይሟል፡፡ ቀጤማውንም ምእመናን እስከ ትንሣኤ ሌሊት በራሳቸው ላይ ያስሩታል፡፡ በቀዳም ስዑር ቀሳውስቱና ዲያቆናቱ ቃጭል /ቃለዓዋዲ/ እየመቱ ገብረ ሰላመ በመስቀሉ ትንሣኤሁ አግሃደ የሚለውን ያሬዳዊ ዜማ በመዘመር፤ ጌታ በመስቀሉ ሰላምን እንደሰጠን እና ትንሣኤውንም እንደገለጠልን በማብሰር፤ ቄጤማውን ለምእመናን ይሰጣሉ፡፡ ምእመናኑም በቤተ ክርስቲያን አገልግሎት የሚውል ገጸ በረከት ያቀርባሉ፡፡ ቄጤማውንም በራሳቸው ያስራሉ፡፡ ይህም አይሁድ ጌታችንን እያሰቃዩ ሊሰቅሉት ባሉ ጊዜ የእሾህ አክሊል ጭንቅላቱ ላይ ያሠሩበትን ድርጊት የሚያስታውስ ነው፡፡

(የቀጤማው አመጣጥና ምስጢርም ከአባታችን ከኖኅ ታሪክ ጋር የተያያዘ ነው፡፡ ምድር በማየ አይኅ /በጥፋት ውኃ/ በጠፋችበት ወቅት የኖኅ ታማኝ መልእክተኛ ርግብ የውኃውን መጉደል ያበሰረችው ቀጤማ ይዛ በመግባት ነው፡፡ ዛሬም ለሐዲስ ኪዳን ክርስቲያኖች የኃጢአት ውኃ ጐደለ፣ የኃጢአት ውኃ ጠፋ በክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ነጻነት ተሰበከ ታወጀ በማለት ካህናት ቄጠማ ይዘው ምእመናንን ያበሥሩበታል፡፡)

#ቅዱስ_ቅዳሜ፡-
ቅዱስ ቅዳሜ መባሉ ቅዱስ የሆነ እግዚአብሔር በጥንተ ተፈጥሮ ፍጥረታትን አከናውኖ ከፈጠረ በኋላ በዚህ ቀን ከሥራው ሁሉ ያረፈበት ነው፡፡ በዘመነ ሐዲስ ደግሞ የማዳን ሥራውን ሁሉ ፈጽሞ በሥጋው በመቃብር ሲያርፍ፣ በነፍሱ ሲዖልን በርብሮ ባዶዋን አስቀርቷታል፡፡ በዚያ ለነበሩት ነፍሳትም የዘለዓለም ዕረፍትን ያወረሰበት ዕለት ስለሆነ ከሌሎቹ ዕለታት የተለየ ዕለት ለማለት ቅዱስ ቅዳሜ ተብሏል፡፡

(ስምዐ ተዋሕዶ የስምዐ ጽድቅ ልዩ እትም ዘሰሙነ ሕማማት ሚያዝያ 2004 ዓም)
654 views03:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-15 06:30:32
542 views03:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-14 18:39:57
‹‹የሚሠዋ በግ እርሱ ነው፤ የሚሠዋ ካህን እርሱ ነው፡፡
ከባሕርይ አባቱ ከአብ ከባሕርይ ሕይወቱ ከመንፈስ ቅዱስ ጋርም መሥዋዕት የሚቀበል እርሱ ነው። በፈቃዱ መከራን በሥጋው የተቀበለ መከራንም ሁሉ የታገሠ እርሱ ነው፡፡ እንደ በግ ሊሠዋ መጣ፤
በግ በሚሸልተው ሰው ፊት እንዳይናገር አልተናገረም፤ በአንደበቱ ሐሰት አልተገኘበትም፡፡››
ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ
485 views15:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-14 18:39:47 ብሒላተ አበው ወእመት ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ pinned «... የአስቆሮቱ ይሁዳ ራሱ ጌታችን ከታገሣቸው መከራዎች አንዱ ነው። ሕማማት ዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ»
15:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-14 17:04:16
"የሕይወትን ራስ የእሾህ ዘውድ ደፉበት። ብርሃንን እንደ ልብስ የሚጎናጸፈውን ልብሱን ገፈው ቀይ ግምጃ አለበሱት።"

ቅዳሴ ዘሠለስቱ ምእት

ይህ ሁሉ ለእኔ ኃጢአት የተከፈለ ነው
534 views14:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-14 16:57:39 “ ሁሉን የያዘውን ያዙት ፣ ሁሉን የሚገዛውን አሠሩት ፣ የሕያው አምላክን ልጅ አሠሩት ፣ በቁጣ ጎተቱት ፣ በፍቅር ተከተላቸው ፣ በሚሸልተው ፊት እንደማይናገር እንደ የዋህ በግ በኋላቸው እየተከተለ ወሰዱት፡፡

ሊቃነ መላእክት በመፍራትና በመንቀጥቀጥ በፊቱ የሚቆሙለትን በአደባባይ አቆሙት ኃጢአትን ይቅር የሚለውን ኃጢአተኛ አሉት ፣ በፈራጆች ላይ በሚፈርደው በእርሱ ላይ ፈረዱበት፡፡ ለሱራፌል ዘውድ የሚያቀዳጃቸውን የእሾኽ ዘውድ አቀዳጁት። ለኪሩቤል የግርማ ልብስ የሚያለብሳቸውን ቀይ ግምጃ አለበሱት። የመላእክት ሠራዊት በፍጹም መደንገጥ ለሚሰግዱለት እየዘበቱበት በፊቱ ተንበረከኩ፡፡

ይህን ያህል ትሕትና እንደምን ያለ ትሕትና ነው?
ይህን ያህል ትዕግሥት እንደምን ያለ ትዕግሥት ነው?
ይህን ያህል ዝምታ እንደምን ያለ ዝምታ ነው?
ይህን ያህል ሰውን ማፍቀር እንደምን ያለ ፍቅር ነው?
ፍቅር የአምላክን ልጅ ከዙፋኑ ሳበው እስከ ሞትም አደረሰው''

ቅዳሴ ዮሐንስ አፈወርቅ
452 viewsedited  13:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-14 15:03:05
"ጌታ ሆይ ረጅሙን ስቃይህን ማን ሊገልጸው ይችላል"
ቅዱስ ኤፍሬም

እንኳን ለበዓለ ስቅለት አደረሰን አደረሳችሁ!
494 views12:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-14 11:45:24 "የጌታችን የኢየሱስ እናቱ እመቤታችንም ከእኅቷ ከቀለዮጳ ልጅ ከማርያምና ከመግደላዊት ማርያም ከመስቀሉ አጠገብ ቆማ ሆድ በሚያቃጥል አንጀት በሚቆራርጥ በጽኑዕ ኀዘን እየጮኸች ታለቅስ ነበር። ከመስቀሉ ሥር ወደቀች፤ ለመሞትም ደረሰች።
፯ ቱም የመላእክት አለቆች መጥተው አረጋጓት፤ አጽናኗት። እርሷ ግን ለቅሶ መተውና መጽናናትንም አልቻለችም። አቧቷ ዳዊትም እሳት በሆነ ፈረስ ተቀምጦ መጥቶ አጽናናት። እሷ ግን ለቅሶ መተውን መጽናናትን እምቢ አለች።"

                ድርሳነ ማኅየዊ ዘዓርብ
594 views08:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ