Get Mystery Box with random crypto!

ብሒላተ አበው ወእመት ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ

የቴሌግራም ቻናል አርማ behlateabew — ብሒላተ አበው ወእመት ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ
የቴሌግራም ቻናል አርማ behlateabew — ብሒላተ አበው ወእመት ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ
የሰርጥ አድራሻ: @behlateabew
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 13.08K
የሰርጥ መግለጫ

የቀድሞ አበው እና እመት የተናገሯቸው መንፈሳዊ ጥበብ
"የእግዚአብሔር ልጅ ሰው የሆነው እኛ አማልክት ዘበጸጋ እንሆን ዘንድ ነው።"
ቅዱስ አትናቴዎስ
👇👇👇👇👇👇👇👇
👉 @behlateabew 👈
👉 @behlateabew 👈
👆👆👆👆👆👆👆👆
https://t.me/joinchat/AAAAAESAiVPCib48ZxL1Pw

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2023-05-05 13:30:59
"ሕዝቡም የሚሾመውን ሰው በሥሙና በመልኩ በጠባዩም ሊያውቁት ይገባል።

ከመራጮች ወገን በሥራው እንጂ በዓይኑ አንዱ እንኳ ጠቅሶ ሊያሳየው አይገባውም!

እርሱም በሥርዓት ጸንቶ መኖር ይገባዋል። ሁሉም ለእርሱ የሚገባውን እርሱን ይጠይቁ፤ አምስቱ ግብራት በእርሱ ዘንድ ይገኙ እንደሆነም ይመዝኑ ይመርምሩ።

ከእነርሱም አንዱ በመጽሐፍ እንደተገለጸ ሃይማኖትን መጠበቅና ከሐዋርያት ቃል በመሰብሰብ የጸና መሆን ነው"

ፍትሐ ነገስት አንቀጽ 4፥72
1.5K views10:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-04 15:03:08 ባሎች ለሚስቶቻቸው ሊያሳዩአቸው የሚገባ ፍቅር በቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

ቤተ ክርስቲያን ለክርስቶስ እንደምትገዛ ሚስትህ ለአንተ ትገዛልህ ዘንድ ትሻለህን? ክርስቶስ ለቤተ ክርስቲያን እንዳደረገላት አንተም እንዲሁ ለሚስትህ አድርግላት፡፡ ሕይወትህን ስለ ርሷ አሳልፈህ መስጠት ካለብህ ስለርሷ ሕይወትህን አሳልፈህ ስጥ፤ መከራም መቀበል ካለብህ መከራን ለመቀበል አትሰቀቅ፡፡

አንተ ይህን ብትፈጽመው ስንኳ ክርስቶስ ለቤተ ክርስቲያን ካደረገላት ጋር ሲነጻጸር የሚወዳደር አይደለም፡፡ ምክንያቱም አንተ ይህን ያደረግኸው ከአንተ ጋር ፈጽማ ለተዛመደችህ ለአንዲት ሴት ነው፡፡ “እርሱ ግን ከእርሱ ለተመለሰችውና ለጠላቸው ራሱን አሳልፎ ሰጠ፡፡” ርሱ ከርሱ የተመለሰችውንና የጠላችውን እንዲሁም ያቃለለችውን ገንዘቡ ሲያደርጋት በማስፈራራት፣ በማስገደድ ወይም ይህን በመሳሰሉ ነገሮች አልነበረም፤ ነገር ግን ኀዘን ባልተቀላቀለበት ፍጹም በሆነ ፍቅር በመሆን ነበር፡፡ አንተም ለሚስትህ እንዲሁ አድርግላት አዎን! ምናልባት ሚስትህ አንተን ልታመናጭቅህ፣ ልትንቅህ፣ ልታፌዝብህም ትችላለች፤ ቢሆንም ግን አንተ ለርሷ ካለህ አርቆ አሳቢነት ንጹሕ ፍቅርና ኀዘኔታ የተነሣ ልትታገሣት ይገባሃል፡፡

ከሰው ሁሉ ጋር ተስማምቶ ለመኖርም ከእነዚህ የተሻሉ ነገሮች ፈጽሞ አናገኝም፡፡ በተለይም ለባልና ለሚስት፡፡ አንድ ሰው አገልጋይ ባሪያውን በማስፈራራት ለመግዛት ቢሞክር ለጥቂት ጊዜአት ሊገዛለት ይችላል፡፡ ሆኖም ይህ ባሪያ እንዲህ ዓይነት አገዛዝ ስለማይመቸው ከእርሱ ፈጥኖ ይሸሻል፡፡ ነገር ግን አንድ ሰው የሕይወቱን አጋር፣ የልጆቹን እናት፣ የደስታው ሁሉ ምንጭ የሆነችውን ሚስቱን በፍቅርና በፍጹም አክብሮት እንጂ ልክ እንደ ባሪያ በፍርሃት ሰንሰለት በማሰር ወይም በማስጨነቅ ርሷን ሊገዛት መሞከር አይገባውም፤ ሚስት በባልዋ ምክንያት የምትሸበር ከሆነ አንድነታቸው ምን ዓይነት አንድነት ነው? ከባሪያ ጋር እንደ መኖር ከሚስት ጋር መቀመጥ ለባል የሚፈጥርለት ምን ዓይነት ደስታ ነው? አዎን ይልቁኑ አንተ ስለ ርሷ ስትል ብዙ መከራዎችን መቀበል ሲገባህ በተቃራኒው በቁጣ ርሷን በማስጨነቅና በማሸበር ታስፈራራታለህን? ክርስቶስ እንዲህ አላደረገም፡፡

“በውኃ መታጠብና ከቃሉ ጋር አንጽቶ አንዲቀድሳት ስለ ርሷ (ስለ ቤተ ክርስቲያን) ራሱን አሳልፎ ሰጠ ፡፡ ከቃሉ እንደምንረዳው ቤተ ክርስቲያን (እኛ) አስቀድማ ንጽሕት አልነበረችም፤ ጉድፍ ነበረባት፤ መልከ ጥፉም ነበረች፡፡ ስለዚህም ለእርሱ የተገባች አልነበረችም፡፡ አንተ እንደ ቤተ ክርስቲያን የሆነችውን ሴት ሚስትህ ትሆን ዘንድ አትመርጥም፡፡ ቤተ ክርስቲያን ከክርስቶስ የተለየችውን ያህል ከአንተ ፈጽማ የማትስማማውን ሴት ሚስትህ ትሆን ዘንድ ወደ አንተ አታቀርባትም፡፡ እርሱ ግን እጅግ መልከ ጥፉ ብትሆንም አልጠላትም፣ አልተጸየፋትም፣ ስለ መልከ ጥፉነቷ የተጻፈውን መስማት ትፈልጋለህን? ቅዱስ ጳውሎስ ስለ ርሷ ምን እንደሚል ስማ “ቀድሞ ጨለማ ነበራችሁ” (ኤፌ.፭፡፰) አላት፤ የገጽታዋን መጥቆር ትመለከታለህን? ከጨለማስ የበረታ ጥቁረት ምን አለ? የአመሏን መክፋት ደግሞ ስማ “በክፋትና በምቀኝነት” ይልና “የምንኖር” ይላል፤ ስለ ነውሮቿ ደግሞ “የማንታዘዝና የምንስት ለልዩ ልዩ ተድላ እንደ ባሪያዎች የምንገዛ” ይላታል (ቲቶ.፫፡፫)፡፡

ነገር ግን ለርሷ ስለተደረገላት በጎነት ምን ማለት ይቻለኛል? ርሷ ስንፍናን የተሞላችና ክፉ አንደበት የነበራት እንዲሁም በነውሮቿ ሁሉ ያደፈች ብትሆንም እነዚህ ሁሉ ጠባዮቿ ከርሷ አላራቀውም፡፡ ነገር ግን ልክ የደስ ደስ እንዳላት ልጃገረድ በአፍቀሪም ዘንድ ለምትወደድ ውብ ሴት እንደሚደረገው ርሱ ስለ ርሷ ራሱን አሳልፎ የሰጠ አይደለምን? ይህንንም በማድነቅ ቅዱስ ጳውሎስ “ስለጽድቅ የሚሞት በጭንቅ ይገኛልና ስለ ቸር ሰው ግን ሊሞት ስንኳ የሚደፍር ምናልባት ይገኛል” ይልና “ነገር ግን ኃጢአተኞች ሳለን ክርስቶስ ስለ እኛ ሞቷልና”(ሮሜ.፭፡፯-፰) ብሎአል፡፡ በዚህ መልክ ርሷ ለርሱ ትሆን ዘንድ አቀረባት፤ በመንፈሳዊ ውበትም አስጌጣት፤ ንጽሕት አደረጋት፤ ስለ ርሷም ራሱን አሳልፎ ለመስጠት ስንኳ የጨከነ ሆነ፡፡

(የትዳር አንድምታ እንደ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ አስተምህሮ ገጽ 17-19 - በመምህር ሽመልስ መርጊያ)
1.7K views12:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-03 11:58:50
1.6K views08:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-03 11:58:49 ቤተ ክርስቲያን "እንቁዎቼ" ከምትላቸው ሴት ጻድቃን አንዷ ቅድስት እንባ መሪና ናት። ጣዕመ ዜናዋ ሙሉ ሕይወቷ አስገራሚም አስተማሪም ነው። ቅድስቷ በአራተኛው መቶ ክፍለ ዘመን በምድረ ግብጽ ተወልዳ ያደገች ክርስቲያን ናት። ወላጆቿ ከእርሷ በቀር ሌላ ልጅ የሌላቸው ሲሆን በአኗኗራቸውም ደግና ቅን ነበሩ።
ቅድስት እንባ መሪና ትክክለኛ ስሟ "መሪና" ነው። ምክንያቱም "እንባ መሪና" የወንድ ስም ነውና። ነገር ግን በወንድ ስም የተጠራችበት የራሱ ታሪክ አለውና እርሱን እንመለከታለን።
ቅድስት መሪና ገና ልጅ ሳለች እናቷ ማርያም ሞተችባት። ደግ አባት አንድ ልጁን በሥጋዊም በመንፈሳዊም ሳያጐድልባት አሳደጋት። ዕድሜዋ አሥራ አምስት ዓመት በሆነ ጊዜ ወደ ፊቱ አቅርቦ "ልጄ! እኔ ወደ ገዳም ስለምሔድ አንቺን መልካም ባል ላጋባሽ።" አላት።
ቅድስት መሪናም "ነፍሰ ዚአከ ታድኅን ነፍሰ ዚአየኑ ታጠፍእ - የአንተን ነፍስ አድነህ እንዴት የእኔን ትተዋታለህ? እኔም እመንናለሁ።" አለችው። አባቷ የተናገረችው ከልቧ እንደሆነ ሲያውቅ "ልጄ! ገዳም ሁሉ በአካባቢው የወንድ ብቻ ነውና ስሚኝ።" አላት።
እርሷ ግን "አባቴ! ግዴለህም ስሜን እንደ ወንድ ቀይረህ አለባበሴንም ለውጥ።" አለችው። (እንደ ወንድ ለበሰች ማለት ግን እንደ ዘመኑ ዓይነት እንዳይመስላችሁ አደራ!)
ከዚያ አባትና ልጅ ሃብት ንብረታቸውን ሸጠው ለነዳያን አካፈሉ። በፍጹም ልባቸውም መነኑ። በደረሱበት ገዳም ቅድስት መሪና በወንድ ስም "እንባ መሪና" በሚል ገባች። ቀጣዩ ሥራዋ እንደ ወንዶች እኩል መስገድ፣ መጾምና መጸለይ ነበር።
ይህችን ቅድስት ልናደንቃት ግድ ይለናል። ማንም በእርሷ አይፈተንም፤ አያውቋትምና። እርሷ ግን ወጣት ሆና አንድም ሴት በሌለበት ገዳም ጸንቶ መቆየት በራሱ ልዩ ነው። መልአካዊ ኃይልንም ይጠይቃል።
ተጋድሎዋ በጣም ስለ በዛ ወንድሞች መነኮሳት ይደነቁባት ነበር። ጺም ስለሌላትና ድምጿ ቀጭን ስለሆነ አልተጠራጠሩም። ምክንያቱም ጃንደረባ ናት ብለው አስበዋልና። ከጥቂት ዓመታት በኋላ ግን አባቷ ታሞ ከማረፉ በፊት አበ ምኔቱን ጠርቶ "ወደ ከተማ ልጄን እንዳትልክብኝ አደራ!" ብሎት ነበር።
ያም ሆኖ አንዳንድ መነኮሳት ቅሬታ በማንሳታቸው ወደ ከተማ ተላከች። ችግሩ ለተልእኮ ባደሩበት ቤት አንድ ጐረምሳ ገብቶ የአሳዳሪውን ልጅ ከክብር አሳንሷት ሔደ። ሲወጣም "ድንግልናሽን ያጠፋ ማን ነው? ካሉሽ ያ ወጣት መነኩሴ አባ እንባ መሪና ነው በይ።" አላት።
ከሦስት ወራት በኋላ የዚያች ዘማ ሴት ጽንስ በታወቀ ጊዜ ለአባቷ "አባ እንባ መሪና እንዲህ አደረገኝ።" አለችው።
አባት መጥቶ እየጮኸ መነኮሳትን ተሳደበ። አበ ምኔቱ ግራ ተጋብቶ ቢጠይቀው "የአንተ ደቀ መዝሙር እንባ መሪና ልጄን ከክብር አሳነሳት።" አለው። አበ ምኔቱ እውነት መስሎታልና ቅድስቲቱን ጠርቶ ቁጣና እርግማንን አወረደባት። በዚያች ሰዓት ተንበርክካ አንድ ነገር ወሰነች።
"ሴት ነኝ።" ብሎ መናገሩስ ቀላል ነው። ግን ደግ ናትና የእነዚያን አመጸኛ ሰዎች ኃጢአት ልትሸከም ወሰነች። ቀና ብላ "ማሩኝ ወጣትነት ቢያስተኝ ነው?" አለቻቸው። ተቆጥተው ዕለቱን እየገፉ ከገዳም አስወጧት። ከባድ ቀኖናም ጫኑባት። ከስድስት ወራት በኋላም የእርሷ ልጅ ነው የተባለ ሕፃን አምጥተው ሰጧት።
ይህኛው ግን ከባድ ፈተና ሆነባት። እንዳታጠባው አካሏ በገድል ደርቋል። በዚያ ላይ ድንግል የሆነች ሴት ወተት የላትም። ነገር ግን በእግዚአብሔር ቸርነት የበጋውን ሐሩር የክረምቱን ቁር ራሷ ታግሣ ለሕፃኑ ከእረኞች ወተት እየለመነች እየመገበች ሦስት ዓመታት አለፉ።
በዚህ ጊዜ ወደ ገዳሙ ከከባድ ቀኖና ጋር ተመለሰች። ሕፃኑን ስታሳድግ፣ ለገዳሙ ስትላላክ፣ ምግብ ስታዘጋጅ፣ ውኃ ስትቀዳ፣ የእያንዳንዱን ቤት ስታጸዳ ሠላሳ ሰባት ዓመታት አለፉ። ሕፃኑም አድጐ ደግ መናኝ ወጣው። (የቅድስቷ እጆች ያሳደጉት የታደለ ነው።)
በመጨረሻ ቅድስት መሪና (እንባ መሪና) ታማ ዐረፈች። እንገንዛለን ብለው ቢቀርቡ ሴት ናት። እጅግ ደንግጠው አበ ምኔቱን ጠሩት። በዙሪያዋ ከበው እንባቸውን አፈሰሱ። ጸጸት እንደ እሳት በላቻቸው። ሥጋዋን በክብር ገንዘው በአጐበር ጋርደው በራሳቸው ተሸክመው ምሕላ ገቡ።
ሙሉውን ቀን "ስለ ቅድስት መሪና ብለህ ክርስቶስ ሆይ ማረን?" ሲሉ ዋሉ። ድንገት ግን ከተባረከ ሥጋዋ "ይቅር ይበለን።" የሚል ድምጽን ሰምተው ደስ ብሏቸው ቀበሯት። እነዚያ ዝሙተኞችም ከእርሷ ይቅርታን እስካገኙበት ቀን አብደው ኑረዋል።
1.6K views08:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-03 11:51:04 “ሰይጣን ለብዙ ሰዓት ስለ እግዚአብሔር እንድናወራ ሊፈቅድ ይችላል በፍጹም ግን እግዚአብሔርን እንድናዋራው አይፈቅድም፡፡''
አባ ብሾይ
1.8K views08:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-29 14:20:11
2.0K views11:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-23 07:46:48 የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ በቴክኖሎጂ በመታገዝ የርቀት እና የኦንላይን ትምህርት ምዝገባ የፊታችን ሰኞ እንደሚጀምር ገለፀ !

ሚያዝያ 13 ቀን 2015 ዓ.ም (ተ.ሚ.ማ/አዲስ አበባ)

የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ በሀገር ውስጥ እና በውጪ ሀገራት ለሚገኙ ምዕመናን በቴክኖሎጂ በመታገዝ በርቀት እና በኦንላይን ትምህርት ሊሰጥ ዝግጅቱን አጠናቆ ምዝገባውን የመጪው ሰኞ ሚያዝያ 16 ቀን 2015 ዓ.ም እንደሚጀምር ገልጿል።

ዩኒቨርስቲው በልዩ ልዩ የሥራ መስክ ላይ ተሰማርተው በጊዜ እና በቦታ ርቀት ትምህርት መማር ላልቻሉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምዕመናን በርቀት እና በኦንላይን ትምህርታቸውን እንዲማሩ በማሰብ ምዝገባውን ሊጀምር መሆኑን ነው የገለጸው።

የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ በርቀት እና በኦንላይን ትምህርት የሙሉ ጊዜ ሙያዊ ሠራተኞችን፣ ሀገርን በመከላከል ላይ ተሰማርተው የሚገኙ ወታደሮችን፣ በስደት ምክንያት በአንድ ቦታ ነዋሪ መሆን ያልቻሉ ሰዎችና በተለያዩ የሥራ መስክ ላይ የሚገኙ ባለሙያዎችን ያላቸውን ሥራ እና ማኅበራዊ ግንኙነት እንዲሁም የአኗኗር ዘይቤ ሳይቀይሩ ካላቸው እውቀትና ጥበብ በተጨማሪ ከፍተኛ የኦርቶዶክሳዊ ነገረ መለኮት ትምህርት ማግኘት ያስችላልም ነው የተባለው።

በርቀት እና በኦንላይን ትምህርት ዘርፍ የሚሰጣቸው የትምህርት መስኮችም

በነገረ መለኮት የትምህርት ዘርፍ በዲግሪ
1, የዶግማ ትምህርት
2, የቅዱሳት መጽሓፍት ትምህርት
3, የቤተ ክርስቲያን ታሪክ ትምህርት
4, የሥርዓተ አምልኮና ትምህርተ ኖሎት
5, ሥነ ምግባርና ኦርቶዶክሳዊ መንፈሳዊነት

በኢትዮጵያ ጥናት ትምህርት ዘርፍን በዲግሪ
1, የኢትዮጵያ ታሪክ
2, የግእዝ ቋንቋና ሥነ ጽሑፍ
3, የሥነ ጥበብና ባህል ጥናት በተጨማሪም በዲፕሎማ የነገረ መለኮት ትምህርት እና በሠርተፊኬት የነገረ መለኮት ትምህርት መሆኑ ተገልጿል።

ትምህርቱን ለመማርም ከአጥቢያ ቤተ ክርስቲያን የአባልነት ማስረጃ፣
ከትምህርት ተቋማት የተማሩበት ማስረጃ (መልቀቂያ) እና 4 ጉርድ ፎቶ በመያዝ መመዝገብ እንደሚችል ተገልጿል።

ይህም ተማሪዎች በአነስተኛ ወጪ ትምህርት እንዲያገኙ እና ዩኒቨርስቲው ለትምህርት የሚያወጣውን ከፍተኛ ወጪ በዝቅተኛ ደረጃ እንዲሆን እና የገቢ መጠኑም እንደሚጨምርም ተጠቁሟል።

ተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል
818 views04:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-23 07:46:48
671 views04:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-19 23:10:22
#የጋብቻ_ሕግጋት_ ~~~ #ሼርርርርርርርር

1.ከተጋቡ በኅላ አንድ አካል ናቸው። (ማቴ 19:4-6
2.መፋታት ክልክል ነው። (ሚል2:14)
3.አንድ ወንድ ለአንድ ሴት ። 1ኛ ቆሮ 7:2
4.የሚገባቸውን ሁሉ ማድረግ።
5.ባልም ለሚስትም በራሳቸሁ ሥልጣን የላቸሁም። 1ኛ ቆሮ 7:4
6.ኃላፊነትን መወጣት። ኤፌ5:20-23 ቆላ 3:18
7.ለጾምና ለጸሎት ካልሆነ አለመለያየት 1ኛ ቆሮ7:5
8.ሥጋዊ ጌጥ አለማብዛት ።1ኛ ጴጥ 3:1-4
9.ድንገተኛ ግጭት ቢከሰት ወዲያው መታረቅ።1ኛ ቆሮ 7:10-11
10.በሞት ካልሆነ አለመለያየት።1ኛ ቆሮ 7:39 እናሮሜ 7:2-3
ከሥጋዊ መንፈሳዊ የጋብቻ ዘመድ አለማግባት።ዘሌ 18:6-20 ዘሌ20:16-21፣ማር 6:17።
387 views20:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-18 05:56:09 ከትንሣኤ እሁድ በኋላ ያሉ ዕለታት ስያሜ

✞ ሰኞ- ማዕዶት ይባላል፡- ማዕዶት ማለት መሻገር፣ ማለፍ ማለት ነው፡፡ በዚህ ዕለት በፋሲካችን በክርስቶስ ትንሣኤ ከድቅድቅ ጨለማ ወደ ሚደነቅ ብርሃን፣ ከሞት ወደ ሕይወት፣ ከሲኦል ወደ ገነት፣ ከሃሳር ወደ ክብር መሻገራችንን እናስባለን፡፡

✞ ማክሰኞ- ቶማስ ይባላል፡- በዚህ ዕለት ቶማስ ጌታን አይቶ ማመኑ፤ ጌታዬና አምላኬ ብሎ መመስከሩ ይዘከራል፡፡ ዮሐ. 20፡27-29

✞ ረቡዕ- አልአዛር ይባላል፡- በዚህ ዕለት ትንሣኤና ሕይወት የሆነው ጌታ ኢየሱስ አልአዛርን ከሞት እንዳስነሳው እናስባለን፡፡ ክርስቶስ የሞትን ስልጣን የሻረ የሕይወት ራስ፤ የመቃብርን ሥርዓት ያጠፋ ትንሣኤ፡ በድልም ያረገ ንጉሥ መሆኑን እንመሰክራለን፡፡

✞ ሐሙስ- አዳም ሐሙስ ይባላል፡- በዚህ ዕለት ለአዳም የተሰጠው ተስፋ እና የተገባለት ኪዳን እንደተፈጸመ አዳምና ልጆቹ ነጻ እንደወጣን እናስባለን፡፡

✞ አርብ- ቅድስት ቤተክርስቲያን ይባላል፡- በዚህ ዕለት ቤተክርስቲያን በክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ስለመመስረቷ ይሰበካል፡፡ ክርስቶስ ስለ እርሷ ራሱን አሳልፎ ሰጥቶ ቤዛ ሆኖ በደሙ አንጽቶ በትንሣኤው ድል ሰጥቶ እንዳከበራት ይነገራል፡፡
ቤተክርስቲያን ስንል ሕንፃውን ሳይሆን አማኞችን ነው፤ ክርስቶስ ለሕንፃ አልሞተምና፡፡

✞ ቅዳሜ- ቅዱሳት አንስት ይባላል፡- በዚህ ዕለት ቅዱሳት አንስት የክርስቶስን አካል ሽቶ ለመቀባት ጨለማ አቋርጠው ወደ መቃብር መምጣታቸውና ትንሣኤውንም ቀድመው ማየታቸው ይሰበካል፡፡

✞ እሁድ- ዳግም ትንሣኤ ይባላል፡- በዚህ ዕለት ክርስቶስ ለሦስተኛ ጊዜ ለደቀመዛሙርቱ ተገልጦ ሰላምን መስበኩ እና ሥልጣንን መስጠቱ ይሰበካል፡
431 views02:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ