Get Mystery Box with random crypto!

የቤተክርስቲያን ታላላቅ ችግሮች የሚመጡት ከየት ይመስልሃል? ባስልዮስ ሆይ! እስኪ ንገረኝ! በቤ | ብሒላተ አበው ወእመት ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ

የቤተክርስቲያን ታላላቅ ችግሮች የሚመጡት ከየት ይመስልሃል?

ባስልዮስ ሆይ! እስኪ ንገረኝ! በቤተ ክርስቲያን እንዲህ ያሉ ታላላቅ ችግሮች ከየት የሚመጡ ይመስልሃል? እኔ እንደሚመስለኝ የእነዚህ ብቸኛ ምንጫቸው ጳጳሳትና ካህናት የሚመረጡበት መንገድ ጥንቃቄ የጎደለውና እንዲሁ በዘፈቀደ በመኾኑ ነው፡፡

ከእርሱ በታች ካሉ ከሌሎች የሰውነት ክፍሎች የሚመነጨውን ክፉና ደካማ አሳብ ለመግዛትና ለመቈጣጠር ይችል ዘንድ ራስ ከኹሉም በላይ ጠንካራና ጽኑዕ ሊኾን ይገባዋልና፡፡ ራስ ደካማ ከኾነና እነዚህን ለመቈጣጠር ካልቻለ ግን ራስም ደካማ ከኾኑት አካላት የባሰ ደካማ ይኾናል፡፡ ሌላውን የሰውነት ክፍልም ያጠፋል፡፡"

(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
በእንተ ክህነት መጽሐፍ
ገብረ እግዚአብሔር ኪደ የተተረጎመው)